አረመኔው የአገር ውስጥ ደህንነት ሃላፊ የነበረው ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል!
Posted: 15 Mar 2020, 18:29
የአገር ውስጥ ደህንነት ሃላፊ የነበረው ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል ከበረሃ ጀምሮ የህወሀት ታጋዬች "ከሴት ጋ ተገኙ" በሚል ሞት ሲወሰንባቸው ግድያውን በ"ደስታ" ይፈፅሙ ከነበሩት አንዱ ነው! ከሰሞኑ ከBBC አማርኛ ፕሮግራም ያደረገውን ቃለምልልስ ስመለከት ውስጤን አመመኝ፣ አዘንኩ! በእሱ መሪነት ደህንነት ቢሮው ስለፈፀመው ግድያና ስቃይ ሲጠየቅ " እኔ እስከማውቀው ድረስ የደህንነት ተቋሙ የዜጎችን ህይወትና ንብረት ለመጠበቅ በታታሪነት ይሰራ የነበረ ተቋም ነው" ብሏል። እነወ/ስላሴ የፈፀሙት ግፍ እስር ቤት ገብተውም ያልተማሩና ያልተፀፀቱ እንደሆነ ይህ የሚያሳምም መልሱ በግልፅ ያስረዳል! ወ/ስላሴ ያሰቃያቸው ወገኖች እንዳሉ ሆነው ለስድስት ወር ያልጋ ቁራኛ ያደረገኝ ወ/ስላሴ እንደሆነ እኔ ምስክር ነኝ! አንድ ጊዜ ካዛንችስ በሚገኘው የደህንነት ግቢ ትልቅ ዛፍ ስር የደህንነት አባላት አስቸኳይ ስብሰባ ተቀምጠዋል። ወ/ስላሴና ሃይላይ የሚባል ይደሰኩራሉ። ፈንጠር ብሎ ጣራ የሌለው በቆርቆሮ የታጠራና ወደ ውስጥ ተቆፍሮ የተዘጋጀ ማሳቃያ አለ። አሞራ ዝቅ ብሎ ስጋ መስሎት ያነሳውና በደም የተጨማለቀ ጨርቅ በዛፉ ስር በተሰበሱ አባላት ላይ ሲጥለው አባላቱ ተገርመው ተያዩ። አንዳንዶቹ ያ የተከለለ ቦታ የነሃይላይ የግል ማሰቃያ መሆኑን አያውቁም ነበር። "ኦነግ" የተባሉ የኦሮሞ ተወላጆች ነበር በደም እየታጠቡ ይሰቃዩ የነበሩት። ወ/ስላሴ ያደረሰብኝ ቁስል ይበልጥ ያሳመመኝ ይህ አረመኔያዊ የክህደት መልሱ ነው! በአረብ አገር ኤምባሲ ተመድቦ የሚገኘው ሀይሌ የተባለው ፋሺስት ለምን እንደተመደበ ግራ ያጋባል!
(በፎቶው ፋሺስቱ ወ/ስላሴና ባደረሰብኝ ከባድ ድብደባ ለስድስት ወር ለአልጋ ቀራኛ ሆኜ)
አርአያ ተ/ማርያም


(በፎቶው ፋሺስቱ ወ/ስላሴና ባደረሰብኝ ከባድ ድብደባ ለስድስት ወር ለአልጋ ቀራኛ ሆኜ)
አርአያ ተ/ማርያም


