Page 1 of 2

ፕሮፌሰር ሪቻርድ ዳውኪንስ ነብይ መሃመድ ጨረቃን ከፈላትና ክንፍ ባለው ፈርስ ላይ ተቀምጦ በመብረር ገነት ገባ ስለሚለው የእስልምና እምነት የሰጡት ምላሽ

Posted: 05 May 2020, 03:35
by clear12
That is why a neuroscientist says religion is a mental illness

Re: ፕሮፌሰር ሪቻርድ ዳውኪንስ ነብይ መሃመድ ክንፍ ባለው ፈርስ ላይ ተቀምጦ በመብረር ገነት ገባ ስለሚለው እምነት የሰጡት ምላሽ

Posted: 05 May 2020, 03:47
by clear12

Re: ፕሮፌሰር ሪቻርድ ዳውኪንስ ነብይ መሃመድ ክንፍ ባለው ፈርስ ላይ ተቀምጦ በመብረር ገነት ገባ ስለሚለው እምነት የሰጡት ምላሽ

Posted: 05 May 2020, 04:35
by Horus
ሪቻርድ ዎኪንስ የዛሬ 45 አመት ሰውን እንደ ቫይረስ ምትወጋ የሃሳብ መርዝ አለች፣ እሷም ልክ ጂን ሰውነታችን እንዴት እንደተገነባ እንደሚነግረን ሁሉ ሚም የምትባል የሃስብ ቫይረስ አይምሮአችህን እንዴት እንደሚሰራ የሚነግረን ቫይረስ ነው ብሎ አለም ከተንጫጫ በኋላ ያቺ ሚምን ማግኘት አልተቻለም ። ዛሬ ሳይንስም እምነት እምነትም ሳይንስ እንደሆነ ራሱ ፊዚክስ እያረጋገጠ ነው ። ይህ ማለት ግን ሳይኮቲክስ፣ ዲሉዥናል ዲሶርደር ፣ እብድ ሁሉ እምነት ነው ማለት አይደለም።

እግዚአብሄር ፣ አማልክት፣ ምልክቶች፣ ምሳሌዎች ተፈጥሮን ማወቂያ ሜታፎሮች፣ ኢንተለጀንሶች ናቸው። ለሚያውቅ ሰው በሳይንስና ፈጣሪ መሃል ልዩነት የለም። ጭፍን ተረት እንደ ፋክት ለሚያምኑ በኢቮሉሽኒስቱ ዶውኪንስ እና በእሕተ ማሪያም መሃል ያለው ወዝግብ ሊገባቸው አይችልም ። ኮግኒሽን፣ መገንዘብ ማወቅ ማመን ነው። በቃ ። ልዩነቱ አንድ ሰው ያመነበትን ነገር በሆነ ዘዴ በእኛ አለም ሊኖር መቻሉን ማሳየት አለበት ። እሀተ ማሪያም ልታሳይ አትችልም። የምታየው ነገር ማሳየት የማይቻል ነገር ስለሆነ !!! ንቃተ አይምሮ ኢማጊኔሽን ፈጥሮ የፈለገውን ፎቶግራፍ ሊሰራ ይችላል ። ይህ የኮንሺየስነስ አንድ መልኩ ነው። በቃ!!!

Re: ፕሮፌሰር ሪቻርድ ዳውኪንስ ነብይ መሃመድ ጨረቃን ከፈላትና ክንፍ ባለው ፈርስ ላይ ተቀምጦ በመብረር ገነት ገባ ስለሚለው የእስልምና እምነት የሰጡት ምላሽ

