Page 1 of 1

ኮሮና ለኢትዮጵያ ስልጣኔ መለምለም የተላከ ጸጋ ነው (ከሳጥን ውጭ ለሚያስቡ) !!

Posted: 05 May 2020, 03:11
by Horus

እኔ ሆረስ፣ ባለሁለት አይናማው ንስር ቃላት መፍለጥ አይመቸኝም !

ይህን ሃሳቤ ማይገባቸው ወይም ማይጥማቸው እንደሚኖሩ አልጠራጠርም ። ኮሮና በሽታ ያለም ሁሉ ሕዝብን ችሎታ በመፈተን ላይ ይገኛል።

ኮሮና ማለት ። ቀውስ፣ ወረርሽኝ ፣ መፍረስ ፣ ወስራከት፣ ቄዎስ፣ ሽብር፣ ዲሶኦርደር ፣ መሰባበር፣ ማለት ነው። ይህ በሽታ በግለሰብ፣ በቡድን፣ በአገር ደረጃ አለምን እየፈተነ ነው።

ብዙ የቲኦሪ ዝብዝብ ውስጥ ሳልገባ፣ በዚህ መአት ምንከሸ፣ በዚህ ምጠጥ ምክንያት፤

(ሃ) የሚጠፉ፣
(ለ) ተሰብረው የሚያገግሙ፣
(ሓ) የማይሰበሩ፣
(4) በቀውሱ የሚያብቡ (ይህች የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ናት!!)

ክፍሎች አሉ።

ያ በያንዳንዱ ክፍል ክህሎት ኢንተለጀንስ ፣ ብቃት ፣ እውቀት ይወሰናል ።

በኢትዮጵያ ለስንት መቶ ዘመን ያልተፈለሰፉ የንጽህና እና የጤና ዘዴያት፣ ክህሎታትሃ፣ ቴክኖሎጂ እና መሳሪያዎች እንደ ጉድ እየተፈለሰፉ ነው።

በሌሎችም ብዙ የሰው ባህሪያት ዙሪያ ህዝባችን ሳይንሳዊ ስልጣኔ ውስጥ እየገባ ነው።

መታጠብ ፣ መጸዳድት፣ በሰውና ሰው መሃል ያለን ድንበር ማክበር፣ ያንዱን አፍ ሽታ ከሌልው መከልከር፣ ውሃን በብዛት የመጠቀን ባህል ብቻ ሌላ ሌላ ሌላ !!

ፈጠራ ተጧጡፏል !!! መንግሥትም ነገሩ በደንብ ገብቶት በፈጠራው ፈረስ ሊጋልብ አዎ ብሏል !!!

ኢትዮጵያ ትቅደም !! ኬር ዬሁን !!!

Re: ኮሮና ለኢትዮጵያ ስልጣኔ መለምለም የተላከ ጸጋ ነው

Posted: 05 May 2020, 03:33
by Horus

Re: ኮሮና ለኢትዮጵያ ስልጣኔ መለምለም የተላከ ጸጋ ነው

Posted: 05 May 2020, 03:41
by Horus

Re: ኮሮና ለኢትዮጵያ ስልጣኔ መለምለም የተላከ ጸጋ ነው (ከሳጥን ውጭ ለሚያስቡ) !!

Posted: 05 May 2020, 04:27
by clear12
sure corona can be a blessing in disguise for Ethiopia!!
ሌላም ካስወገደው ቆሻሻ አንዱ ኢትዮጵያ ውስጥ በየትኛውም እምነት ውስጥ የተሰገሰጉ ነብይ ነን ባዮች የሳይኮሎጂ ሌቦች እንጂ ምንም የተለየ ሃይል እንደሌላቸው ለህዝባችን ትምህርት ሰጥቷል :idea: :idea:

Re: ኮሮና ለኢትዮጵያ ስልጣኔ መለምለም የተላከ ጸጋ ነው (ከሳጥን ውጭ ለሚያስቡ) !!

