Page 1 of 1
ኢዘዲን ካሚል የ40 አመት እድሜ ከመድረሱ በፊት 200 ፈጠራዎችን በመፈልሰፍ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ወጣት ቢል ጌት ይሆናል
Posted: 15 Jun 2020, 02:28
by Horus
ይህ ጂኒየስ በ14 አመቱ መፍጠር ጀምሮ በ4 አመት ውስጥ 30 ፈልስፏል፤ በዚህ ስሌት በ40 አመቱ 200 ኢንቬንሽኖች ያልፋል። ባሁን ግዜ 14 ፓተንቶች አሉት ። ይህ ነው የዘመናችን ግዙፍ ቢሊዮኔር !!
https://www.youtube.com/channel/UCwfBND ... mgDujXNqXw
Re: ኢዘዲን ካሚል የ40 አመት እድሜ ከመድረሱ በፊት 200 ፈጠራዎችን በመፈልሰፍ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ወጣት ቢል ጌት ይሆናል
Posted: 15 Jun 2020, 02:45
by Horus
Re: ኢዘዲን ካሚል የ40 አመት እድሜ ከመድረሱ በፊት 200 ፈጠራዎችን በመፈልሰፍ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ወጣት ቢል ጌት ይሆናል
Posted: 15 Jun 2020, 08:35
by Ethoash
እንደ ቢል ጌት ይህ ልጅ እንዲያድግ ከፈለግህ ቢል ጌት ያደገበትን መንገድ መመልከት ነው። በቀላሉ አክሲዬን ካምፓኒ በመጀመሪና ብዙ ሰዎች ቢል ጌት አክሲዬን በመግዛታቸው ነው።
አሁንም ልጅ ኮረሪማን ለማሳደግ ከፈለግን የወልቃይት ሕዝብ የሱ ድርጅት ወስጥ እክሲዬን መግዛት አለበት ። ለምሳሌ መቶ ሺህ ወልቃይት ነዋሪዎች ልጁን በማድነቅም በአክሲዬን ትርፍም ለማግኘት በለው አንድ አንድ ሺህ ብር አክሲዬን ቢገዙ መቶ ሚሊዬን ብር ተስበስበ ማለት ነው። የዚህ ልጅ እወቀት ልክ ቤንዚን እንደማግኘት ነው። የተስራበት።
የጉራጌ ክልል ባለስልጣኖች ደግሞ መሬት በነፃ ፤ ታክስ እፎይታ ለ፳ አመት ቢሉ ምድረ አዳሜ ይህ ልጅ ላይ ኢንቨስት ያረጉ ነበር። በዚህ ልጅ ስበብ መድረ የጉራጌ ብሐረተስብ ሀብታም ይሆን ነበር። ለኔ ያስደስተኝ የኤሌትሪክ በጃጅ ነው። ምንም አያስፈልግም ያሉትን የነዳጅ በጃጆች ወድ ኤሌትሪክ መቀየር ብቻ ትልቅ እምርታ ያመጣ ነበር ። በጉራጌ ክፍለሐገር ሳይወስን በሚሊዬን የሚቆጠሩ በጃጆችን መቀየር ይችል ነበር የተስተካከለ ፋብሪካ ቢኖረው።
ይህ አክሲዬን ካልተቻለ ደግሞ አንድ በለሀብት ጋራ መስራት ይችላል። ልክ አንድ ሚዚቀኛ ገንዘብ ሳይኖረው የሙዚቃ አሳታሚ ጋ ሄዶ በሙሉ ዝቅጅቱ ተደርጎለት ሙዚቃው ታትሞለት እንደሚወጣለት ያለምንም ውጪ ከሙዝቀኛው በኩል ችሎታው ብቻ በመሽጥ ገንዘብ ይስራሉ ብዙ ሙዝቀኞች ታድያ በፈጠራም ክእነት እንዲህ ያለ የንግደ ፕላን ተይዞ የፈጠራ ስዎችን ፈጠራ ገበያ የማደረሱ ጉዳይ መታስብ አለብት። እንዳልኩት መንግስት ይህንን እንዱስትሪ ለማሳደግ ታክስ እፎይታ መስጠት አለበት መሬትም በነፃ ብድርም ማመቻቸት አለበት
ለሙዚቃ አሳታሚዎች የታክስ እፎይታ አይስጥም ለሚሉ የፈጠራ ችሎታና ሙዚቃ የተለያዩ ነው። ለምሳሌ አንድ ሰው ሙዚቃ ሲገዛ ገንዘቡን አወጣ ማለት ነው ።። ግን አንድ ሰው የፈጠራ ውጤት ሲገዛ አንድ ጎን ላይ ስራ ፈጠረ ገንዘቡንም ቆጠበ ማለት ነው በርካሽ ስለሚገዛ ከውጭ መምጣቱ ስለሚቀር ።።ሽማቹ ገንዘቡን ያተርፋል የፈጠራ ውጤት በመግዛት ስለዚህ የፈጠራ ወጤቶችን መደገፍ አለብን።
Re: ኢዘዲን ካሚል የ40 አመት እድሜ ከመድረሱ በፊት 200 ፈጠራዎችን በመፈልሰፍ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ወጣት ቢል ጌት ይሆናል
Posted: 15 Jun 2020, 10:31
by Horus
ኢቶአሽ
ያልከው ሁሉ ትክክል ነው ። ብዙዎቹም እየተደርጉ ነው ። ልጁ ትንሽ አሁን ላለው የህዝብ ማሰብና የኢኮኖሚ እውቀት አልፎ ስለሄደ ያልካቸው ነገሮች ለምሳሌ ኢንዱስትሪአል ኦርጋኢዛቲኦን፣ ማሥ ፕሮዳክሽን፣ ማርከቲንግ ወዘተ ትንሽ ግዜ ይወዳሉ ፣ ግ ን ያልካቸው ነገሮች መሆናቸው የማይቀር ነው ። ክልሉ ባሁን ሰአት መሬት ሰጥቶት የራሱ ላቦራቶሪ ገንብቷል። የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲና ፖሊቴክ ኢንስቲቲኡት ፓርትነር ሆነው እየረዱ ነው ' ፕሮቶ ታይፕና ዲዛይን የሚረዱት እነሱ ናቸው።