-
Revelations
- Senior Member+
- Posts: 34573
- Joined: 06 Jan 2007, 15:44
-
Revelations
- Senior Member+
- Posts: 34573
- Joined: 06 Jan 2007, 15:44
-
Revelations
- Senior Member+
- Posts: 34573
- Joined: 06 Jan 2007, 15:44
-
Revelations
- Senior Member+
- Posts: 34573
- Joined: 06 Jan 2007, 15:44
Re: የተስፋዬ ገብረአብን ተራ ቅጥፈት ፎቶው ያጋልጣል
Tesfaye like he said, he was born in Debreziet from Eritrean parentage. Due to the economic status of his family and the split up of his parents he has led a tough life. He was raised by his step mother and life for him was unbearable so he joined the Derge army. Towards the end of the war Tesfaye was captured by EPRDF fighters in one of the battle ground and became a POW. The fact that he was a Tigrigna speaker, however, was a good opportunity for him to join the struggle. Knowing Eritrean heritage some EPRDF commanders at the time have advised him to join the liberation movement in Eritrea but he told them that he wants to fight for the liberation of Ethiopians and officially stated that he has no faith in the Eritrean liberation movement.
After he joined the struggle, he was assigned in the propaganda branch of EPRDF until the city of Addis came under the control of the liberation fighters. During that time the key positions in the Ethiopian media was given to the EPRDF fighters in the propaganda wing and Tesfaye was one of the beneficiaries of it and he became head of the Ethiopian press known as press memria. This position was given to him not because of his knowledge of the media or his talent but it was the case of among the blind one eyed man is king. Otherwise when Tesafaye joined the Derg army he did not even complete secondary school.
-
( ͡° ͜ʖ ͡°)
- Member
- Posts: 2312
- Joined: 11 Jan 2020, 21:22
Re: የተስፋዬ ገብረአብን ተራ ቅጥፈት ፎቶው ያጋልጣል
After his mother passed away, the Oromo native Tesfaye Gadaa Gebreab moved in with his older sister and he lived with her until he enlisted in the Derg army out of desperation. He doesn't have a step-mother. That part is Weyane's propaganda.
After he was captured on the battlefield, he never made any statements about not wanting to join the EPLF, nor was he made an offer to join. That part is also a Weyane propaganda.
Anyone who read the native Oromo Tesfaye Gadaa Gebreab's books is very familiar with the background of the most prolific author in Ethiopia's history.
After he was captured on the battlefield, he never made any statements about not wanting to join the EPLF, nor was he made an offer to join. That part is also a Weyane propaganda.
Anyone who read the native Oromo Tesfaye Gadaa Gebreab's books is very familiar with the background of the most prolific author in Ethiopia's history.
-
( ͡° ͜ʖ ͡°)
- Member
- Posts: 2312
- Joined: 11 Jan 2020, 21:22
Re: የተስፋዬ ገብረአብን ተራ ቅጥፈት ፎቶው ያጋልጣል
በኮሎኔልነት ማዕረግ የወያኔ መርሰነሪ ጦርን ሲያገለግል የነበረው የጂማ ተወላጅ የሆነው ኮሎኔል አበበ ገረሱ የሰጠው ቃለ-መጠይቅ ነው።
ማን ያውራ? የነበረ! ……. ማን ያርዳ? የቀበረ!
ፃድቃንና ፆረና

TPLF General Tsadqan Gebre-Tensae providing the general scope of the invasion campaign
"እንደምን አደርክ ኮሎኔል?"
"ሰላም ላንተ ይሁን ጋዜጠኛው።"
"ቀጠሮ በማክበርህ አመሰግናለሁ።"
"ወታደር አይደለሁ መቸስ!"
"... እንግዲህ ወደ ጉዳያችን እንዝለቅ። ጄኔራል ፃድቃንና የፆረና ውጊያን በተመለከተ አጫውትሃለሁ ብለኸን ነበር። ከየት ብንጀምረው ይሻል ይሆን?"