Posted: 05 May 2020, 05:03
by clear12
በመሰረቱ የቪዲዮ አላማ እኔ እስከተረዳኝ ምን ያክል እምነታዊ(Faith) አመለካከቶች ኢራሽናልና ኢሎጂካል የሆኑ ቲዎሪዎች ላይ የተመሰረተ መሆኑን ለማሳየት ነው በተለይ ብዙዎቹን ሳይንስ ጠጋ ብሎ ሲያጠናቸው የሳይኮሎጂካል ወይም ፊዚክሳዊ ምክንያታቸው ማወቅ ተችሏል :: ሀቁ ግን በ21ኛው ክፍለ ዘመን ብዙዎችን ነብይ በፈረስ በሮ ሰማይ ላይ ወጣ የሚለው እምነት ራሽናሊቲ ጥያቄ ላይ ቢያቀርቡ አያስደንቅም በተመሳሳይ በሌላውም እምነት ወጥስ ጥያቄ ውስጥ የሚገቡ ቲዎሪዎች መኖራቸው ሳይረሳ:: በመሰረቱ በኳንተም ፊዚክስ እምነትና ሳይንስን አንድ ለማደርግ የሚደረገው ጥረት ውጤት አሳይቶ ዳርዊናዊያን መሳሳታቸውን ቢያረጋግጥ ዳርዊናይናን እውነቱን በሳይንስ እስከተረጋገጥ ድረስ የሚቀበሉት ይመስለኛል፥፥ ችግሩ ግን ሁሉም ነገር ታውቋል አጠይቅ አትመርምር የሚለው አካሔድ አለማችንን ኤክስትሪሚስቶና ያልተማሩ ነብዮች እጅ ጥሎ ችግር ጦርነትና መከራን ሲያመጣ እንጂ መልካም ነገር አምጥቶ አያውቅም::

Re: ፕሮፌሰር ሪቻርድ ዳውኪንስ ነብይ መሃመድ ጨረቃን ከፈላትና ክንፍ ባለው ፈርስ ላይ ተቀምጦ በመብረር ገነት ገባ ስለሚለው የእስልምና እምነት የሰጡት ምላሽ

Posted: 05 May 2020, 06:39
by EPRDF
clear12 wrote:
05 May 2020, 05:03

ወንድሜ clear12

ኃይማኖት አዳምን በአፈር ፈጠረው፣ ሄዋንን ካለእናት በግራ አብራኩ ፈጠረለት፣ ጌታ እየሱስን ካለ አባት በድንግል እናቱ ማሪያም በመንፈስ ፈጠረው፣ ወይንም አምላክ ራሱ በሰው ተመስሎ የማሪያም ማዕፀን ውስጥ ተገኘ፣ ገብርኤል፣ሩፋኤል፣ ሚካኤል የሚባሉ መላእክት በክንፋቸው እየበረሩ ሰማይ ቤትና በምድር ላይ ያለውን ፍጥረት ያማልዳሉ ካለ፣ የነብዩ መሐመድ ክንፍ ባለው ፈረስ በሮ ገነትን ጎብኝቶ ተመለስ ካለ፣ ለምን ይደንቀሃል?

Re: ፕሮፌሰር ሪቻርድ ዳውኪንስ ነብይ መሃመድ ጨረቃን ከፈላትና ክንፍ ባለው ፈርስ ላይ ተቀምጦ በመብረር ገነት ገባ ስለሚለው የእስልምና እምነት የሰጡት ምላሽ

Posted: 05 May 2020, 06:43
by clear12
ሰላም EPRDF
ፕሮፌሰሩ በጥናት ላይ የተመሰረተ ሳይንሳዊ መልስ ሰጥተዋል ...ደግመህ አዳምጠው

ተጨማሪ ፕሮፌሰር ስቲቨንም ይህንን ጥያቄ በጥናት ላይ የተመሰረተ ሳይንሳዊ መልኩ ጥሩ አድርገው መልሰውታል

Re: ፕሮፌሰር ሪቻርድ ዳውኪንስ ነብይ መሃመድ ጨረቃን ከፈላትና ክንፍ ባለው ፈርስ ላይ ተቀምጦ በመብረር ገነት ገባ ስለሚለው የእስልምና እምነት የሰጡት ምላሽ

