Page 1 of 1

my best Ethiopian movies

Posted: 26 Mar 2020, 10:26
by Abaymado
የፊልሞቹ አቀማመጣቸው አሪፉን በደረጃ ለማስቀመጥ ሳይሆን ደጋግሜ ያየሁትና ከሌሎቹ የተለየ የመሰለኝን ነው::

ቀዝቃዛው ጦርነት

ይህ ቪድዮ እፀ ህይወት አበበ የተጫወተችበት ነው:: እፀ ሕይወት ቀላል የማይባሉ ጥሩ ጥሩ ፊልሞች ላይ ተሳትፋለች:: ግን በጣም የምታበዛው ይመስለኛል:: ባል አግብታ ሶስት ልጅ ብትወልድም :ከባሏ ጋር እንደተፋታች ነው ሲነገር የነበረው::
እዚህ ፊልም ላይ አንድ የሚገርም አነጋገር ዋናው ተዋናይ ተናግሯታል "አንቺ ገና ለሚስትነት ብቁ አይደለሽም " ነው ያላት:: ይህ ለእሷ ምን ይነግራታል?

በተረፈ ግን ጥሩ ትሰራለች:: ልጁም የሚመች ነው::



Re: my best Ethiopian movies

Posted: 27 Mar 2020, 07:07
by Abaymado
ሰምና ወርቅ ፊልም

ይህ ፊልም በጣም ደስ የሚለኝ ፊልም ነው:: ፊልሙ እንደ በፊቱ youtube ላይ በቀላሉ ስለማይገኝና ከ youtube ላይ ስለተነሳ ይህንን ቪድዮ ማግኘትከበድ ይላል::

የዚህ ፊልም ደራሲ እና ዳይሬክተር ቅዱሳን ታደሰ ናት:: በዋና ተዋናይነት ይህንን ፊልም ተጫውታዋለች:: አሪፍ ነው:: የሚያሳዝነው ግን ሌላ የቅዱሳንን ሥራ ወይም ሌላ ፊልም ላይ የተወነችውን አላየሁም:: ግን በቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማ ላይ ዋና አዘጋጅ ናት ተብሏል::

ከዚህ ሌላ በዚህ ፊልም ላይ ዋና ተዋናይ ሆኖ የሰራው አማኑኤል በጣም የሚመቸኝ ተዋናይ ነው:::



Re: my best Ethiopian movies

Posted: 02 May 2021, 06:21
by Abaymado
This is entertaining Ethiopian movie I got right now, you will enjoy it.



by the way, all the movie I posted in this post aleady removed, I will try my best to retrieve it back.

here it is one of the movies removed above:

"ቀዝቃዛው ጦርነት "