"ከመሃሉ መጀመር ሳይሻል አይቀርም። ያየሁትና የሰማሁት እንደወረደ ላውጋህ። ጸሃፊው አንተ ነህና እንደሚሆን ታደርገዋለህ።"
"መልካም ወንድሜ። አንተ እንደመጣልህ ተናገር። እኔ ያንን ወስጄ ለታሪክ ተረካቢው ትውልድ አደርስልሃለሁ።"
"... ወያኔ ወደ ኤርትራ ጦርነት የገባው 10 ክፍለጦሮች ይዞ ነበር" ሲል ጀመረ። እናም ቀጠለ፦
"... ከዚህ ዉስጥ አንዱ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ሲሆን፤ አንድ ተጨማሪ ኮማንዶ ብርጌድም ነበር። በ1991 ጦርነቱ ሲጀመርም ይህ የሰራዊት ሃይል በአራት ግንባሮች ነበር ለማጥቃት የተዘጋጀው። ቡሬ፣ ዛላንበሳ፣ ፆረና እና ባድመ ግንባሮች ላይ ማለት ነው።
በ1991 ላይ የተደረገው የመጀመሪያው ዉግያ የተበላሸና በጣም ኣሰቃቂ ነበር። የጦር መኰነን ሆነህ እንደ ባለ ሙያ ስታየው ዉግያው በጥቅሉ የሙያ ብቃት ያልታየበት ኣሳፋሪ ጦርነት ነበር ማለት ይቻላል።
ያ ሁሉ ዜጋ ያለቀበትና ያ ሁሉ የአገር ሃብት የወደመበት ጦርነት ከጦርነት አመራር ችግር መሆኑ በግልጽ እየታወቀ አንድም የጦርነቱ መሪ ተጠያቂ ሳይሆን እንዲሁ መቅረቱ በጣም ያሳዝነኛል። ይልቁን በምርጫ 97 "ቅንጅትን ኣልተዋጋችሁም!"... "የኣመለካከት ችግር ኣለባችሁ!" በሚል ከጦርነቱ በላይ ትኩረት ተሰጥቶ ነበር። ከጄኔራል መኮንን እስከ ተራ ወታደር 20,000 የመገመት መለዮ ለባሽ ያለሃጢኣቱ ታስሮ ተባሮአል። ከሃላፊነት እንዲወገድ ተደርጎአል።
በጃንሆይና በደርግ ዘመን ኤርትራ ላይ ዉጊያ ተደርጎ የተሰዋው ዜጋችን ቁጥር ከ250 ሺህ እስከ 300 ሺህ ይደርሳል። ከዚህ ኣንጻር ወያኔ በአንድ አመት ዉስጥ ኤርትራ ላይ ያስፈጀው የወታደር ቁጥር በጣም አሳፋሪ ነው። ከመከላከያ የሰው ሃይል አስተዳደር ልማት መምሪያ ሰነዶች ያገኘሁት መረጃ እንደሚያሳየው፣ በጠቅላላ በኢትዮ-ኤርትራ ዉግያ 98,700 ወታደር ሲሞትብን፣ 194,300 ቁስለኛ ተረክበናል። ከኦርዲናንስ እዝ ያገኘሁት መረጃ ደግሞ መጀመሪያ ለዉጊያ ከተዘጋጀው ከባድ መሳርያ ⅔ኛው መውደሙን ነግረዉኛል። ይህንን ትርጉም አልባ ጦርነት የመሩት መሪዎች