Posted: 05 May 2020, 14:21
by Horus
እምነት ከፍስፍና የተጠጋ በነበረበት ዘመን ነግሮች ሁሉ ይሻሉ ነበር ። ፍልስፍናና ሳይኮሎጂ ወደ ሳይንስ በተጠጉ ልክ ሃይማኖት የሚያነሳቸው የህላዌ እና የነፍስ ምንነት ጉዳዮች ከሳይንስ እየራቁ ቢመጡም አሁን ሁለቱም ተመሳሳይ ጥያቄ ለመመለስ እየለፉ ነው ፤ ሃይማኖት ዩኒቨርሰ ሁሉ በአንድ ፈጣሪ ተፈጠረ ሲል፣ ሳይንስ ዩኒቨርሰ ሁሉ ባንድ ትልቅ ፍንዳታ ተፈጥሮ በአንድ ፊዚካል ሕግ (ዩኒፋይድ ቲኦሪ) ይገለጻል ይላል ። እነዚህ ሁለት ወገኖች አስተማሪዎች ናቸው ። የኛ ችግር ያለው መሃይም አማኞች ምናብና ቅዠት እየቀደዱ መቀባጠራችው ነው ። ዞሮ ዞሮ ለሃይማኖትም ለሳይንስም መፍትሄ የሚገኘው ኮንሺየስነስ ምን እንደ ሆነ ሲረጋገጥና የሰው ልጅ በቋንቋ ተጠቅሞ ማንኛው ያለም የሌለም ነገር መፍጠር እንዴት እንደ ሚችል ሲረጋገጥ ነው። ይህ ደሞ ይሆናል ። እውነታ (ሪያሊቲ) ያለ ተመልካቹ አይኖርም፤ ይህ ነው ሚስጥሩ! ይህን ፊዚክስ አረጋግጧል ። ክንፍ ባለው ፈረሰ የሚጋልው መላክም የተመልካቹ ኢማጂኔቲቭ ፈጠራ ሆኖ በቋንቋ በስዕል አማካይነት ካንድ ሰው ወደ ሌላ ተላልፎ ወደ እውነታ ይለወጣል ። ይህ ሁሉ የኮንሺየስነስ ስራ ነው ።

Re: ፕሮፌሰር ሪቻርድ ዳውኪንስ ነብይ መሃመድ ጨረቃን ከፈላትና ክንፍ ባለው ፈርስ ላይ ተቀምጦ በመብረር ገነት ገባ ስለሚለው የእስልምና እምነት የሰጡት ምላሽ

Posted: 05 May 2020, 14:42
by clear12
የሰው ልጅ ማይንድ በሁለት ይከፈላል:: እነርሱም አንደኛው ከትምህርት የምናገኝው ሎጂክና ምክንያታዊነት ተጠቅመን የምንቀሳቀስበት conscious የሚባለው ሲሆን ሌላው ሳናውቀው ከልጅነታችን ከባህላችን ከሃይማኖታዊ ልምምዳችን የምናገኝው ሰብ ኮንሺዮስ (Subconscious Mind or habits mind )ማይንድ የሚባለው ነው፥፥ ከ95% በላይ የህይወታችን እንቅስቃሴ በሰብ ኮንሺየስ ማኝዳችን ( Subconscious Mind) የሚመራ ሲሆን ይህም ሳናውቀው ከልምድ የመነጨ መሆኑን ብዙ ሳይንሳዊ ምርምሮች ደርሰውበታል፥፥
ይህም ማለት ሃይማኖትም ጨምሮ ብዙ ከልጅነታችን ጀምሮ ያሳደግነው ልምምዳችን ከሰብ ኮንሺየስ ( Subconscious Mind) ጭንቅላታችን የመጣ ሳናስበው አውቶማቲካሊ የምናደርገው የምናስበው የምንመኝው ሲሆን የሰው ልጅ ይህንን ፕሮግራም የተደረገበትን ሲስተም የመቀየርም ችሎታ አለው፥፥ ለምሳሌ አንዴ መኪና መንዳት ከተማርን በኋላ ከሰዎች ጋር እያወራን ቢሆን ወይም በሌላ ነገር ተጠምደን መኪና ሳናስብና ሳንጭነቅ ማርሽ ቀይረን መንዳት የሚያስችለን ከልምድ የመጣው ሰብ ኮንሺዮስ (Subconscious Mind or habits mind )ማይንድ ነው::
በነገራችን ላይ የመጀመሪያ ሰባት አመታቸውን በበውጪ የተወለዱ ህጻናት ለምን 100% የሀበሻ አስተሳሰብና አመለካከት ሙሉ በሙሉ አያንጸባርቁም? የሚለውን ጥያቄ ስብ ኮንሺየስ ማይንዳቸው ( Subconscious Mind) የት ነው ፕሮግራም የተደረገው የሚለው ጥያቄ ይመልሳል፥፥ በተመሳሳይ ሁኔታ የትውልድ ልዩነት ያላቸው (1970-2020 ደርግ / ወያኔ / አብይ)ሰዎች አስተሳሰባቸው ለምን ይለያያል የሚለው ጥያቄ ስብ ኮንሺየስ ማይንዳቸው በልጅነታቸው በምን ፕሮግራም ተደረገ የሚለው ይመልሰዋል:: ስለዚህ ነጥብ ዶክተር ብሩስ ሊፕቶን ያቀረቡት ቪዲዮ በስፋት ስለሚያስረዳ ማየት ከማንበብ ስለሚበልጥ ዝርዝሩን ትቼ ሊንኩን እተዋለሁ::