Posted: 05 May 2020, 04:45
by Horus
clear12 wrote:
05 May 2020, 04:27
sure corona can be a blessing in disguise for Ethiopia!!
ሌላም ካስወገደው ቆሻሻ አንዱ ኢትዮጵያ ውስጥ በየትኛውም እምነት ውስጥ የተሰገሰጉ ነብይ ነን ባዮች የሳይኮሎጂ ሌቦች እንጂ ምንም የተለየ ሃይል እንደሌላቸው ለህዝባችን ትምህርት ሰጥቷል :idea: :idea:
እጅግ እጅግ ትክክል።

እንኳንስ ኮሮና ራሷ እህተ ማሪያም ብዙ የኦርቶዶክስ ፋናቲኮችን እንዲነቁ ምክንያት ሆናለች ። የኦርቶዶሽ አክራሪ ባይኖር እሷ አትፈጠርም ነበር። እምነት ለሰው አስፈላጊ ነው ። ግ ን ጭፍን እብደት ፣ ከሪያሊቲ የተላቀቀ መቀባጠር ትርፉ እህተ ማሪያን ማምረት ነው።

Re: ኮሮና ለኢትዮጵያ ስልጣኔ መለምለም የተላከ ጸጋ ነው (ከሳጥን ውጭ ለሚያስቡ) !!

Posted: 05 May 2020, 05:07
by clear12
Horus wrote:
05 May 2020, 04:45
clear12 wrote:
05 May 2020, 04:27
sure corona can be a blessing in disguise for Ethiopia!!
ሌላም ካስወገደው ቆሻሻ አንዱ ኢትዮጵያ ውስጥ በየትኛውም እምነት ውስጥ የተሰገሰጉ ነብይ ነን ባዮች የሳይኮሎጂ ሌቦች እንጂ ምንም የተለየ ሃይል እንደሌላቸው ለህዝባችን ትምህርት ሰጥቷል :idea: :idea:
እጅግ እጅግ ትክክል።

እንኳንስ ኮሮና ራሷ እህተ ማሪያም ብዙ የኦርቶዶክስ ፋናቲኮችን እንዲነቁ ምክንያት ሆናለች ። የኦርቶዶሽ አክራሪ ባይኖር እሷ አትፈጠርም ነበር። እምነት ለሰው አስፈላጊ ነው ። ግ ን ጭፍን እብደት ፣ ከሪያሊቲ የተላቀቀ መቀባጠር ትርፉ እህተ ማሪያን ማምረት ነው።
በትክክል ምንም መጨመር አያስፈልገውም

Re: ኮሮና ለኢትዮጵያ ስልጣኔ መለምለም የተላከ ጸጋ ነው (ከሳጥን ውጭ ለሚያስቡ) !!

Posted: 05 May 2020, 09:08
by clear12
ሌላው የኮሮና ክራይስ አስተማሪ ሆኖ (Lessons Learned) ያለፈበት ክፍል አንዱ የፌደራሊስትና አሃዳዊ (Federalist vs. Unionist ) አስተድደሮች ወረርሽኝና መሰልት ችግሮችን ለመከላከልና ፈጥኖ ለማስወገድ ያላቸውን ጥቅምና ጉዳት በምሳሌም ጭምር ነው፥፥ ከኮሮና ክራይስ ጋር በተያያዘ ክፍለ ሀገሮችን ለመዝጋትና ለመክፈት ትራንፕ ከየስቴቱ ገቨርነሮች ጋር ያደረገውን ጭቅጭቅና በየአውሮፓ ፌደራላዊና አሃዳዊ አስተዳደር የሚከተሉ አገሮች አገራችው ውስጥ ያደረጉትን ከተሞችን ለመዝጋትና ለመክፈት ፣ ወረርሽኙን ለመከላከል የደረሱበት ውጤት እንዲሁም የህገ መንግስትና ፓርላመንት ውሳኔ ውጣ ውረዶችን ወደፊት ረጋ ብሎ አጥንቶ ለሚነሳ ሀገር ውስጥ ፓርቲ ለምርጫውም ይሁን ለቀጣይ እድገቱ ብዙ ትምህርት ያገኛል ብዬ አስባለሁ

Re: ኮሮና ለኢትዮጵያ ስልጣኔ መለምለም የተላከ ጸጋ ነው (ከሳጥን ውጭ ለሚያስቡ) !!

Posted: 05 May 2020, 09:23
by Digital Weyane
ከአክሱም ሆቴል ግቢ ውጭ የሚያስቡ የወያኔ መሪዎቻችን ኮሮና ቫይረስን ኤርትራና ኢትዮጵያ ሊያጠፋ የሚችል ኃይል ነው ብለው ስለሚያስቡ ለትግራይ ነፃነት ትግል "A blessing in disguise" ነው እያሉ ያስተምሩናል።