ሰኣረ መኮንን፣ ሳሞራ የኑስ፣ ዮሃንስ ገብረመስቀል፣ ታደሰ ወረደ፣ ኳርተር (አብርሃ ወልደማሪያም)፣ ብርሃነ ነጋሽ፣ የተባሉት ጄኔራሎች ናቸው። የጦርነቱ የማእከላዊ እዝ አባላት ደግሞ መለስ ዜናዊ፣ ስዬ አብርሃ፣ ተወልደ ወልደማርያም፣ ኣለምሰገድ ገብረኣምላክ፣ ተፈራ ዋልዋ፣ ፃድቃን ገብረትንሳኤ እና ክንፈ ገብረመድህን ነበሩ።

የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ሰነድና መረጃ ገና ታሪክ ጸሃፊዎች እጅ አልገባም። ወደፊት ብዙ ኣስገራሚ ታሪኮችን ልንሰማ እንችል ይሆናል። በ1991 የተካሄደውን የመጀመሪያ ዙር ጦርነት እንኳ ብናይ በጣም መሰረታዊ የሆኑ ወታደራዊ ስህተቶች በቀላሉ ማውጣት እንችላለን።
የቡሬ ግንባር ላይ ታደሰ ወረደ ተመደበ።
የተሰጠው ትእዛዝ አሰብን ከያዘ በሁዋላ የቀይ ባህርን ዳርቻዎች እያጠቃ፣ ምፅዋን እንዲቆጣጠርና እዚያው ሆኖ ቀጣዩን ግዳጅ እንዲጠባበቅ ነበር።
ፆረና ላይ አብርሃ ወልደገብርኤል፣ (በቅርብ ፃድቃን እየተከታተለው)፣ ዛላንበሳ ደግሞ ብርሃነ ነጋሽ ነበሩ።
ሁለቱም በየአቅጣጫው አጥቅተው ሰገነይቲ ላይ በመገናኘነት አንድ ግንባር እንዲፈጥሩና በአንድ ኮማንድ ስር በመደራጀት አስመራ እንዲገቡ ታዘዙ።
ባድመ ላይ ሰአረ መኮንንና ዮሃንስ ገብረመስቀል፣ እንዲሁም አበባው ታደሰ (በቅርብ ሳሞራ እየተከታተላቸው) ተሰየሙና ቆላማውን የኤርትራ ክፍል ሙሉ በሙሉ እንዲቆጣጠሩ ተነገራቸው።
ለዚህ እቅድ የአሸዋ ገበታ በየአካባቢው ተዘጋጅቶ ያን መሰረት ያደረገ ሰፋፊ ልምምዶች ተደርገዋል። የጦርነቱ እቅድም በየደረጃው ተነግሮኣል። በእቅዱ ላይ ታዲያ ብዙ ኣከራካሪ ጉዳዮች ተነስተው ነበር። ለምሳሌ አዲግራት ላይ በተዘጋጀው የአሸዋ ገበታ ልምምድ ላይ የ23ኛ ክፍለ ጦር ኣዛዥ የነበረው ኮሎኔል በርሄ ገብረማርያም፥
- "ኤርትራን የመውረር እቅድ ፖለቲካዊ ኪሳራ አያስከትልብንም ወይ? ሰራዊታችንስ የመዋጋት ፍላጎት እንዴት ይኖረዋል? እንዴትስ ማሳመን ይቻላል? በትክክልስ ዉጊያውን በተባለው መሰረት ማካሄድ እንችላለን ወይ? እቅዱን እንደገና ብታዩት ጥሩ ነው።" የሚል አስተያየትና ጥያቄ አነሳ።
