Page 1 of 1

>> ሹክ ለሚል መልዕክት<< ግማሹ ህገወጥ አጣሪ ፣ ግማሹ ተፈናቃይ!

Posted: 29 Apr 2020, 11:09
by kibramlak
>> ሹክ ለሚል መልዕክት<< ግማሹ ህገወጥ አጣሪ ፣ ግማሹ ተፈናቃይ!
ለህገ-ወጥ መሬት አጣሪዌች አይኑ የተደፈነ መንግስት ፣ ምነው ዝም ብለው ለሰፈሩት ሰላማዊ እና ሰርቶ አደር ዜጎች አይኑ ተጎልጉሎ ጡንቻው ፈረጠመ??? እስኪ መድልኦ ከሌለ በመሬት እስተዳደር የተሰገሰጉትን የኦሮሞ እና ኦሮሞ ቀመስ ሌቦች ጡንቻውን አያሳይም??? ይኸው አሁን በአዲስ አበባ ስንት ቦታ በጉልበት እየታጠረ (ከመሬት አስተዳደር ሰወች ጋር በሙስና በመቆራኝት) ይገኛል፣፣ የጀሜ ለቡ ድራማ እኮ አባይን በጭልፋ ነው፣፣

የኦሮሞ ጠባብ ፅንፈኞች መታወቂያ መቀራመቱ ሲነቃባቸው፣ መረን የለቀቀ እና አን ያወጣ የመሬት ዘረፋ ተያይዘውታል፣፣

ነገሩ እሚካሄደው እንደዚህ ነው፣

1ኛ፣ በፊት ባለመሬት ነን የሚሉ ወይም "ጊዜ የሰጠኝ ጉልበተኛ" ነኝ እሚል ኦሮሞ ሰው ያልሰፈረበትን ወይም ካርታ ያልወጣለትን ቦታ እንዲሁም ለመዝናኛ ይሆናል ተብሎ የተተወን ቦታ ግጥም አድርጎ ያጥራል፣፣ ከዛ ሶስት ቁልፍ ሰወች ይፈልጋል ፣ ደላላ ፣ ገዥ፣ እና የመሬት አስተዳደር (ዋናው ወይም ምክትሉ በዋናው እውቅና)፣ ስምምነቶች በሁለት ይከፈለሉ፣ በገንዘብ ወይም በአይነት፣፣ የመሬት አስተዳደር ሰው እስከ ግማሽ ሚልዮን ብር ሲቀበል፣ ሻጭ ደግሞ (ህገ-ወጥ አጣሪው ማለቴ ነው) ወይ ግማሹን ቦታ ገዥ ካርታ (የውሸት) እንዲሰራለት ያደርጋል ወይም እስከ 50% የቦታውን ዋጋ ይወስዳል፣፣ ደላላው ከመቶ እስከ አራት መቶ ሺ ብር ይገጫል፣፣ በዚህ ስምምነት አስር ምልክት የተገመተ ዋጋ፣ ህገ ውጡ ሻጭ እስከ አምስት ሚልዮን ሲያገኝ፣ ደላላው እና የመሬት አስተዳደሩ ሰው አንድ ሚልዮን ሲወስዱ፣ ገዥ (እያወቀ የገባበት ) ቦታውን በ ስድስት ሚልዮን በማግኝት አራት ሚልዮን ያተርፋል፣፣ በብር ካልሆነ ግማሽ ቦታውን ለጉልበተኛው አጣሪ በራሱ ወጭ ህገ-ወጥ ካርታ በማሰራት ግማሹን ቦታ ይተዋል ማለት ነው፣፣ እዚህ ላይ የግዥ ወጭ ለደላላ እና ለመሬት አስተዳደሩ መክፈል ነው፣፣ ያ ለግማሽ ቦታ ካርታ ያገኘው ለሌላ ሰው አሳልፎ ይሸጣል ማለት ነው፣፣

ይህ ጉድ ባለበት ነው እንግዲህ እነኝህ ሌቦች ዛሬ ዘመናዊ ፒካፕ ይዘው ሲንቀባረሩ፣ አሁን መንግስት ነኝ ባይ በደካሞች ላይ የዘመተው፣፣ እነኝህ ሰፋሪወች ህጋዊ ናቸው ማለቴ ሳይሆን አሁን ግን ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ለዋናወቹ ህገወጥ የመሬት ነጋዴዎች እና ላስፈፃሚወቻቸው ነው መሆን የነበረበት፣፣