· የወደቁበት ዘመን እንዳውም ቆይቷል ባይ ነኝ። ለዚህ ደግሞ ጠንቋይ መቀለብ አያስፈልግም፤ በዚያ አካሄዳቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊወድቁ እንደሚችሉ ግልፅ ነበር። በዚያ ጊዜ እኔ የማወራው የነበረው ስለቅንጦታቸውና ስለሙስና ህይወታቸው ነበር።
· አሳፋሪ ውድቀት የምትወድቁበት ጊዜ ይመጣል በማለት የመጨረሻ ንግግር አድርጌ ነው የወጣሁት።
· ወያኔዎች ከአለም በተገለለና በጣም ጠባብ የሆነ የእውቀት ክምችት በነበረበት በርሃ ውስጥ እንደመቀመጣቸው ከእነሱ ውጪ ያለውን አለም ማየት እንዲሳናቸው አድርጎ ነበር።
· አለም በብዙ መንገድ ፈትሾ ችግር አለበት ያለውን የማርክሲስት ፍልስፍና ከቻይና እና ከራሺያ ተሰብስቦ አገር ውስጥ የገባ ፍልስፍና ሲያነቡ ነው የከረሙት።
· በእነሱና በእኔ መካከል ከፍተኛ የሆነ ልዩነት ነው ያለው። እነሱ ነፃ አውጪዎች ናቸው። «ነፃነትን የማያውቅ ነፃ አውጪ» ብዬ ለመፃፍ የተገደድኩበት አንዱ ምክንያት ይህ ነው።
· እነሱ የቆሙበት የማርክሲዝም መሰረት ምን ያህል ደካማ እንደነበር አውቀው ነበር። በዚህ ምክንያት ስንነጋገር ልንግባባ የማንችልበት ሁኔታ ውስጥ ነው የገባነው።
· ከሚገባው በላይ ትእቢትና ትምክህት ይዘው ስለመጡ እንዲሁም ከማሸነፍና ከድንቁርና ጋር ተደምሮ ሰው የሚላቸውን ወደማይሰሙበት ሁኔታ ውስጥ ነው የገቡት።
· በአንድ ጊዜ ስልጣን ወደመያዝ በመጡ ቁጥር በደንብ ያላሰቡበት ከህዝብ ጋር የተቆራኘ ነገር እየላላ መጣ። እንደማንኛውም ነፃ አውጪ ህዝብ መልሶ ረጋጭ በህዝብ ሃብት የቅንጦት ኑሮ ነዋሪነት ተሸጋገሩ። እንዳውም ከመጀመሪያውም ይህንን እያለሙ የመጡ ነው የሚመስለኝ።
· ለአሜሪካን ድምፅ በኢትዮጵያ ታሪክ በሙስና እስከዛሬ ድረስ ከመጡት መንግስታት ሁሉ በከፋ መልኩ የሚታይ መንግስት ይሆናል ብዬ ነበር የተናገርኩት በዚያን ወቅት።
· በሰራዊት ደረጃ ለረጅም ዘመናት በራሳቸው መንገድ ጠፍጥፈው የሰሩት ሰራዊት በመኖሩ የተነሳ ደርግ በአንድ ቀን ምሽት 1ሺ 500 ሰዎች ቢገድል እነሱ 200ሺ ሰዎችን በአንድ ቀን ሌሊት ገድለው ሊያድሩ ይችላሉ ብዬ ነበር የገለፅኩት። ትዕዛዛቸውን ያለምንም ማንገራገር ሊፈፅም የሚችል ሰራዊት መኖሩም በድፍረት ተናግሬአለሁ።
· ወያኔዎች ስንት አበሳቸውን አይተው መጥተው ሁለት ወር ሳይመላቸው ያንን ሁሉ ችግር አብሯቸው ያለፈውን ህዝብ ረስተው በውድ ዋጋ በዲዛይነር የተሰራ ሱፍ ለብሰው የ300ዶላር ጫማ አድርገው የደርግ ላንድሮበሮችን ወደ መከፋፈል ነው የገቡት።
· አሁን የእኔ ነው እያሉ የሚጮሁለትን የትግራይ ህዝብ ስድስት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ረስተው መኖር ለመጀመር ጊዜ አልወሰደባቸውም። ለምን የሚባል ጥያቄ እንኳ መጠየቅ አልፈለጉም።
· ከዚያ ሲለፍፉለት የነበረው ደሃ ህዝብ ጋር የሚያስተሳስራቸው ነገር አልነበረም። እነሱ ራሳቸው የተዋረዱበት፣ እነሱ ራሳቸው የተራቡበት ፣ እነሱ ራሳቸው መብት አጥተው የኖሩበት አድርገው አላዩትም።
· እነሱ እዚህ መጥተው ከማንም በባሰ መብት ገፋፊና ዘራፊ ነው የሆኑት። አሁንም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ድርጅት ውስጥ በዚህ ደረጃ ብስለት ያላቸው ፖለቲካ ሃይሎች የሉም።
· እኔና መለስ በተመሳሳይ አመት ነው ዩኒቨርሲቲ የገባነው፤ ኢህአፓን በከፍተኛ ደረጃ ይመሩ የነበሩት የትግራይ ተወላጆች ነበሩ። በዚህ ምክንያት መለስ ኢህአፓ ውስጥ ሊገባ የሚችልበት እድል ነበር።
· ይሁንና የብሄርተኝነት እንቅስቃሴ ከጀመሩ ሰዎች ጋር ቅርበት ስለነበረው ህውሓትን ተቀላቀለ። ይህም ቢሆን ግን እሱም ልክ እንደእኛ ይሄኛው ከዚህኛው ይሻሻል ብሎ መዝኖ የገባበት ሁኔታ እንዳልነበረው አውቃለሁ።
ለሙሉ ቃለ ምልልሱ: https://www.press.et/Ama/?p=33372&fbcli ... LjP8DS75zY
Re: «እንደ ኢህአዴግ ዴሞክራሲን በዚህ ደረጃ የስለላ መሳሪያ ያደረገ መንግስት የለም» – አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ
Endargatchw Tsige is a lost man and out of dated. The TPLF has been merciful with him a couple of yomes, but he still continues until today to blackmail TPLF and serve the interest of his master Isaias Afeworki.If he was true to his words by now he should have denounced what Isais has been doing to the people of Eritirea. TPLF is here to stay and down the line it shall establish the Axumite Federal States.
-
Tog Wajale
- Member
- Posts: 4919
- Joined: 23 Dec 2017, 07:23