ጄኔራል ፃድቃንና ወዲ መድህን የሰጡት መልስ፣
- "ሻእቢያን ካላጠፋን እኛ መኖር አንችልም። የሻእቢያ ሃይል ደካማ ነው። የኤርትራ ኢኰኖሚ ጦርነቱን መሸከም አይችልም። በተኩስ ሃይልም የበላይነት አለን። ይህ ዉሳኔም የመንግስት ዉሳኔ በመሆኑ ማንም ሊያደናቅፈው አይችልም!" የሚል ነበር።
በአሸዋ ገበታው ዙሪያ የነበሩት የበታች ኣዛዦች፣ "እቅዱ ሊሳካ አይችልም" የሚል ጥርጣሬ ነበራቸው። አሽዋ ላይ የምናየውን፣ በተግባር መሬት ላይ በትክክል መፈጸም የመቻላችን ጉዳይ ሚዛኑን ያልጠበቀ ነበር። ይህ የጥርጣሬ ጥያቄ በባድመና በቡሬ ግንባሮችም ተነስቶ የነበረ ሲሆን፣ እንደ አዲግራቱ ዉይይት "ዉሳኔው የመንግስት ነው!" በሚል ነበር የተዘለለው።
ጦርነቱ ተካሄደ።
በባድመ ግንባር ነበር የተጀመረው። ማጥቃቱን የጀመሩት ሶስት ክፍለ ጦሮች ከፍተኛ ጉዳት ስለደረሰባቸው፣ 20ኛው ሜካናይዝድ ክፍለ ጦርና አንድ ኰማንዶ ብርጌድ ተጨምሮ፣ ሌሎች ሁለት ክፍለ ጦሮች ታክለው በድጋሚ ተሞከረ። ከፍተኛ ሰብአዊና ማቴሪያላዊ ጉዳት ደርሶብን እቅዱ ሳይፈጸም ቀረ።
በባድመ ውጊያ በእቅዱ መሰረት መሄድ እንዳልተቻለ እየታወቀ፣ በፆረና በኩል ዉጊያው እንዲቀጥል ፃድቃን አዘዘ።
የዉጊያው እቅድ መግለጫ የተሰጠው እንፋራ በተባለ ቦታ ላይ ነበር። ፆረና ላይ ልዩ ዝግጅት ተደርጎ ነበር። 12,000 ያህል የትግራይ ሚሊሺያ፤ ከ5,000 በላይ አግላይ እንዲሁም ስንቅና ጥይት አቀባይ፤ በሺህዎች የሚቆጠሩ አህያና ፈረስም ለዚሁ ጦርነት ተሰልፈው ነበር። ለአንድ ሳምንት ያህል ከፍተኛ የጭንቀት ሙከራ ቢደረግም በዚያች ጠባብና ሙት መሬት የተሰለፈው ያ ሁሉ ንብረት፣ መሳሪያ፣ ሚሊሻና አግላይ፣ አህያና ፈረሶች ሳይቀር አንድ ላይ ረገፉ።
የ20ኛው ግዙፍ ሜካናይዝድ ሃይል እግሪ መከል ላይ አመድ ሆኖ ቀረ። ታንኰቹና ተሽከርካሪዎች በሙሉ አረሩ። ሻእቢያ በቀላሉ ከዛለንበሳ፣ ከአዲኳላና ከማይአይኒ አቅጣጫዎች በተጠመዱ መድፎች ሰራዊታችንን ተቀበለው። ይህ የጀግንነት ጉዳይ አይደለም። የኛ የጦር መሪዎች ወታደራዊ ቴክኒክ ከአለማወቅና ከብቃት ማነስ የመጣ ነበር። ሰራዊታችን እንዳለ ገብቶ ረገፈ። ከዚህ እልቂት የተረፉት ወደ ሁዋላ ሸሽተው ገርሁ ስርናይ እና እንትጮ፣ አድዋ ገቡ። ለአንድ ሳምንት የተሞከረው ዉጊያ በከፍተኛ ኪሳራ ከተደመደመ በሁዋላ የጦርነቱ ኣዛዥ የነበረው ጄኔራል ፃድቃን በወቅቱ ማዘዣ ጣብያ ከነበረችው እንፋራ ላይ ስብሰባ ጠራ።
