Chigaram breeder Ethiopia: ኢትዮጵያ ነዳጅ በዱቤ እያስገባች መሆኑ ተሰምቷል
Posted: 06 May 2020, 16:28
ትዮጵያ ከኩዌት እና ከተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ነዳጅ በዱቤ በማስገባት ላይ መሆኗን የነዳጅ አቅራቢዎች ድርጅት አስታወቀ።
የኢትዮጲያ ነዳጅ አቅራቢዎች ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታደሰ ሃ/ማሪያም ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ኢትዮጵያ ከኩዌት እና የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ነዳጅ እያስገባች ነው።
የዓለምን ኢኮኖሚ ክፉኛ እያደቀቀ ያለው የከሮና ቫይረስ መስፋፋቱን ተከትሎ የወጪ ንግዱ እየተቀዛቀዘባት ያለችውን ኢትዮጵያንም እያዳከማት ይገኛል።
የነዳጅ አቅርቦቷን ለመሸፈንስ የውጪ ምንዛሬ እጥረት አላጋጠማትም ወይ በሚል ላነሳነው ጥያቄም አቶ ታደሰ ነዳጅ በዱቤ እያስገባን ስለሆነ የውጭ ምንዛሬ በነዳጅ አቅርቦቱ ላይ ስጋት አይኖረውም ብለውናል።
ነዳጅ በዱቤ ማስገባት የተጀመረውም ባለፈው ዓመት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከ ኤሜሬትስ እና ከክዌት መንግስት ጋር በጉዳዩ ላይ ከተነጋገሩ በኋላ እንደሆነ ገልጸዋል።
መሪዎቹ የዱቤ ነዳጅ ግዢ ስምምነት በማድረጋቸው በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ የነዳጅ እጥረት አያጋጥምም ያሉት አቶ ታደሰ ከሁለቱ አገራት ነዳጁን በዱቤ ማግኘት የምንችልበት ሁኔታ እስካልተቋረጠ ድረስ በአሁኑ ወቅት ችግሩ አሳሳቢ አይደለም ሲሉ ነግረውናል።
አሁን ላይ በኢትዮጵያ በቂ የነዳጅ አቅርቦት አለ ያሉን አቶ ታደሰ ሙሉ በሙሉ ችግሩ እንዳያጋጥም ተጨማሪ ነዳጅ ከውጪ እየገባ እንደሚገኝና በጅቡቲ ወደብ ላይም በቂ አቅርቦት እንዳለ ነግረውናል።
ኢትዮጵያ በሱዳን በኩል የምታስገባው ነዳጅ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ሱዳን ለጊዜው ድንበሯን በመዝጋቷ ምክንያት ተቋርጧል።
በሱዳን በኩል ያለው ትራንስፖርት ቢቋረጥም በቂ ድፍድፍ ነዳጅ በጅቡቲ ደረቅ ወደብ በኩል ወደ ሃገር ውስጥ በመግባት ላይ በመሆኑ እጥረቱ እንዳማይኖር ነግረውናል።
የኢትዮጵያ ዕለታዊ አማካኝ የነዳጅ ፍጆታ መጠን ከሁለት ሚሊየን ሊትር በላይ ሲሆን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እንቅስቃሴዎች ቢገደቡም ፍጆታው አለመቀነሱን ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።