Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Fiyameta
Senior Member
Posts: 19943
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

የቀን ጅቦችን ያስቆጣው የጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ ንግግር

Post by Fiyameta » 10 May 2020, 04:02



“ዲጂታል ወያኔ ሰውን መስደብ መብት ይመስለዋል። ለምሳሌ ፕሬዚዳንት ኢሳያስን እየሰደበ ኤርትራን የሚቃወም የሚመስለው ብዙ ዲጂታል ወያኔ አለ። ይሄ ስህተት ነው። ሄይት ስፒች (Hate Speech) መብት አይደለም።”

“ስልጡን ለመሆን ፈይስቡክ መጠቀም ብቻ ሳይሆን፣ አጠቃቀሙንም ማወቅ ያስፈልጋል። አዋቂ መሆን ፈይስቡክ አካውንት መክፈት ብቻ ሳይሆን፣ ምን እንደምንጽፍ እና እንደማንጽፍ ካላወቅን፣ በቴክኖሎጂ አጥር ውስጥ የምንኖር መሃይሞች እንጂ አዋቂዎች መሆን አንችልም።”

“ቀኑን ሙሉ የውጊያ ፊልም እያየ የሚውል ሰው፡ ማታ የሚያልመው ውጊያ ነው። ይሄ ሳይንስ ነው። ቀኑን ሙሉ ጋርቤጅ ወሬ እየሰማና እያነበበ የሚውል ሰው፡ ጋርቤጅ ነው የሚያልመው። ሰው መሆን አያልምም።”

“በየድህረ ገፁ የሚጮኸው ሁሉ እኮ አይዋጋም። ባድሜ ከማንም በላይ የሞተው ኦሮሞ ነው።”



ኢኮኖሚክ ኢንቴግሬሽን

“በአፍሪቃ የቀኝ ገዢዎች ያቋቋሙት አርቲፊሺያል ድንበር እንጂ አፍሪቃውያን ያቋቋሙት ድንበር የለም። ይህን አርቲፊሺያል ድንበር ህዝብን ከህዝብ ከፍሏል። ለምሳሌ ትግራይና ኤርትራ ውስጥ ኩናማን ከፍሏል። ኢትዮጵያ ያለው የቦረና ኦሮሞና ኬንያ ያለው ኦሮሞ ከፍሏል። አንድ ህዝብ ሆኖ እያለ ሁለት ፓስፖርት አለው። ነገር ግን በአንድ አባ ገዳ ይተዳደራሉ። ቋንቋው፡ ባህሉ፡ አለባበሱ ሁሉ አንድ ነው። ቤተሰብ ነው። ጅቡቲ ያለው አፋር፡ ኢትዮጵያ ያለው አፋር፡ ኤርትራ ያለው አፋርም እንዲሁ አንድ ህዝብ ነው። ነገር ግን ሶስት አገር ይኖራል። ጅቡቲ ያለው ሱማሌ፡ ሶማልያ ያለው ሱማሌ፡ ኢትዮጵያ ያለው ሱማሌም አንድ ህዝብ ነው። ግን ሶስት አገሮች ይኖራል።”

“ለዚህ ነው ድንበሩ አርቲፊሺያል ነው የምለው። ህዝብ ከፍሏል። ይህንን አርቲፊሺያል ድንበር የአፍሪቃ ሃገሮችን ወደ ኢኮኖሚክ ኢንቴግሬሽን ለማምጣት አልጠቀመም። የምስራቅ አፍሪቃ አገሮች ደግሞ በመለያየት እነሱ ይብሳሉ። ይህንን ችግር ከመሰረቱ እንዴት እንፍታ የሚል ውይይት ነው የሚያስፈልገው። አርቲፊሺያል ድንበሩን ያስከተለው የመለያየት አስተሳሰብ እንዴት አስወግደን፡ እንዴት ኢትዮጵያና ኬንያ አንድ ይሁኑ፣ እንዴት ሶማልያና ጅቡቲ አንድ ይሁኑ፣ እንዴት ሱዳንና ኢትዮጵያ አንድ ይሁኑ፣ እንዴት ኤርትራና ኢትዮጵያ አንድ ይሁኑ፡ ወዘተ፡ ብለን በማሰብ የተሟላ ኢንቴግሬሽን ማምጣት አለብን።”