Re: ፕሮፌሰር ሪቻርድ ዳውኪንስ ነብይ መሃመድ ጨረቃን ከፈላትና ክንፍ ባለው ፈርስ ላይ ተቀምጦ በመብረር ገነት ገባ ስለሚለው የእስልምና እምነት የሰጡት ምላሽ

Posted: 05 May 2020, 18:50
by Horus
እኔ በጣም የተለየ ቲኦሪና ፍልስፍና ነው ምከተለው ። ግሪኮች የጀመሩት ስህተት ማለትም ቦዲ ማይንድ ዱዋሊዝም አሁን ተሽሯል ። አሁን ኒዉሮ ሳይንስ በደረሰበት ደረጃ ያለው እውቀት ኢምቦዲድ ኮኚሽን ይባላል። ሰውነታችን ሁሉ ብሬን ነው ። ሰብኮንሸስ የምንለው ኢምቦዲድ አንጎል ነው ። ማለትም የድሮ ሞዴል አሁን ሳይንስ አይቀበለውም ። ሰውነታችን ሁሉ ብሬይን ነው። ይህ ነው አዲሱ ንዉሮሳይንስ ።
ሁለት ሊንክ ይሀው።

Re: ፕሮፌሰር ሪቻርድ ዳውኪንስ ነብይ መሃመድ ጨረቃን ከፈላትና ክንፍ ባለው ፈርስ ላይ ተቀምጦ በመብረር ገነት ገባ ስለሚለው የእስልምና እምነት የሰጡት ምላሽ

Posted: 05 May 2020, 18:56

Posted: 05 May 2020, 19:33
by sun
All of these witch doctors and voodoo priests were/are sniffing LCD, Cocaine and Shisha for getting very high and coming out to explain what is going on in their own brains which is NOTHING TO DO WITH CHRIST OR Prophet MOHAMMAD, since the idea is only the result of their own willing self intoxication and hypnotization which they claim to be realities in the world visible and accessible to them but not to the ordinary non smoking and non sniffing folks.

Let alone that they are telling the holy men's flight to heaven even some these false prophesy preaching redneck patriarchal liar baboons themselves tried to fly from the high cliffs or high buildings when they happen to be high themselves and got themselves instantly killed and there after buried. Why should such false prophets then and now were/are eager to make false prophesies?
:shock:

"The prophets are prophesying lies in My name," the LORD replied. "I did not send them or appoint them or speak to them. They are prophesying to you a false vision, a worthless divination, the futility and delusion of their own minds." Bible, Jeremiah 14:14 :P

Re: ፕሮፌሰር ሪቻርድ ዳውኪንስ ነብይ መሃመድ ጨረቃን ከፈላትና ክንፍ ባለው ፈርስ ላይ ተቀምጦ በመብረር ገነት ገባ ስለሚለው የእስልምና እምነት የሰጡት ምላሽ

Posted: 05 May 2020, 23:53
by Dawi
sun wrote:
05 May 2020, 19:33

sun,

I truly enjoyed all the videos in this thread; I usually stay cleared from "clear12" cause he posts those videos of the fanatics cause they bore me but, today I realized he has reasons for it; Horus intensified the discussion, well, you ruled the thread out.

