Page 1 of 1
ስልጣንን ያለ ምርጫና ከህግ ውጪ በሁከትና በብጥብጥ ካልሰጣችሁን ሀገር አተራምሳለሁ የሚለውን ማንኛውንም ሀይል አንታገስም – ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ
Posted: 07 May 2020, 03:12
by MINILIK SALSAWI
Re: NEW- የኮቪድ ወረርሽኝ እስኪወገድና ቀጣዩ ምርጫ እስከሚካሔድ የብልጽግና ፓርቲ ሐገር የማስተዳደር ኃላፊነት አለበት።- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሰጡት መ
Posted: 07 May 2020, 03:26
by Horus
ሚኒሊክ
ያቢይ ስህተት ምን እንደ ሆነ ልንገርህ ። ያቢይ ችግር ወያኔ፣ ጃዋር፣ ልደቱ ፣ አራርሶ አይደሉም። ያቢይ ችግር ራሱ አቢይ ነው ። ከመስክረም በኋላ እስከ ተፈለገ ድረስ ምርጫ ማራዘም ይቻላል ። እነሱ የጻፉት ሕገ መንግስት ተቢዬ ራሳቸው ሊለውጡት ይችላሉ ፣ ግን እህ እንዲሆን አቢይ ለ1፣ 2፣ ወይ 3 አመት ከሌሎች ፓርቲዎች ወይ ሊሂቃን ጋር ስልጣን መጋራት መሻማት አለበት ። ይህ ግድ ነው ። ይህን እምቢ እያለ ማንም አያምነውም ። አቢይኮ እግዚአብሄር አይደለምን ። ራሱ ስልጣን የሚወድ የፖለቲካ እንሰሳ ነው በቃ !!! ዝሆኑን በስሙ ጥሩት፣ ያኔ ሁሉ ነገር ግልጽ ይሆናል !! አሚን !!!!
Re: NEW- የኮቪድ ወረርሽኝ እስኪወገድና ቀጣዩ ምርጫ እስከሚካሔድ የብልጽግና ፓርቲ ሐገር የማስተዳደር ኃላፊነት አለበት።- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሰጡት መ
Posted: 07 May 2020, 04:59
by MINILIK SALSAWI
Horus wrote: ↑07 May 2020, 03:26
ሚኒሊክ
ያቢይ ስህተት ምን እንደ ሆነ ልንገርህ ። ያቢይ ችግር ወያኔ፣ ጃዋር፣ ልደቱ ፣ አራርሶ አይደሉም። ያቢይ ችግር ራሱ አቢይ ነው ። ከመስክረም በኋላ እስከ ተፈለገ ድረስ ምርጫ ማራዘም ይቻላል ። እነሱ የጻፉት ሕገ መንግስት ተቢዬ ራሳቸው ሊለውጡት ይችላሉ ፣ ግን እህ እንዲሆን አቢይ ለ1፣ 2፣ ወይ 3 አመት ከሌሎች ፓርቲዎች ወይ ሊሂቃን ጋር ስልጣን መጋራት መሻማት አለበት ። ይህ ግድ ነው ። ይህን እምቢ እያለ ማንም አያምነውም ። አቢይኮ እግዚአብሄር አይደለምን ። ራሱ ስልጣን የሚወድ የፖለቲካ እንሰሳ ነው በቃ !!! ዝሆኑን በስሙ ጥሩት፣ ያኔ ሁሉ ነገር ግልጽ ይሆናል !! አሚን !!!!
ይህ በኢሕአዴግ/ብልጽግና ሰፈር እኮ የማይታሰብ ነው። ሕጉን በፈለጉት ስታይል አሽከርክረው ወደፊት ይመጣሉ እንጂ ሕገመንግስትም ይተርጎም ያሉትን በፈለጉት ስታይል ተርጉመው ያመጡታል እንጂ በፍጹም ስልጣን ከኢሕአዴግ/ብልጽግና ሰፈር እንዲወጣ አይፈለግም። ምናልባት ሰሞኑን በመግለጫቸው የሕገመንግስት ትርጓሜውን የደገፉ ፓርቲዎችን ሊያስጠጋቸው ይችላል። ካሁን ቀደምም ሕገመንግስቱን በመመሪያና በቀላጤ ሲሽሩ ነበር ለነሱ አዲስ ነገር አይደለም።
Re: NEW- የኮቪድ ወረርሽኝ እስኪወገድና ቀጣዩ ምርጫ እስከሚካሔድ የብልጽግና ፓርቲ ሐገር የማስተዳደር ኃላፊነት አለበት።- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሰጡት መ
Posted: 07 May 2020, 06:02
by MINILIK SALSAWI
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከህጋዊ መንገድ ውጪ ስልጣን ለመያዝ የሚንቀሳቀሱ ናቸው ያሏቸውን የፖለቲካ ፓርቲዎችና ፖለቲከኞች አስጠነቀቁ፡፡መንግስታቸው በህገ መንግስቱና በህገ መንግስታዊ ሥርዓቱ ካልሆነ በስተቀር የጨረባ ምርጫ ለማድረግ በሚነሱት ላይ ወሳኝ እርምጃ ለመውሰድ ይገደዳል ብለዋል፡፡ ለዚህም መንግስታቸው ዝግጁ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ስልጣንን ያለ ምርጫና ከህግ ውጪ በሁከትና በብጥብጥ ካልሰጣችሁን ሀገር አተራምሳለሁ የሚለውን ማንኛውንም ሀይል አንታገስም ብለዋል፡፡
Re: ስልጣንን ያለ ምርጫና ከህግ ውጪ በሁከትና በብጥብጥ ካልሰጣችሁን ሀገር አተራምሳለሁ የሚለውን ማንኛውንም ሀይል አንታገስም – ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ
Posted: 07 May 2020, 08:19
by MINILIK SALSAWI
ምርጫው እስኪካሄድ ድረስ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት መቆየትና የሽግግር ሂደቱን መምራት የተሻለ ነው ብለን እናምናለን – አብን
Read Full press statement -
https://mereja.com/amharic/v2/266952