መብራት ኃይልን ሃይ የሚለው የለም እንዴ ? በጣም መጥፎና ግዜውን ያልተከተለ መስሪያ ቤት ነው: መሸጥ አለበት!
Posted: 14 Mar 2020, 06:25
መንግስት የለም እንዴ? መጠኑን አለፈ :: መብራት ኃይል በጣም የተለየ መስሪያ ቤት ነውማለት ይቻላል:: መስርያ ቤታቸው ራሱ ንፅህና የለውም:: ደምበኛ እንደተጉላላ ነው:: የመብራት ሂሳብ ተመን ራሱ እያሳሳቱ ይዘግባሉ: ደንበኛ አቤት ቢል የሚሰማው ለማግኘት ወር እንኩዋን አይበቃም:: በቃ እዛ ተገትሮ መዋል ነው::
ብር ለመክፈል ሰዉ ተገትሮ መዋል ግዴታው ነው::
እዚህ ቪድዮ ላይ የሚታየው : አቤቱታ ለማቅረብ አራት ኪሎ የተሰለፈ ሕዝብ ነው:: የሆነ ችግር ገጥሞት አቤት ለማለት ፈልጎ ነው:: ካሜራው የተነሳበት ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ተኩል ቢሆን ነው:: ህዝቡ መቼ እንደመጣ ራሱ አይታወቅም:: ከጠዋቱ አስራአንድ ሰዓትም ሊሆንም ይችላል::
ከዛስ ምን ሆነ?
ሱፍ የለበሰ ጠቆር ያለ ሰው መጥቶ :"password ስለሌለ ዛሬ ምንም አንሰራም: ሂዱ " ሲል ህዝቡ ሲንጫጫ ነው የሚያሳየው:: ሌሊት መጥቶ የተሰለፈው ምን ይሁን? ነገስ ምን ያገኛል? ይህ በየቀኑ እንዲህ የተለመደ ነው::
መብራት ኃይል የህዝቡን አቤቱታና ችግር ለማዳመጥ የተቀመጠው ሰው አንድ ነው:: ለዛውም እስከ ስድስት ሰዓት ብቻ ነው የሚሰሩት::ለምን ከቴሌ አይማሩም:: ቴሌ ማንም ሄዶ ማየት ይችላል: የመስርያ ቤቱ ጥራትና አገልግሎት ያስንቃል:: ሳያርፉ ነው የሚሰሩት: በዛ ላይ ብዙ አስተናጋጅ ነው ያለው:::