Looks like Asfaw is part of the deep state! What do you think? He looks guilty! :P

Re: ፕሮፌሰር ሪቻርድ ዳውኪንስ ነብይ መሃመድ ጨረቃን ከፈላትና ክንፍ ባለው ፈርስ ላይ ተቀምጦ በመብረር ገነት ገባ ስለሚለው የእስልምና እምነት የሰጡት ምላሽ

Posted: 06 May 2020, 00:42
by Horus
ዳዊ፣
ለምን መሰልህ እዚህ ኮሜንት ያረኩት ። ሰዉ ሃይማኖትን ሲደግፍ ፣ ወይ ሲቃወም ልክ እንደ ድሮ ምክንያታዊ ፣ ኢምክንያታዊ ፣ ራሽናል ፣ ኢሞሽናል እያለ የድሮ ሞዴል ይዞ ነው ያለው ። ይህ እነ ዴካርት የሰሩት ቦዲ ማይንድ ክፍፍል ስህተት አሁን ፈርሷል እና አበሻም አዲሱ ሞዴል ጋር እንዲተዋወቅ ብዬ ነው ። ይህ ፊልድ እጅግ ሰፊ ነው ግን ከዚህ አልፈው ይህን አዲስ ቲኦሪ ኦፍ ማይንድ እና የቋንቋ ሳይንስ ማወቅ ለሚሹ ለመጠቆም ነው።

Re: ፕሮፌሰር ሪቻርድ ዳውኪንስ ነብይ መሃመድ ጨረቃን ከፈላትና ክንፍ ባለው ፈርስ ላይ ተቀምጦ በመብረር ገነት ገባ ስለሚለው የእስልምና እምነት የሰጡት ምላሽ

Posted: 06 May 2020, 01:10
by clear12
Dawi wrote:
05 May 2020, 23:53

sun,

I truly enjoyed all the videos in this thread; I usually stay cleared from "clear12" cause he posts those videos of the fanatics cause they bore me but, today I realized he has reasons for it; Horus intensified the discussion, well, you ruled the thread out.
[/image]
ስለራሴ ለመናገር ሳይሆን በዚህ ፎረም ውስጥ የምለጥፈው መረጃ ፎረሙን ቦሪንግ ለማድረግ ሳይሆን:

-በሃገራችን ሀይማኖት ምን ያክል ታቡ(Taboo) እርሶ የተባለ ለምንና እንዴት ተብሎ የማይጠየቅ ርእስ መሆኑንና በሃይማኖት ማስክ የሚሰሩ ወንጀሎች ለተጠቂዎቹ /Spiritual Abuse Victims) በራሳቸው ሊረዱትና ሊፈቱት ከሚችሉት በላይ መሆኑን በአይኑ ኢትዮጵያ ለተመለከተ ሰው በየትኛው መልኩ ይህንን የአለማወቅ እንዲሰበር የማይመቹ መረጃዎችን መልቀቅ ያስፈልጋል ብሎ የሚንቀሳቀስ ሰው ነኝ እንጂ ፋናቲክነት ከሗላ የሚገፋው ሰው አይደለሁም:: ውጤቱም በቅርቡ በታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ነብይ ነን ብለው የሚያጭበርብሩ ሰዎች በኦርቶዶክስም በጴንጤም እምነት ውስጥ የደረሰባቸውን መጋለጥ ማየቱ በቂ ነው፥፥ ይህ መጋለጥ ብዙ ወጣቶችን ከታሰሩበት የአስተሳሰብ እስራት (Mind Control) ፈቶ ነጻ ትውልድ ያደርጋቸዋል ብዬ አምናለሁ ለዚህ ደግሞ የሆነ ስው መጥረጊያውን ወስዶ ዝቅ ብሎ ቆሻሻውን ወደ ላይ ሊያወጣው ግድ ይላል:: ይህንን ለማድረግ ቦሪንግ መሆን ሊያስፈልግ ይችላል::

- ሌላው በጣም ልብ የሚሰብረውና የተማረ ኢትዮጵያዊን በሙሉ አንገት የሚያስደፋው አሜሪካና አውሮፓ የተማሩ ለብዙ ወጣቶች ምሳሌ (Role model on Logical Thinking/Reasoning)መሆን የሚገባቸው ፕሮፌሰሮችና ዶክተሮች እነዳንሳ ዘንድ እየሔዱ ለማስጠንቆል ሲንከባለሉ ማየቱ ብቻ ሳይሆን ሀገር ቤት እነርሱ ለእስራኤል ዳንሳ ከሰገዱ እኔ ማን ነኝ ብሎ የሚጠፋው ወጣቱ ትውልድ ነው:: viewtopic.php?f=2&t=218245

