Former US Ambassador Herman Cohen Said Sebhat Nega is a Big Liar! HAHAHAHAHAHAHA
Posted: 12 Jun 2020, 01:01
Herman Cohen served as United States Assistant Secretary of State for African Affairs.
Zmeselo wrote: ↑11 Jun 2020, 18:18የሔርማን ኮሄን አማራጭ የኢሳያስ አፈወርቂ አቋም እና የስብሃት ነጋ ትርክት (ግንቦት 1983)
በ1985 መገባደጃ አካባቢ የቢቢሲ ጣቢያ “ውስብስብ ድርድሮች” ብሎ ካቀረባቸው ቃለምልልሶች አንዱ ከአሜሪካው ከፍተኛ አደራዳሪ ከሔርማን ኮሄን ጋር ያደረገው ይገኝበታል፡፡ ኮሄን ስለ ግንቦት 1983ቱ የለንደኑ ድርድር ከሰጡት ትንታኔዎች መካከል አንዱን አልረሳውም፡፡
እንዲህ ነበር ያሉት
ኢሳያስን ‘አሁን ጦርነቱ አልቋል፤ እናንተም ተባብራችሁ ከሳሃራ በታች የአፍሪካ አምባገነኑን መንግስት ማስወገድ ችላችኋል፤ አሁን ኤርትራም ስጋት የለባትም፡፡ ስለዚህ አንተ የምትመራው የኢትዮጵያ ጥምር መንግስት ብታቋቁሙ እና ሪፈረንደሙን ለአንድ አምስት አመት ብታዘገዩትስ? ከዛ ደግሞ አይታችሁት እንደሁኔታው ብትሄዱበት’
ብዬ ጠየኩት፤ እሱም የሰጠኝ መልስ ቁርጥ ያለ ነበር፤
እኔ የተዋጋሁት ኤርትራን ነጻ ለማውጣት እንጂ የኢትዮጵያ መሪ ለመሆን አይደለም፤ ያን ካደረኩ የ30 አመታቱን ትግላችንን በዜሮ ያባዛዋል፤ ይቅርታ ሚ/ር ኮሄን፤’ ነበር ያለኝ፡፡
አስገራሚው ቃለምልልስ ሆኖ ነበር ያገኘሁት፤
ሰሞኑን አቶ ስብሃት ነጋ
ኢሳያስ የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ካደረጋችሁኝ የኤርትራን መገንጠል አስቀረዋለሁ፤
አሉና አስገረሙኝ፡፡
በኔ አስተያየት ኤርትራውያን ለ30 ኣመታት ተዋግተው ያገኙትን ነጻነት ራስን ከማስተዳደር ውጪ የሚክሳቸው ነገር የነበረ አይመስለኝም፤
የኢሳያስ አፈወርቂ አቋም ወጥ ነው፤ በኔ በኩል ከስብሃት ነጋ ይልቅ ሔርማን ኮሄንን ማመን ይቀለኛል፡፡ ምክንያቱም ያለምንም የፖለቲካ ስሌት የሰጡት ምስክርነት ነው፡፡ ከአብይ መንግስት መፈጠር በኋላ ግን አቶ ስብሃትንና የትግል ጓዶቻቸውን አስተያየቶችን በተለይም ፕሬዚዳንት ኢሳያስን አስመልክቶ የሚሰጧቸውን አስተያየቶች ማመን ከባድ እየሆነብን ነው፡፡
(Courtesy of Ohad Benami - ኦሃድ ቤንዓሚ)
