Page 1 of 1

ቡሩንዲ ውስጥ መራጮች አዲስ ፕሬዝደንት ለመምረጥ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች እየጎረፉ ነው።(BBC)

Posted: 20 May 2020, 11:03
by EthioRedSea
ቡሩንዲ ውስጥ መራጮች አዲስ ፕሬዝደንት ለመምረጥ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች እየጎረፉ ነው። ገዥው ፕሬዝደንት ፒዬር ንኩሩንዚዛ ከ15 ዓመታት ሥልጣን በኋላ መንበራቸውን ይለቃሉ። ነገር ግን ከሥልጣን በኋላ የሚኖራቸው ጊዜ በመንግሥት ቤት ነው የሚኖሩት፣ የዕድሜ ዘመን ደሞዝ ይኖራቸዋል፤ ኦፌሴላዊ ሥልጣን እንደሚሰጣቸው ይጠበቃል። ሰባት ዕጩዎች የንኩሩንዚዛዘን መንበር የራሳቸው አድርገው የቡሩንዲ ፕሬዝደንት ለመሆን ይፋለማሉ። በተሻሻለው ሕገ-መንግሥት መሠረት አዲሱ ፕሬዝደንት ለሰባት ዓመታት ያገለግላል፤ ሥልጣን ማራዘም የሚችለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው።
https://bbc.in/3e47hcB