-በበኩሌ የምንም ሃይማኖት ጭፍን ተከታይ አይደለሁም ልሆንም አልችልም ነገር ግን ሳይንስና ሃይማኖት ለሚያስረዱ ታሪካዊ አመለካከቶች ምርምሮችና ፍልስፍናዎችን ለመረዳት የምጥር ሰው ነኝ እንጂ የማንንም አጃንዳ አንግቤ አልዞርም::

Re: ፕሮፌሰር ሪቻርድ ዳውኪንስ ነብይ መሃመድ ጨረቃን ከፈላትና ክንፍ ባለው ፈርስ ላይ ተቀምጦ በመብረር ገነት ገባ ስለሚለው የእስልምና እምነት የሰጡት ምላሽ

Posted: 06 May 2020, 02:32
by clear12

Re: ፕሮፌሰር ሪቻርድ ዳውኪንስ ነብይ መሃመድ ጨረቃን ከፈላትና ክንፍ ባለው ፈርስ ላይ ተቀምጦ በመብረር ገነት ገባ ስለሚለው የእስልምና እምነት የሰጡት ምላሽ

Posted: 06 May 2020, 03:33
by Dawi
clear12 wrote:
06 May 2020, 01:10
በበኩሌ የምንም ሃይማኖት ጭፍን ተከታይ አይደለሁም ልሆንም አልችልም ነገር ግን ሳይንስና ሃይማኖት ለሚያስረዱ ታሪካዊ አመለካከቶች ምርምሮችና ፍልስፍናዎችን ለመረዳት የምጥር ሰው ነኝ እንጂ የማንንም አጃንዳ አንግቤ አልዞርም::
clear,

Sorry for my ambiguous comment earlier; It was meant to indirectly apologize to you for evading your other threads; it was my loss in assuming that you were posting some "ጭፍን ሃይማኖት" stuff.

I learned a lot from you and Horus's comments and the videos you guys posted. I appreciate both of you for reviving the curiosity I have in a subject matter I enjoy following.

Re: ፕሮፌሰር ሪቻርድ ዳውኪንስ ነብይ መሃመድ ጨረቃን ከፈላትና ክንፍ ባለው ፈርስ ላይ ተቀምጦ በመብረር ገነት ገባ ስለሚለው የእስልምና እምነት የሰጡት ምላሽ