ፃድቃን ስብሰባዉን ሊጀምር ሲል እንባው ቀድሞት ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ። ሁሉም ተሰብሳቢ ተያይዞ መላቀስ ሆነ።
እንፋራ የለቅሶ ቦታ ሆነች።
ፃድቃን በመጨረሻ እንደምንም ራሱን ተቆጣጥሮ ከተረጋጋ በሁዋላ ተሰብሳቢውን ለማረጋጋት ሞከረ። እንዲህ ሲልም ተናገረ፤
- "እስካሁን ብዙ ጦርነቶች መርቻለሁ። ብዙ ዉጊያዎችን ተዋግቼያለሁ። አይቻለሁ። ሰምቼያለሁ። እንዲህ አይነት መጥፎ ሁኔታ ግን ገጥሞኝ አያውቅም።"
የስብሰባው አላማ የጦርነቱን ሁኔታ ገምግሞ መፍትሄ ለመፈለግ የታሰበ ነበር። በመሆኑም ጦርነቱ ሁለት መሰረታዊ ችግሮች እንዳለበት ተሰብሳቢው ገመገመ።
"ከቦታው አስቸጋሪነት አኳያ የዉጊያ እቅዱ ስህተት ነበር። ቦታው ለመከላከል ለጠላት ምቹ ሲሆን፣ ለወገን ጦር ማጥቃት ምቹ ኣልነበረም። በቂ ዝግጅት አልነበረንም። በቂ የሰው ሃይልና የተኩስ ኣቅም አልነበረንም። በጠላት ላይ የነበረን ግምገማ የተሳሳተ ነበር። ጠላት የመሬቱን አመቺነት ተጠቅሞ ተኩስ እንደፈለገ ማዘዋወር ችሎኣል። ጠላት በቂ የሰው ሃይልና የዉግያ ቁመና ይዞ ነበር" ተባለ።
ወደ ዝርዝር ጉዳይ ሳይገባ፣ ግምገማው በዚሁ ተዘጋ። ይህን መነሻ በማድረግም ሌላ ዉሳኔ ተወሰነ።
"... በዛላንበሳና በቡሬ ተይዞ የነበረው የማጥቃት እቅድ እንዲሰረዝ። የተኩስ አቅምን ለማጠናከር ከአየር ሃይልና ከምድር ሃይል ኰሚቴ ተቋቁሞ በጄኔራል አበበ ተክለሃይማኖት መሪነት መሳርያዎች እንዲገዙ። ከፍተኛ የሰው ሃይል ምልመላ ተደርጎ በስፋት ስልጠና እንዲካሄድ። ይህን የምልመላ ስራ ደግሞ በረከት ስምኦን እንዲመራው። የስልጠና ስራውን አባዱላ እንዲከታተለው። አሁን ያሉን 12 ክፍለጦሮች በአጭር ጊዜ ወደ 30 ክፍለጦሮች እንዲያድጉ። ሰራዊቱ ማገገም እንዲችል በመከላከል ብቻ እንዲቆይ..."