“Our sub-region, the Horn of Africa, after decades of externally induced inter and intra-state conflicts, has begun to breathe air of hope and togetherness. Peace and stability, critical prerequisite of regional integration, is a new opportunity that we can leverage on for regional integration.” -- (Eritrea’s Foreign Minister, Mr. Osman Saleh, 2019)

“ [ከየትግራይ ፓርላማ አባል] ጠብቄ የነበረው ጥያቄ፡ "የአልጄርስ ስምምነት እንድትፈራረሙ እና፡ ፊርማውን ከተፈራረማችሁበት ቀት ጀምሮ ስምምነቱ የፀና መሆኑን በአዋጅ ህግ አውጥቼ ሳበቃ፡ ለምን አልተፈጸመም?”

“ህዝቡ የሚጠይቀው ያለው ይህንኑ ነው። በተለይ በትግራይ ባደረግነው ሰፋፊ ውይይቶች፡ ህዝቡ የድንበሩ ጉዳይ ፍቱልን፡ ሚሊሽያ ሆነን ሃያ አመት ካለክፍያ ድንበር ጠብቀናል፡ እኛም እንደሌላው መልማት እንፈልጋለን፡ እንደሌላው መለወጥ እንፈልጋለን፡ የሚሉ ጥያቄዎች አንስተውልኛል። መቀሌ በነበረው ውይይት፡ ይሄ ጉዳይ ስላልለየለት፡ አንድ ጀኔረሽን (generation)፡ አንድ ሰው ተወልዶ እሚያገባበት እድሜ ያክል፡ ያለምንም ደሞዝ፡ ያለምንም ክፍያ፡ ድንበር ጠባቂ ነን። ይብቃን፡ ፍቱልን፡ ብለዋል።”

“በትግራይ በየቦታው በነበረው ውይይትም ጥያቄው ተነስቷል። የድበቃ ፖለቲካ ከንግዲህ በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ አይሰራም። ድበቃ አይጠቅምም። ሃያ አመት ሙሉ በብዙ ሺ የሚቆጠር ወታደር ለውጊያ ድንበር አከባቢ አሰልፈናል። ሚግ 29፡ ታንክ፡ መድፍ፡ ያልተገዛ መሳርያ የለም፣ በብድርም፡ በልመናም፡ በሃገር ሃብት። የተገዛው ትራክተር ቢሆንና ምእራብ ትግራይ በለማበት በጣም ጥሩ ነበር። ብዙ ሃብት ነው እየጠፋ ያለው። ማንም አይጠቀምም ከዚህ። ኤርትራ አይጠቀም፡ ኢትዮጵያ አይጠቀምም። ጥቅም በሌለው ምክንያት የህዝብን ሃብት እያወደምን መቀጠል እንደ ጥሩ ነገር መታየት የለበትም። ሰላም ለማግኘት የምንከፍለው ዋጋ ለጦርነት ከምንከፍለው ዋጋ ጋር ሲነፃፀር ሰማይና ምድር ነው። እኛ የድንበር ውሳኔውን ለመተግበር መዘጋጀታችን የናንተን የዘገየው ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግና ማስፈጸማችን ብቻ ነው። ከኤርትራ ጋር ወደ የተሟላ ኢኮኖሚክ ኢንቴግሬሽን መሄድ አለብን።”




Fiyameta
Senior Member
Posts: 19943
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: የቀን ጅቦችን ያስቆጣው የጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ ንግግር

Post by Fiyameta » 10 May 2020, 06:09

To a person with an average IQ a mere gesture suffices. :oops:



Post Reply