Posted: 06 May 2020, 05:00
by EPRDF
clear12 wrote:
05 May 2020, 05:03
ሀቁ ግን በ21ኛው ክፍለ ዘመን ብዙዎችን ነብይ በፈረስ በሮ ሰማይ ላይ ወጣ የሚለው እምነት ራሽናሊቲ ጥያቄ ላይ ቢያቀርቡ አያስደንቅም በተመሳሳይ በሌላውም እምነት ወጥስ ጥያቄ ውስጥ የሚገቡ ቲዎሪዎች መኖራቸው ሳይረሳ::
clear12
በነገራችን ላይ፣ ይህንን የሪቻርድ ዶውኪንስን ኢንተርቪው ከረዥም ጊዜ በፊት አይቼው ነበር፣ ሰውዬው ሳይንቲስት ስለሆነ ነቢዩ መሐመድ በፈረስ ወደ ሰማይ በረረ የሚባለውን እምነት dismiss ያደርገዋል፣ ያም አይደንቅም ምክኒያቱም በኣንደበቱ አንደተናገረው፣ በብዙ የሚያሳስበውና የሚጨነቀው ለሳይንስ ነው ብሎዋልና፣ መልካም ነው ያም አያጣላም። ነገር ግን፣ አንተም በትሬድህ አርዕስት እንዳስቀመጥከውና ልታስነብበን እንደከጀልከው
ፕሮፌሰር ሪቻርድ ዳውኪንስ ነብይ መሃመድ ጨረቃን ከፈላትና ክንፍ ባለው ፈርስ ላይ ተቀምጦ በመብረር ገነት ገባ ስለሚለው የእስልምና እምነት የሰጡት ምላሽ
ሰውዬውም የነቢዮ መሐመድን አንድ case ብቻ ነጥሎ በማውጣትና በማፌዝ የራሱን ሳይንትፊክ የሆነ የዚህችን universe ዕይታ justify ለማድረግ ሲሞክር ተደመጠ። እኔም በዚህ ትሬድ ውስጥ ልገባ የሳበኝ ምክኒያት፣ ነቢዩ በሮዋል አልበረረም፣ ዕውነት ሐሰት ለማለት ሳይሆን፣ ዶውኪንሰን የነቢዮን በፈረስ መብረር ሲያነሳ ወይንም ይህንን እንደምሳሌ ከመጥቀስ ይልቅ የኣብረሃም ኃይማኖቶች ወይም monotheistic religions:የምንላቸው የዓለማችን ሕዝብ ገሚሱ እምነት የሆኑት Christianity, Islam and Judaism በጋራ የሚጋሩትና ለአብነትም ለመጥቀስ የሚያዋጡ የእምነት ምሳሌዎች ነበሩ፣ ለምሳሌ ዮናስ ለሳምንታት ዓሳ ነባሪ ሆድ ውስጥ ኖረ፣ ሙሴ በበትሩ ውኃውን ሲመታው ቀይ ባሕር ለሁለት ተሰንጥቆ ደረቅ መሬት ተከፈተለት፣ሕዝቡንም አሻገረ፣ ሔዋን ከኣዳም ግራ ጎን ተፈልቅቃ ወደ ሕይወት መጣች፣ ክርስቶስ/ ኢሳ የሞተ አነስነሳ፣ ራሱም ከሞት ተንስቶ ወደ ሰማይ አረገ።።ሌሎችም ብዙብዙ ታዕምራዊ እምነቶች በነኚህ ኃይማኖቶች ተካተዋል፣ እንዲያው ከነዚህ ኣንዱን ከነቢዩ መብረር ጎን በመጥቀስ ለክርክሩ ምሰሶ ቢያደርግ ኖሮ፣ ሳይንቲስቱ ትንሽ ራሽናል በሆነ ነበር። የJudeo/Christianity ውስጥ ያሉትን ተመሳሳይ ታዕምራዊ እምነቶችን ባለመዳፈር simply religious belief ብሎ preserve ለማድረግ በመሞከር፣ የእስልምናን ተኣምራዊ እምነት ግን፣ Scientific belief ስር በመደበቅ፣ በቀልድና ፌዝ መልክ አድበስብሶ ለማለፍ ሙከራው Biased የሆነ አመለካከትና፣ አምንበታለሁ ለሚለው ሳይንስ ራሱም sincerity የሚጎድለው ሊቅ ሆኖ አገኘሁት ለማለት ነው። ከምስጋና ጋር።

Re: ፕሮፌሰር ሪቻርድ ዳውኪንስ ነብይ መሃመድ ጨረቃን ከፈላትና ክንፍ ባለው ፈርስ ላይ ተቀምጦ በመብረር ገነት ገባ ስለሚለው የእስልምና እምነት የሰጡት ምላሽ

Posted: 06 May 2020, 05:09
by Noble Amhara
clear12 wrote:
06 May 2020, 02:32
Why are you bringing religion into a secular forum, your religious obsession belongs in church!

Re: ፕሮፌሰር ሪቻርድ ዳውኪንስ ነብይ መሃመድ ጨረቃን ከፈላትና ክንፍ ባለው ፈርስ ላይ ተቀምጦ በመብረር ገነት ገባ ስለሚለው የእስልምና እምነት የሰጡት ምላሽ

Posted: 06 May 2020, 05:26
by clear12
EPRDF የእኔ አላማ እስላምን ለይቶ ለማቅረብ ሳይሆን እንደሰለጠነና የተማረ ሰው መወያየት ከተቻለ የቀረበ ሀሳብ ነው :: ስለፕሮፌሰሩ በተለያየ አርእስቶችና እምነቶች ላይ የሰጠው ሀሳብ በዩቱብ ስለሚገኝ ማየት ይቻላል:: ቢሆንም ስለሃሳብህ አመሰግናለሁ

፥ዳዊት: ስለራሴ ያነሳሁት ከአንተ ጋር ሳላገናኝ ነው ቢሆንም ሀሳብህን በሙሉ ተቀብያለሁ፥፥አመሰግናለሁ

ኖበል አማራ: ሳይንስና ሃይማኖት በአንድነት ትርጉማቸውንና ምንነታቸውን ሳይንስ እያስረዳ የሚያሳይ መረጃ /ቪዲዮ ደረጃ ቀርቦልህ ለስድብ መሮጥህ ጥሩ አይመስለኝም ሀይልህን ለፖዘቲቭ ነገር ተጠቀምበት