ያአኩል ለል ኸዛብ
ወያኔ ባወጣችው አዲሱ መግለጫ ላይ የዲጂታል ወያኔ አባላትን " ግንባር ቀደም ደጀናችን ናችሁ " ሲል አሞካሽቷል።
እንደሚታወቀው ወያኔ የዲጂታል ወያኔ አባላትን በየደረጃው በወር ከ5,000 ብር እስከ 15,000 ብር ትከፍላቸዋለች ። ከነዚህ ተከፋይ ፀሓፊዎች መካከል አብዛኞቹ አባላት የግንቦት 20 በዓልን እያሞካሹ ሲፅፉ የተጠቀሟቸው ምስሎች በሙሉ ከሻዕቢያ የተሰረቁ ነበሩ ። ከታች ያለውን ምስል የተጠቀሙ አባላትም ነበሩ ። እነዚህ የዲጂታል አባላት በቀጣይ እንደማናያቸውና ከአባልነት እንደሚቀነሱ እርግጠኛ ሆኜ መናገር እችላለሁ ! አስፎጋሪዎች ናቸዋ !!
ይህ ምስል የሻዕቢያ ሲሆን የዓለም የመገናኛ ብዙሃን የተቀባባሉት ምስል ነው ። ያም ሆነ ይህ ዲጂታልንና ቀጣሪያቸውን ወይም ተከፋዮቹን እና ከፋዩን ሳስብ አንድ የአረቦች ተረት ትዝ አለኝ ።
ማል አል ሃራሚ ..
ያአኩል ለል ኸዛብ
"የሌባን ብር ውሸታም ይበላዋል" ማለት ነው ።

