Please wait, video is loading...
ዘመን ተሻጋሪ ድንቁርና የወለደው የድኩማኖች ፉከራ!
የትግራይን ህዝብ ለ2 አመት ያህል አብሬው ባልኖር ኖሮ፣ ህወሓት ማለት በትግራይ ህዝብ ዘንድ ወራዳና ከሃዲ ተብለው የተገፉ የባንዳ_ልጆችና የልጅ ልጆች ስብስብ መሆኑን ጠንቅቄ ባላውቅ ኖሮ፣ የኢትዮጵያ እትብት አክሱም ላይ የተቀበረ እንደመሆኑ መጠን ትግራይን ከኢትዮጵያ መገንጠል የሁሉንም ኢትዮጵያዊ አካል ለሁለት የመሰንጠቅ ያህል ከባድ ባይሆን ኖሮ፣ የኢጣሊያን ፓስታ መብላትና ከረንቡላ መጫዎት ሀገራዊ ማንነት (National Identity) ይሆናል በሚል ቅዠት የተገነጠሉት ኤርትራውያን ተመልሰው የኢትዮጵያ ዕዳ መሆናቸውን ባላውቅ ኖሮ.... ትግራይን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል፣ ኢትዮጵያን ከትግራይ ለመነጠል በምድር ላይ የማላደርገው ነገር አይኖርም ነበር። ከላይ የተጠቀሰውን እውነታ ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰው ትግራይን ለመገንጠል መሞከር የመጨረሻ ቂልነት፣ ባዶ ቀረርቶ፤ የተረሱ ዕለት ሰሚ ጆሮ ለማግኘት የሚነገር #የቱልቱላዎች ቱሪናፋ እንደሆነ ይገነዘባል። በመሆኑም አስታወሽ ባጣ ቁጥር ትግራይን ስለመገንጠል አይናገርም። ይሄን የሞኝ ጨዋታ የሚጫወቱት ህወሓቶች ብቻ ናቸው። እነሱ ደግሞ ከኢትዮጵያ ለመገንጠል 17 አመታት "ታግለው ካሸነፉ" በኋላ ላለፉት 27 አመታት ኢትዮጵያ ውስጥ ቁጭጭጭ ብለው ፀጉራቸውን ሲያበጥሩ የኖሩ ድኩማኖች ናቸው። ባለፉት 44 አመታት ያላደረጉትን ነገር ከዚህ በኋላ 24/7 ቢያወሩት አያደርጉትም፣ አይፈልጉትም፣ አይችሉም። ቲሽ.....ምድረ ቶርቶራ‼