Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3978
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

የወልቃይት ጉዳይ ለዘራፊዋ ህወሓት ብዙም አልተመቻት!!!!

Post by Ejersa » 22 Apr 2020, 13:56



የታላቋ ትግራይ ህሎመኞች የአማራን እርስት ወሎቃይና ራያን ወደ ትግራይ ካካለሉ 28ኛ አመታቸው እየተገባደደ ነው። የአማራን እርስት ወልቃይት እና ራያን ብቻ ሳይሆን ሰፋፊ የአፋር ግዛቶችን አቅፎ የያዘ ካርታ አሁንድ ድረስ በህወሓቶች ዘንድ እንደተጨበጠ ነው። በእርግ ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ የሐገር ሐብት ዘርፎ በቃኝ ያላለ ዘራፊ ቡድን፣ ከአማራው እርስት ወልቃይት እና ራያን ዘረፈ ቢባል ብዙም አይደንቅም። ምክናየቱም ህወሓት ወያኔ ባለፉት 27 አመታት ከዘረፈው የሐገር ሐብት ጋር ሲነፃፀር ይሔ በጣም ዝቅተኛው ነው። ለአማራው ግን የህልውናው ጉዳይ ነው የእርስት ጉዳይ ነው። ወልቃይት እና ራያ ለባለቤቱ የአማራ ህዝብ እስካልተመለሰ ድረስ በአማራ እና በትግራይ ህዝብ መካከል ዘላቂ ሠላም መቸም ሊፈጠር አይችልም። ይሄን ህወሓት በደንብ አድርጋ ታውቃለች። ለዛም ነው ወልቃይት እና ራያ ለባለቤቱ የአማራ ህዝብ እንድመለስ የማትፈቅደው። ግን ይዘገይ ይሆናል እንጂ ወልቃይትም ሆነ ራያ ለባለቤቱ አማራ ተመላሺ ነው።

ህወሓቶች የውሸት ታሪክ መደርደር ቀደምት የደደቢት አባቶቻቸው ያስተማሯቸው አጋንቶች ያወረሷቸው የማይለቅ አባዜና ለብዙ አመታት የተማሩበት ህይዎት ብለው የኖሩበትና እየኖሩበት ስለሆነ፣ የወልቃይት እና የራያ ጉዳይ ደም ሳያፋስስ ለባለቤቱ የሚመለስ አይመስልም ከወቅቱ የህወሓት አቋም አንፃር ሲታይ።
ትህነግ ወያኔ እራሱን ሙሉ በውሸት የኖረ ከመሆኑም በላይ ሰፊውን የትግሬይ ህዝብ በዚህ ክፉ በሺታ እየለከፈው ይገኛል። ህወሓትን ማን አደብ ያስይዘው? መቸም ህወሓት በእራሱ ፍላጎት ወደ እውነት የሚመጣና ከእውነት ጋር የማታረቅ ድርጅት እንዳልሆነ እንኳን ሰው ሰይጣኖችም ያመኑበት ጉዳይ ነው።