እነዚህ ዉሳኔዎች ከጦርነቱ ማእከላዊ እዝ መወሰናቸውን ፃድቃን እንፋራ ላይ ከክፍለ ጦር በላይ ላለን ኣዛዦች ጠርቶ ዉሳኔዉን ነገረን።
በዚህ መመርያ መሰረት እንድንዘጋጅም ተነገረን።
በዚህ ዉሳኔ መሰረትም ለአንድ አመት ያህል ዝግጅት አደረግን። በ1992 ሚያዝያ ወር ላይም አጠቃላይ የጦርነት እቅድ ወጣ። ፃድቃን፣ ጀቤ እና አባዱላ በመቀሌ ከተማ የምክር ቤት የስብሰባ ኣዳራሽ ሰብስበው እቅዱን ገለጹልን።
- (የ1992 እቅድ ከ1991 እቅድ የሚለየው ነገር ነበረው። በ1991 ኤርትራን ጠቅልሎ የመያዝ ፍላጎት ነበረ። በ1992 ግን "አቅማችን የፈቀደውን እንዋጋለን" የሚል ሆነ። በ1991 በነበረው እቅድ፣ "ወደ ኤርትራ መሬት ስንገባ የኤርትራን ሃብትና ንብረትን እናወድማለን። ህዝቡም የሻእቢያ ደጋፊ ስለሆነ ልናምነው አይገባም!" የሚል ነበር። በ1992 እቅድ ይህ በግልጽ አልተቀመጠም። "ህዝቡ የሻእቢያ ደጋፊ ስለሆነ ከፍተኛ ጥንቃቄ እናደርጋለን" የሚል አረፍተነገር ግን ነበረበት።)
በ1992 ሚያዝያ መጨረሻ ግንቦት መጀመሪያ ላይ ጦርነቱ በባድመ ግንባር ተጀመረ። በዉጊያው ከፍተኛ ጉዳት ቢደርስብንም እስከ ባረንቱ መዝለቅ ቻልን። ሻእቢያ ሰራዊቱን ይዞ ስልታዊ ማፈግፈግ እያደረገ ስለሆነ፣ የጠላት ኪሳራ አነስተኛ መሆኑን፣ ይልቁን ወደ መግደያ ወረዳ እየሳበን መሆኑን አዛዦች ሃሳባቸውንም ለፃድቃን ያቀርቡ ነበር። በአንጻሩም ወደ ኤርትራ ምድር እየዘለቅን በገባን ቁጥር ከዋና ማዘዣችን እየራቅንና የድርጅት ድጋፍ እያጣን እንሄድ ስለነበር፣ የሚያዋጣን አማራጭ ወደ ሁዋላ መመለስ ሆነ።
ከባድመ ግንባር ዉጊያ በኋላ የባድመ የዉጊያ ችግር ሳይገመገም በችኮላ በራማ፣ በፆረና እና በዛላንበሳ ግንባሮች በተመሳሳይ ጊዜ ማጥቃቱ ተጀመረ።
የነበረው ግምገማ፣
- "በባድመ ዉጊያውን ቀድመን ስንጀምር ሻእቢያ ብዙ ሃይል ወደ ባድመ ሊያመጣ ስለሚችል ሌሎች ግንባሮች በሰው ሃይልና በመሳርያ አቅም ይሳሳሉ" የሚል ነበር።
እንደታቀደው ግን አልሆነም።
በመሆኑም በእነዚህ ሶስት ግንባሮች በተመሳሳይ ሰአት የተጀመረው ዉጊያ በእቅዱ መሰረት ሳይሳካ ሲቀር ባጭር ጊዜ ዉስጥ ሌላ የዉጊያ እቅድ ተዘጋጀ።
- "በቡሬ ግንባር አሰብ ከተማን መያዝ ከቻልን የሞራል ግንባታ እናገኝበታለን" የሚል አሳብ መጣ።
አሰብን ለመያዝ ያደፋፈረው ዋናው ምክንያት፤
- "ጠላት በቡሬ ግንባር እንጠቃለን ብሎ ስለማይገምት በቂ ዝግጅት አይኖረውም። ከጅቡቲ መንግስት ጋር ስለተነጋግርን ሃይላችን በቀላሉ በጅቡቲ መሬት ማስጠጋት ለዉጊያም ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንችላለን" የሚል ነበር።
በዚሁ መነሻና ገለጻ ላይ በርካታ ጥያቄዎች ተነስተው ነበር። ለምሳሌ የ36ኛ ክፍለጦር አዛዥ ኮሎኔል መሃመድ ኢሻ፣ የ39ኛ ክፍለጦር አዛዥ ኮሎኔል ወንደሰን ተካ፣ የ14ኛ ክፍለጦር አዛዥ ኮሎኔል ወዲ አባተ ያነሱት ጥያቄ፣
- "እስካሁን ባደረግናቸው ዉጊያዎች ሁሉ ሻእቢያን ከያዘው ምሽግ እንዲያፈገፍግ አደረግነው እንጂ፣ በእቅዳችን ያስቀመጥነውን ተግባራዊ አላደረግንም። ለዚህም ብዙ ኪሳራ ከፍለንበታል። በኪሳራው ምክንያትም የጦሩ ሞራል መጥፎ ሁኔታ ይገኛል። የቡሬ አየር ጠባይም ሆነ መሬቱ በጣም አስቸጋሪ ነው። በቂ የሎጂስቲክ ዝግጅት የለንም። ድንገተኛ ድል እናገኛለን ብለን ድንገተኛ ሽንፈትም ሊከተል ይችላልና ቢታሰብበት? ስለ ጠላት እስካሁን የተናገራችሁት ሁሉ ልክ አልሆነም። እና አሁንስ ምን ያህል ትክክል ናችሁ?" የሚል ጥያቄ አንስተው ውይይት አደረግን።
