Page 1 of 1

የጉራጌ የጀግና ለቅሶና የጢያ ሜዳ !!

Posted: 09 May 2020, 02:29
by Horus

ይህን ለማታቁ፣ አንድ ታዋቂ፣ ተወዳጅ፣ ጀግና ፣ መሪ ሲሞት የሚደረግለት የልቅሶ ሽኝት እጅግ ግዙፍ ነው። ፈረሶች ወጥተው ጃኖ ይለብሳሉ ! የሃዘን ምልክት ነው። ሰው በፈርስ ላይ አይቀመጥም ። ልክ ሴቶች ነጠላ ገልብጠው እንድ ሚያለቅሱ ሁሉ ፈረሰ ያለው ወንድ ፈረሱን ጃኖ አልብሶ በእግሩ እየጎተተ ትልቁ ገናናው ዪዎፈን ይጀመራል !!

ዎፈን ወጣት ሃያል በሬ ነው ። ዎፈን የጀግና ተምሳሌት መታፎር ነው ። ከዚያም በረጅሙ ሜዳ ዳርና ዳር ድረስ እየተመላለሱ አለም ገፈረም፣ አለም ገፈረም በዋሻ እየተባለ ዬዎፈን ኦፈንታ ተብሎ ከንጋት እስከ ቀጥር ተለቅሶ (ተዘፍኖ) ይቀበር ነበር ጀግና !! በጉራጌ ሴትም ወንድም አልቃሾች ሁለት እጆቻቸውን ወደ ሰማይ አንስተው ነው የሚያቦሱት ። አቦሰ ማለት አነሳ ማለት ነው ። በግዕዝ ታበጽህ ይባላል። ታቦስህ ማለት ነው። በጉራጌ አቦሰ ማለት ሰው እጆቹን ወደ ሰማይ ዘረጋ፣ አነሳ ማለት ነው። ኢትዮጵያ እጆችሂ ትዝጌርይነን ታቦሲ ፤ ኢትዮጵያ ታበጽህ እደዊሃ አበ አግዚአብሄር እንላለን ። ከታች ቪዶዮ አሳያለሁ ።

ይህን ሁሉ ያነሳሁት፣ ልብ በሉ እነዚህ የጢያ የመቃብር ሃውልቶች የሚተከልላቸው ጀግኖች ሲቀበሩ የነበረው ዪዎፈንና ለቅሶ የፈረስ ጋጋታ፤ ያ ነው አንድ ቀን ተመልሶ መቀረጽ ያለበት ። ይህን የምታዩት ሜዳ ያ ነበር የሚካሄድበት የዛሬ 1000 እና 900 አመት



Re: የጉራጌ የጀግና ለቅሶና የጢያ ሜዳ !!

Posted: 09 May 2020, 02:53
by Horus
ይህ አንድ ትንሽ የድሃ ለቅሶ ነው ። ፈረሰም የለም ። ግን የሴቶቹ የእጅ ዋቡስ ታያላችሁ ። ይህ በጥንታዊ ግብጽ ካሃ ይባል የእበረው የጸሎትም የሃዘንም ባህል ነው።