Page 1 of 1

ትግራይ ከ40ሺ በላይ እስረኛ በአመለካከታቸው ምክንያት በ10 ማረሚያ ቤት እየማቀቁ ይገኛሉ!

Posted: 11 Mar 2020, 01:17
by Hameddibewoyane
መምህር የማነ ንጉስ በትግራይ እንደርታ ነው የተወለደ፣ ከመቀሌ ዩኒቨርስቲ በታሪክ ትምህርት ተመርቆ በዚሁ ትምህርት ሲያስተምር ነበር። 2007 ዓ.ም በተካሄደው ምርጫ የአረና ፓርቲ ዕጩ ሆኖ በመቅረቡ ተከሶ 3 ዓመት ተፈርዶበታል። ፍርዱንም በመቃወሙ በችሎት መድፈር 6 ወር ተጨምሮለት ከ2007-2010 ዓ.ስ 3 ዓመት ከ 6 ወር በመቀሌ ማረሚያ ቤት በእስር አሳልፏል። የደረሰበትን በትግራይ ሕዝብ ላይ ሕወሃት እየፈፀመ ያለውን ወንጀል ይገልፃል። በትግራይ ከ40ሺ በላይ እስረኛ በአመለካከቱ ምክንያት በ10 ማረሚያ ቤት እየማቀቁ ይገኛል በማለት ምስክረነቱን ሰጥቷል። ከእነዚህ ውስጥ ቤተሰብ የማያዩ ክ 22 ዓመት በላይ በእስር ላይ ያሉ የወልቃይት ተወላጆች በእስር ቤቱ እንዳገኘ ይገልፃል። ትግራይ ውስጥ ያለው የሕወሃት አፈና ማብቂያው ደርሷል ይለናል። በእነዚህና በአዲሱ የትግራይ ትውልድ እንቅስቃሴ ዙሪያ ከኢሳት ጋር ቆይታ አድርጓል። ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን መከታተል ይቻላል

Re: ትግራይ ከ40ሺ በላይ እስረኛ በአመለካከታቸው ምክንያት በ10 ማረሚያ ቤት እየማቀቁ ይገኛሉ!

Posted: 11 Mar 2020, 02:12
by Digital Weyane
የትግራይ ኡስር ቤቶቻችን ከአርባ ሺ ኡስረኞች ቦላይ ሞያዝ ስለማይቹሉ ነው ኡንጂ ሰባት ሞቶ ሺ ሰው በሽብርተኝነት ክስ ኡናስር ነበር። ዎንድሜ አዋሽ በቱክክል ኡንዳስቀመጠው፡ የትግራይ ኡስር ቤቶች በቴክኖሎጂ የተደገፉ ከፍተኛ የዴሞክራሲ ትምህርት ተቋሞች ናቸው። ኡያንዳንዱ ኡስረኛ ከኡስር ሲለቀቅ የዴሞክራስያዊ ዲግሪ አለው። ሎዚህም ነው ፈረንጆች ትግራይን የዴሞክራሲ ገነት ቡለው የሚጠሯት።

Re: ትግራይ ከ40ሺ በላይ እስረኛ በአመለካከታቸው ምክንያት በ10 ማረሚያ ቤት እየማቀቁ ይገኛሉ!

Posted: 11 Mar 2020, 23:06
by Digital Weyane
ቹግር የለም!