በመጨረሻ አሳማኝ ነጥቦች ባይቀርቡም፣ የማይቀየር የመንግስት ዉሳኔ ነው ተብሎ "አሰብን መያዝ!" የሚለው እቅድ ፀደቀና ዉጊያው ተካሄደ። ዉጊያው ለአምስት ተከታታይ ቀናት የተካሄደ ቢሆንም፣ እንዲያዉም ከሌሎች ዉጊያዎች ሁሉ የከፋ ዉጊያ ሆነ። ሻእቢያ በበርካታ ዉጊያዎች የሚጠቀምበትን ወደ መግደያ ቦታ እያስገባ የመምታቱን ስልት ቡሬ ላይም ስለ ደገመው ከፍተኛ እልቂት ተቀብለን አሰብን የመያዙ እቅድ ከሸፈ....
"... የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ሲነሳ ከሁሉም እንቆቅልሽ የሚሆንብኝ የፆረናው ዉጊያ ነው። እንደገለጽኩልህ ከፍተኛ መስዋእትነት ከፍለንበታል። ማነው ተጠያቂው?
በወቅቱ ግን የግድ አንድ አካል ተጠያቂ ማድረግ ስለነበረባቸው፣ አምስት ኦሮሞ መኮንኖች እንዲወነጀሉ ተደርጎአል።
"የዉጊያው እቅድ በኦነግ በኩል ለሻእቢያ አሳልፋችሁ ሰጥታችሁዋል" የሚል ክስ ቀርቦባቸው፤ ኮሎኔል ብራ የተባለች ሴት ጢጣ ካምፕ ዉስጥ ስታስገርፋቸው ሰነበተች።
ኦሮሞ መኮንኖች ድብደባው ሲበረታባቸው፣ "አድርገናል፤ ፈጽመነዋል" ብለው አመኑ።
"ግንኙነታችሁ በማን በኩል ነበር?" ተብለው ሲጠየቁ፣ "አባዱላ" ሲሉ መለሱ።
አባዱላ ግን ወያኔን እንደማይከዳ ይታወቅ ስለነበር ምርመራው እዚያው ላይ ቆመ።
በኮሎኔል ብራ ግርፍያ ከተፈጸመባቸው ከፍተኛ ኦሮሞ መኮንኖች አንዱ በድብደባ የዘርፍሬው የተኮላሸ ሲሆን፤ ሌላው ፓራላይዝድ ሆኖአል። መኮንኖቹ በህይወት ያሉ ሲሆን፤ የወያኔ ስርአት ለሚፈጽመው አሰቃቂ የመብት ጥሰት ህያው ምስክር ሆነው የተፈጸመውን ሁሉ ህግ ፊት የሚገልጹበት እለት ይመጣ ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። እነዚህ ኦሮሞ መኮንኖች ላይ የደረሰው አሰቃቂ ግፍ "በፆረናው እልቂት ማን ይጠየቅ?" የሚለዉን ጥያቄ ከህወሃት ዝሆኖች ሰፈር ለማውጣትና አጀንዳውን ለመዝጋት እንጂ መኮንኖቹ ንጹህ መሆናቸዉን ፃድቃን፣ ስዬ እና መለስ ያውቁ ነበር።
✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄✄
“……የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ለጦርነቱ መሪዎች የሐብት ምንጭ ሆኖ ማገልገሉን ማየት ችያለሁ፡፡ በጦርነቱ ሰበብ በተዘረፈ ሐብት የሕወሃት ጄነራሎች ሚሊየነር ሆነዋል፡፡ ፃድቃን፣ ጀቤ፣ ብርሃነ ነጋሽ፣ ገዛኢ አበራ፣ አባዱላ ገመዳ፣ አበባው ታደሰ፣ ባጫ ደበሌ፣ ታደሰ ወረደ፣ ሰዓረ መኮንን፣ እና ሌሎችም ጄነራሎች በአዲስ አበባ በባህርዳርና በመቀሌ ያስገነቡት ቪላና ፎቅ ውበቱ አይንን ያፈዛል፡፡ የቤት እቃዎቻቸው፣ ምንጣፎቹ፣ መብራቶቻቸውና ኮርኒሶቻቸው በውድ ዋጋ ከአውሮፓ እየተጫኑ የመጡ ናቸው፡፡ የመጨረሻውን ቴክኖሎጂ እየተጠቀሙ ለቪላዎቻቸው ማሞቂያና ማቀዝቀዣ ተክለውላቸዋል፡፡ ከዚያ ሁሉ እልቂት በኋላ ጄነራሎቹ በቀጥታ ወደ ሃብት ፉክክር ነው የገቡት፡፡ የሚፈሰው ገንዘብ በጦርነቱ ወቅት የተዘረፈ ነው፡፡ …..”
መፅሀፍ: የደራሲው ማስታወሻ፣ በተስፋዬ ጋዳ ገብረአብ

-
Revelations
- Senior Member+
- Posts: 34573
- Joined: 06 Jan 2007, 15:44
Re: የተስፋዬ ገብረአብን ተራ ቅጥፈት ፎቶው ያጋልጣል
N° 949
12/05/2001
ETHIOPIA
The Ripple Effect of TPLF’s Crisis
