ሙክት ሲሰባ ሾተል ይልሳል
Posted: 10 May 2020, 21:06
የዶክተር አብይ አህመድን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ያለው መቀራረብ እያደገ መምጣቱ እሙን ነው ። በቅርቡም በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ከግብፅ ጋር በነበረው የሃሳብ ልዩነት ጅቡቲና ሶማሊያን ጨምሮ ብዙ ሀገሮች የግብፅን አቋም ሲደግፉ ኤርትራ የኢትዮጵያ አጋርነቷን አሳይታለች። በተለያዩ የአዉሮጳ ሀገራት የሚኖሩ ኤርትራውያንም በተለያዩ መንገዶች ለኢትዮጵያ ያላቸውን አጋርነትና ፍቅር ገልጸዋል። ክቡር ፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በዚሁ ጉዳይ አቋማቸውን ግልጽ ከማድረጋቸው በተጨማሪ በተለያዩ ጊዜያት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት አጋርነታቸውንና ፍቅራቸውን ገልጸውልናል።
ይህ ከጅምሩ ያላስደሰታቸው ህወሃቶች አንድ ጊዜ ኤርትራ በሀገራችን ጉዳይ ጣልቃ እየገባች ነው ሌላ ጊዜ መደራደር ያለባት ከኛ ጋር ነው ሌላ ጊዜ በዲያስፖራ ለመደራደር ሙከራ ሌላ ጊዜ ሌላ በማለት መልካም ግንኙነታችንን ለማበላሸት ከላይ ታች ሲሉ ከራርመዋል።
የ 2012 ሀገራዊ ምርጫ በ COVID 19 ምክንያት ማካሄድ አለመቻሉን የምርጫ ቦርድ ማስታወቁን ተከትሎ ህወሃት የቀሰቀሰችውን ዉዥንብር ለማጋጋል የበፊት ተቃዋሚ መሳይ የዉስጥ አርበኞቿን ( እነ አቶ ልደቱ አያሌው ) በማሰባሰብ በመፍጨርጨር ላይ ትገኛለች።
ሰሞኑን አቶ ልደቱ አያሌው በድምፅ ወያኔ ጣቢያ ላይ ዶክተር አብይንና ፕረዚዳንት ኢሳያስን ከላይ ታች እያደረገ በማጠልሸት ስራ ተጠምዶ ይገኛል። ይህንም የሚያደርገው እዉነት የፖለቲካ አለማ ኖሮት አይደለም ይልቁንስ ከ ህወሃት ጋር በገንዘብ ተደራድሮ እንጂ። በጣም የሚገርመው የአንድን አገር መሪ ከሌላ አገር የፖለቲካ አክቲቪስት፣ የክልል አስተዳዳሪ ጋር እያወዳደረ ወሬ ለማሳመር መሞከሩ ነዉ ። እዚህ ላይ ለኢትዮጵያ ከ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ይልቅ ፕረዚዳንት ኢሳያስ እጅጉን የተሻሉ ሰው መሆናቸውን የተከበሩ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም የገለፁትን ማስታወስ እፈልጋለሁ።
አቶ ልደቱ አያሌው የ ህወሃት የ ዉስጥ አርበኛ በመሆንና መረጃ በማቀበል አንዳንዴም የዉሸት እስር ታሰረ ተፈታ እየተባለ የራሱን ንግዱ በተሳለጠ መንገድ ሲያስኼድ ነበር። አሁን ወደ ሃብታሞች ተርታም እየተጠጋ ይገኛል። ሌሎች ተቃዋሚ የፖለቲካ አመራሮች ግን ለእስር አልፎም ለግርፋትና እንግልት ተዳርገዋል።
አሁን አቶ ልደቱ ደረጃውን አሳድጎ ፉክክሩን ከአገር መሪዎች ጋር አድርጓል መጨረሻውን እናያለን።