Page 1 of 1

ከመቶ ሺ ደንቆሮ የዘር ፖለቲከኛ አንጎሎች የላቀ አንድ አስገራሚ ምሁር !!

Posted: 19 Jun 2020, 03:02
by Horus
ይህ ነው የ21ኛ ዘመን አንጎል ። ኢትዮጵያ ዛፍ በመትከል ብቻ ያባይን ዉሃ መቆጣጠር እና መጠቀም መቻሉን የሚያቅ ስንት የጎሳ ካድሬ አለ?

Re: ከመቶ ሺ ደንቆሮ የዘር ፖለቲከኛ አንጎሎች የላቀ አንድ አስገራሚ ምሁር !!

Posted: 19 Jun 2020, 03:24
by Andertan
Horus wrote:
19 Jun 2020, 03:02
ይህ ነው የ21ኛ ዘመን አንጎል ። ኢትዮጵያ ዛፍ በመትከል ብቻ ያባይን ዉሃ መቆጣጠር እና መጠቀም መቻሉን የሚያቅ ስንት የጎሳ ካድሬ አለ?

Re: ከመቶ ሺ ደንቆሮ የዘር ፖለቲከኛ አንጎሎች የላቀ አንድ አስገራሚ ምሁር !!

Posted: 19 Jun 2020, 03:49
by DefendTheTruth
Horus wrote:
19 Jun 2020, 03:02
ይህ ነው የ21ኛ ዘመን አንጎል ። ኢትዮጵያ ዛፍ በመትከል ብቻ ያባይን ዉሃ መቆጣጠር እና መጠቀም መቻሉን የሚያቅ ስንት የጎሳ ካድሬ አለ?

Horus,

Demeku ye Guraghe sem new inde? Just out of curiosity.

Re: ከመቶ ሺ ደንቆሮ የዘር ፖለቲከኛ አንጎሎች የላቀ አንድ አስገራሚ ምሁር !!

Posted: 19 Jun 2020, 03:55
by Horus
እኔ ልጅ ሆኜ ስለ ልዩ ልዩ ግዙፍ የግድብ ፕሮጀክቶች ህንድ፣ ቴኒሲ ቫሊ ሌሎች ስማር እንዚህ ግድቦች ሂደው ሂደው ከባቢን ያወድማሉ የሚል ተምሬ ስላደኩ ለብዙ ግዜ ባባይ ግድብ ላይ የነበረኝ አተያይ ኔጋቲቭ ነበር። እኔ የኢንቫሮንመንት ተርማሪ አይደለሁም ። ዛሬ ይህን ሰውዬ ስሰማ አለም ነው የበራልኝ ።

ልብ በሉ ፣ ጥርቁ አባይ ዝም ብሎ አንድ ቀን የሚጎርፍ የዉሃ መአት አይደለም ። አባይ የምንጮች፣ የጉሬዎች፣ የትናንሽ እና የትላልቅ ወንዞች ጥርቅም ነው ። እንዚህ ደሞ ከየመንደሩ ፣ ከየሰፈሩ ፣ ከየቀበሌው ፣ ከየአገሩ ፣ ከየክልሉ አፈር እየሰረቀ የሚወስድ ዉሃ ነው። ያ ነው አባይ ተሸክሞ ለግብጽ የሚገብር ።

ይህን እንዴት እንደ ምናስቆም ዛሬ አንድ ምሁር አስተማረን ።

ከዛሬ ጀምሮ የኢትዮጵያ አርበኛ ነኝ ባይ ምን ማድረግ እንዳለበት ያቃል ማለት ነው። ዛፍ በመትከል፣ አፈርና ዉሃችንን መቆጣጠር !!! እጅግ እጅግ አስገራሚ ብርሃነ እውቀት !!!

Re: ከመቶ ሺ ደንቆሮ የዘር ፖለቲከኛ አንጎሎች የላቀ አንድ አስገራሚ ምሁር !!

Posted: 22 Jul 2020, 22:16
by Horus
.......................................................................................

Re: ከመቶ ሺ ደንቆሮ የዘር ፖለቲከኛ አንጎሎች የላቀ አንድ አስገራሚ ምሁር !!

Posted: 22 Jul 2020, 22:39
by TGAA
I agree ,Horus. Abiy has his finger on it. By the way, it gives me much comfort to know that you happen to be Yeledata leg;)

Re: ከመቶ ሺ ደንቆሮ የዘር ፖለቲከኛ አንጎሎች የላቀ አንድ አስገራሚ ምሁር !!

Posted: 22 Jul 2020, 23:40
by Horus
TGAA wrote:
22 Jul 2020, 22:39
I agree ,Horus. Abiy has his finger on it. By the way, it gives me much comfort to know that you happen to be Yeledata leg;)
ፕ/ሩ በጣም ወሳኝ ነገር ያነሳል። መሬቱ በሳርና ዛፍ ካልተሸፈነ መያመቱ የሚሸረሸረው አፈር ግድቡ ባጭር ዘመን ስለሚሞላው ይህ ሁሉ ጥረት ብላሽ ነው የሚሆነው ። ይህ ዉሃን በእጸዋት ዉስጥ መገደብ የሚለው ክንሴፕት ፍጹም አስገራሚ ነው ። እኔ ስለነገሩ ማንበብ ጀምሪያለሁ !!