The crisis within the Tigray People’s Liberation Front (TPLF), the hard core of the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF), is having side effects in several sectors of society. The first repercussions touched the armed forces (ION 948), where the most notable example was last week’s refusal, by Brigadier General Tadesse Berhe, to attend an officers’ meeting presided by Meles Zenawi, during which the prime minister denounced the positions of the dissident group expelled from the TPLF’s central committee.
The brigadier general is said to have explained his decision by pointing out that the army ought to remain removed from any and all political influence. Another repercussion is the closing down of the TPLF’s Efoyta daily, with only the magazine of that name remaining with the party. Tesfaye Gebreab, Efoyta's editor-in-chief, recently left Ethiopia for Kenya without informing his colleagues.
A former army lieutenant for former President Mengistu Haile Mariam, Tesfaye Gebreab was made a prisoner by the TPLF, then a guerilla movement, after suffering wounds in Debre Tabor, Gondar.
He subsequently joined the TPLF, worked for the party, and wrote a book called "Yeburka Zimta"(The Silence of Burka), a fictional account a bit too close to reality since it led to accusations of his having wanted to stir up passions between the Oromo and the Amhara communities.
Considered close to the TPLF dissidents led by Grebu Asrat and Alemseged Gebre Amlak, Tesfaye Gebreab had not been allowed to join a meeting of TPLF leaders held in Addis Ababa a few weeks ago.
After his departure to Kenya, the Ethiopian leaders claimed they found the newspaper’s coffers empty, with a debt of almost 500,000 Birrs ($1 = 8 Birrs) in a local bank.
According to certain sources, Tesfaye Gebreab has already contacted the Eritrean embassy in Nairobi and may already have found refuge in Asmara .