ህወሓት ጤነኛ እና አስተዋይ ቢሆን ኑሮ ለሱዳን የኢትዮጵያን መሬት አሳልፎ ከመስጠት ይልቅ፣ ከሱዳን ተጋፍቶ የኢትዮጵያን መሬት አስክብሮ ስለሌላው ጉዳይ ከአማራው ህዝብ ጋር ለድርድር ይቀርብ ነበር። ዛሬ ከእነሱ በላይ የተዋረደና የወደቀ የለም። ግን ይሔንን ውድቀታቸውን እና ውርደታቸው ለመሸፈን ማዕከላዊ መንግስትን ሳይቀር በጦር ነጋሪት ጉሰማ አጠንክረው እያስፈራሩ ነው።
ከ1983 ዓ/ም ጀምሮ በአጋጣሚ ያገኘውን ስልጣን ተጠቅሞ በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ብድር በመበደር ዘመኑ ያፈራቸውን ወሳኝ ወሳኝ የጦር መሳሪያዎች በየግዜው ትግራይ ክልል አከማችቷል። ህወሓት የወልቃይት እና የራያን ጉዳይ መመለስ አለብኝ ብሎ የሚያምነው በመሳሪያ ነው። ማዕከላዊ መንግስትም ሆነ መሬቱን የተዘረፈው የአማራ ህዝብ ይሔንን እውነታ በደንብ ጠንቅቆ ያውቃል። ስሰዚህ ሁሉም ወገን ህወሓትን የሚያንበረክክበትን ኃይል እስከሚያገኝ የህወሓትን የጦር ጉሰማ ሰምቶ ባልሰማ ማለፍን መርጧል።
ግን ደግሞ ማዕከላዋ መንግስቱ ቸልተኝነትና ለውሳኔ ያለመፍጠን ሁኔታ እንጂ፣ ህወሓትን ከወሰነባት በሳምንታት ውስጥ ግብአተ መሬቷን ማስፈፀም ይችላል። በዚህ ማንም ጥርጥር የለውም። ግን መንግስት የትግራይን ህዝብ በማይነካ መልኩ ብቻ ህወሓትን ለማንበርከክና ለህግ ተገዥ ለማድረግ የወሰነ ይመስላል። እስከዚያው ግን የህወሓት ቀረርቶና ፉከራ ጎረቢት አማራን እየረበሸ ነው።
አማራው መሬት ላይ ቤትና ምሺግ ሰርታ ህወሓት "አማራ ጥላቴ ነው" የሚለውን ማኒፌስቷን በትግራይ ክልል በዩኒቨርስቲ ሳይቀር ለትግራይ ተማሪዎች በትምህርት መልኩ ታስተምራለች ትሰብካለች። ይህ ብቻ ህወሓትን በአለም አቀፍ ህግ ያስጠይቃታል። ግን ማን ለሚመለከተው አካል አቤቱታ አቅርቦ?

ህወሓቶች እንዘጭ ብለው ወድቀውም የአማራን መሬት ወልቃይት እና ራያን ከትግራይ ጋር አካተው ካርታ በማስተዋወቅ ላይ ይገኛሉ።
በበሬ ወለደ ታሪክ የሚፅፉ፣ በአጋጣሚ ያገኙትን ስልጣን ለሐሰት ፕሮፑጋንዳ የሚያውሉ፣ የራሳቸውን ህዝብ የማሞኘት ምኞት በደንብ ስለሚችሉበት የትግራይ ህዝብም ሊከላከላቸው እና ከስህተታቸው ሊያቆማቸው አልቻለም።

ህወሓቶች በአሁኑ አቋማቸው በተለይም ከላይ በርዕሴ እንደጠቆምኩት "የወልቃይት ጉዳይ" የሚለው መጽሐፍ ታትሞ ለንባብ ከበቃ ጀምሮ እንኳን ወልቃይት እና ራያን ሊመልሱ ይቅርና ጭራሺ ለሌላ ወረራ እና ለሌላ ፉከራ እራሳቸውን እያነሳሱ ነው።

መፈክራቸውም እንዲህ ነው።
"እኛ የአሉላና የሃየሎም ልጆች እጃችን ላያ ያለው ግዛታችን ሊሸረፍ ይቅርና ሌሎች የቀሩት የምንፈልጋቸው መሬቶችን ከአማራው ለመውሰድ ጉዞ ጀምረናል። ድንበራችን ከአልውሃ እስከ ሊማሊሞ ነው።" የሚል ነው።

እኛ ደግሞ እንላለን አይደለም ወልቃይት እና ራያን የአማራን መሬት ቀርቶ ከጭቁኑ የአፋር ህዝብ ወደ ትግራይ የተካለሉ ሰፋፊ የአፋር ግዛቶች ጭምር ለባለቤቱ የአፋር ህዝብ ተመላሺ ነው።
ህወሓት ሆይ ፉከራና ዛቻ ሚኒልክ ቤተ መንግስትም ሆነሺ አልበጀሺም!