Re: ከመቶ ሺ ደንቆሮ የዘር ፖለቲከኛ አንጎሎች የላቀ አንድ አስገራሚ ምሁር !!

Posted: 23 Jul 2020, 00:20
by TGAA
ይህ አብሮ ፕሮጀግቱ ሲጀመር አብሮ መጀመር የነገረበት ስራ ነው ፤ ወጪውም ብዙ አይሆንም ነበር በአለፉት ዘጠኝና አስር አመት አካባቢውን ሌላው እንኳን ቢቀር ወንዙ የሚያልፍባቸውን ቦታዎች በሳርና በዛፍ ማልበስ ይቻል ነበር፡ እርግጥ እንዳልከው በዚህ መጠን አፈር ይዞ ግድቡ ሲደርስ አፈሩ የሚዘቅት ከሆነ ግድቡ ላይ ችግር ነው የሚያመጣው፤ ሆኖም ውሀው ከአዲስ አበባ እሰክ ሻሸሜኔ በሚደርስ ቦታ ላይ ስለሚሰፍር አፈሩ እየዘቀጠ የጠራው ዉሀ ወደ ግድቡ ይሄዳል የሚል ሀሳብ አለኝ ፤ ሆኖም እንዳልከው ውሀን በዛፍና በሳር መያዝ የሚለው ኮንሲፕት ምሁሩ እስከሚናገረው ድረስ አላሰብኩበትም ነበር ፤ በእርግጥም ልክ ነው፡ እኛ አፈር ከመከላከል አንጻር ብቻ ስለምናሰብ ነው፤ ብዛ ቢል ንጹህ አየር ወዘተ፤

Re: ከመቶ ሺ ደንቆሮ የዘር ፖለቲከኛ አንጎሎች የላቀ አንድ አስገራሚ ምሁር !!

Posted: 23 Jul 2020, 00:46
by Horus
TGAA

ይህም ማለትኮ እነዚህ የእጸዋትና ውሃ ሳይንቲስቶች ሊያውቁ የሚችሉዋችው ነገሮች ብዙ ናቸው። ቲኦሮቲካሊ ስንት ዝናብ እንደ ሚዘንብና መሬት ላይ ማረፍ እንደ ሚችል ያውቃሉ ። እያንዳንዱ እጸዋት እንደ ሳይዙ ስንት ዉሃ በውስጡ ልይዝ እንደ ሚችል ያውቃሉ ። ብሎም አፈሩ ስንቱን ዉሃ እንደ ምይዝና ስንቱ ዉሃ ወደ መጋቢ ወንዞችና ሃይቆች፣ ኩሬዎች እንደ ሚሄዱ ማወቅ ይችላሉ ። እንግዲህ ይህን መሰለኝ ዋተር ማኔጅመንት ሚባለው ።

እኔ ድሮ እንደ የዛሬ 20፣ 15 አመት ኢትዮጵያ ከሚያስፈልጓት የፓርቲ አይነቶች አንዱ አረንጓዴ ፓርቲ መሆን አለበት እል ነበር ። ይህ ነገር አሁን እየመጣ ነው ። ሁሉም ነገር ግዜውን መጠበቅ አለበት ። እኔ ምንም ጥርጥር የለኝም እኛ በህይወት እያለን የኦጋዴንና አፋር በረሃዎች ሰፋፊ ዘመንዝዊ እርሻ እንደ ሚሆኑ !አባይ እንደ ሆነ ያፍሪካ ቀንድና ቀይ ባህር ጂኦፖለቲካን ለዘላለም ይለውጣል ። አስገራሚ ዘመን እየገባን ነው !

Re: ከመቶ ሺ ደንቆሮ የዘር ፖለቲከኛ አንጎሎች የላቀ አንድ አስገራሚ ምሁር !!

Posted: 23 Jul 2020, 01:14
by TGAA
ሆሩስ የሚገርም ዘመን ነው እየገባን ያለነው ; እኔን የሚገርመኝ ደግሞ ፕላን አድርገን ሳይሆን እንደ ሰካራም ተደናብረን ነው እየገባን ያለነው ፤ ነገሮች ሲሰክኑ ኢትዮጵያ ብሩህ ተስፋ ያላት ሀገር ነው የምትሆነው፡ ለማይት ያብቃን ፡፡ ኬር !

Re: ከመቶ ሺ ደንቆሮ የዘር ፖለቲከኛ አንጎሎች የላቀ አንድ አስገራሚ ምሁር !!

Posted: 23 Jul 2020, 01:37
by Horus
ታጅ

አው እንደ ሰካራም በሁሉም አቅጣጫ ስንሽከረከር አንዱ ትክክል ሆነና ነው። ታዲኮ የፕሮባቢሊቲ ህግ የሚሰራው እንደዚህ ነው ፤ ልክ እንደ ቁማር አንድን ነገር ለብዙ ግዜ ደጋግመን ከሞከርነው ሂዶ ሄዶ አንዱ ቤት ይመታል። ያ መሰለኝ የሰካራሙን ስኬት የሚገልጽልን ! ሰላም !!