5 hrs · [Taken from FB]
መንግስት ሰሞኑን በኦሮሚያ የተላያዩ ዞኖች ለሚታዩ የትጥቅ ግጭቶች የኦሮሞ ነጻነት ግንባርን ተጠያቂ ለማድርግ ሞክሯል። ነገር ግን ኦነግ በእዙ ስር የነበሩትን ወታደሮቹን ከኤርትራ እንዲሁም ከጫካ አስገብቷል። እምቢ ብሎ የቀረውን ሀይል የኔ አይደለም ብለህ በፊርማ አረጋግጥ ለህዝብም አውጅ ተብሎ፤ ይህንኑ ፈጽሟል። ኦነግ በእዙ ስር ያለ ምንም ጦር እንደሌለው ከመንግስት ጋርም የነበረው የጦርነት ግንኙነቱ የተቋጨ መሆኑን በሊቀመንበሩ አቶ ዳዉድ ኢብሳ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራር ፊርማ አወጀ። መንግስትም ኦነግ የሚያዘውን ጦር በሙሉ አስገብቶ በአባገዳዎች አማካይነት ለመንግስት ማስረከቡን፤ እናም ከንግዲህ ከምንግስት ጋር የጦርነት ግንኙነት እንደሌለው፤ ማንኛውም ታጥቆ ለሚንቀሳቀስ ሀይል ኦነግ ተጠያቂ እንደማይሆን፤ እምቢ ብሎ ጫካ ለቀረው ሀይል መፍትሄ መንግስት እንደሚያበጅ በባለስልጣናቱ ፊርማ አረጋገጠ። የኦሮሚያን ክልል መንግስት ወክሎ ፕረዝዳንቱ አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ ገዢውን ፓርቲ ወክሎ አዲሱ አረጋ፤ የፌደራል መንግስትን ወክሎ ደግሞ የመከላከያ ምክትል ኢታማጆር ሹም ጀ/ል ብረሃኑ ጁላ ፊርማቸውን አሳረፉ። ከቴክኒካል ኮሚተው ደግሞ አቶ ሀይሌ ገብሬ፤ በቀለ ገርባ እና እኔ ፈረምን። ይህም በሚዲያ ተላለፈ።
ስላዚህ መንግስት ከታጠቁ ህይሎች ጋር ላሚያካሂደው ግጭት ኦነግን መወንጀል የሚያስችለው ምንም ህጋዊ መሰረት የለውም። ኦነግ ትጥቅ ትግል በቃኝ ብሎ በሰላማዊ መንገድ አላማውን ለማሳካት እንደ ፓርቲ ተመስርቶ እየተንቀሳቀሰ ነው። ስለዚህ የመንግስት ባለስልጣናት አላፈላጊ ንትርኮች ውስጥ ባይገቡ ጥሩ ነው።

