Page 1 of 1

አስደንጋጭ ነው!!

Posted: 26 Apr 2020, 16:19
by Hameddibewoyane
ሃቅ፣ ፍትህና ሰላም ወዳዱ የትግራይ ህዝብ የህወሓት መሪዎችን በሰላማዊና በሰለጠነ መንገድ ቁጭ አድርጎ መገምገምና መጠየቅ እንደሚጀምር መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚጠብቀው ክስተት ነው፤ ይህ ስልጡን የታሪክ ክስተት እንዲፈፀምም በአንዳንድ ሃላፊነት የጎደላቸው አካላት ይፈጠሩ የነበሩ ተንኳሽ አጀንዳዎች እንዲቆሙ ስንወተውት ቆይተናል። ሆኖም ግን ህዝባችን በቅርቡ የህወሓት መሪዎችን በሰላማዊ መንገድ ለጥያቄ ማቅረቡን ይጀምራል ያልነው የፀና እምነታችን በአመፃ መፈፀም መጀመሩ አስደንጋጭ ክስተት ሆኖብናል።

በዚህ ሳምንት መጨረሻ በመቐለ ከተማ በ4 የህወሓት ከፍተኛ ካድሬዎችና የጥቅም ተጋሪዎች፦ 1ኛ፤ ዶ/ር ፋና ሓጎስ (የትግራይ ክልል የፍርድ ቤቶች ፕሬዝዳንት) 2ኛ፤ ወ/ሮ ሰብለ ካሕሳይ (የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ኣባል) 3ኛ፤ የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸው እንዳይጠቀስ ከፍተኛ የመረጃ አፈና ያካሄዱ አንድ የህወሓት አፈ-ቀላጤ 4ኛ፤ አንድ የህወሓት ባለስልጣናት የጥቅም ተጋሪ የሆኑ ልማታዊ ባለሃብት በድምሩ 4 የህወሓት ከፍተኛ ካድሬዎች ላይ ኣካላዊ ጥቃትና ዘረፋ መፈፀሙ ተረጋግጧል።

እኛም ህዝባችን በህወሓት መሪዎችና በስርዓቱ ላይ ፍፁም ተስፋ ቆርጦ ወደ ሃይል እርምጃ መግባት መጀመሩ የህዝባችን ጨዋነትና ሰላማዊነት ላይ መጥፎ ጥላ እንዳያጠላ ስጋት ገብቶናል።

ለዚህም የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ጉዳዩን በከፍተኛ ትኩረት እንዲያጤኑትና በሰላማዊ መንገድ ስልጣን እስከማስረከብ የሚደረስ ሰላማዊ ድርድር ከወዲሁ እንዲጀመር በፅኑ እናሳስባለን።

Nebiyu Sihul Mikael



Re: አስደንጋጭ ነው!!

Posted: 26 Apr 2020, 16:44
by EthioRedSea
Who are you to challenge TPLF? TPLF will be replaced only by election if the people of Tigray do not vote them again. TPLF has committed mistakes, but it has contributed more to Ethiopia and Tigray than the silly mistakes they committed, one of which is landlocking Tigray or Ethiopia and forcing Ethiopians to pay more than 28 billion dollars to Djibouti for port services. This money should have been given to Eritrea by using the ports in Massawa or Asseb.

Any Eritrean who is a member of TPLF is Tigrayan-Ethiopian. TPLF leaders are not Shaebya agents. They could be Tigrayans from Eritrea or half cast. Eritreans are Tigrayans and can be members of TPLF or leaders of Tigray communities if they have the qualification or prove to be good leaders.