Page 1 of 1

የኮሮና ወረርሽኝ መድሃኒት ጾም ነው

Posted: 22 Mar 2020, 01:45
by Horus
ምን ማለቴ ነው?

ባሁን ሰዓት ባለም ሁሉ መፍትሄ ሆኖ በተግባር ላይ እየዋለ ያለው 'ማህበራዊ መራራቅ' ወይም ሶሺያል ዲስታንስ የተባለው መድሃኒት ነው።

ይህን ማለት ከሰው ተገልሎ ለብቻ መሆን፣ ለብቻ መብላት፣ ለብቻ መስራት ማለት፣ ለብቻ መተንፈስ ማለት ነው።

ትልቅ እምነትና የፈሪሃ እግዚአብሄር ስነ ምግባር የተላበሱት ኢትዮጵያዊያን ይህን ለሺ ዘመናት የኖሩበት ካልቸር ነው ።

እሱም ጾም፣ ከሁሉም ነገር መገለል ነው ።

እሱም ሱባኤ፣ ከአለም ሁሉ ተገሎ፣ ተለይቶ መጸለይ ማለት ነው ።

እሱም ዪጉባ ዬብቻ መሆን ማለት ነው ።

እሱም ጦማ መሆን ማለት ጦማ ወኩን ማለት ነው።

ጦመ፣ ጾመ ፣ ጉበኛ ሆነ፣ ብቸኛ ፣ጾመኛ እንዲል !!!

Re: የኮሮና ወረርሽኝ መድሃኒት ጾም ነው

Posted: 23 Mar 2020, 00:22
by Horus
በሰረቱ እንዲህ ባለ ግዜ የሁሉም ቤተስኪያን አማኞች አብረው እግዚኦ እያሉ ምህላ ያረጋሉ፣ ይማለዳሉ ። ግን አሁን ያን ማድረግ ይበልጥ በሽታውን ስለሚያስተላልፈው ጸሎትችን በጾም፣ ለብቻ፣ ዬጦማ መሆን አለበት !