.***********************************************************************
አቦይ ስብሓት እኛ ደርግን ለመጣል እና ለውጥ ለማምጣት በብረት(ክላሽ)ታግለን ደርግ ጥለን ታሪክ ሰርተናል ይላሉ፣ አቦይ ስብሓት ልክ ናቸው፣ ይቀጥላሉ አቦይ ስብሓት፣ ይህ ትውልድ አለም የደረሰችበትን ቴክኖሎጂ እና ፖለቲካዊ ስልጣኔ ለመደርሰ መታገል ያቃተው ፈሪ ትውልድ ነው ብለዋል። አቦይ ስብሓት ለመሳፍንት ተገዢ ነበር ያሉት ትውልድ አሁን ካለው ትውልድ ጋር አዛምደው ይህ ትውልድ የኛ ባርያ ተገዢ ነው ይላሉ፣ በዚህ አላቆሙም፣ የፊታውራሪ ነጋ ልጅ አቦይ ስብሓት እኔ አባቴ እንዲገዛኝ ስለማልፈልግ ፀረ መሳፍንት(ፀረ አባቴ) ታግየ ለውጥ ያመጣሁ ጀግና ነኝ ይላሉ፣ አሁን ያለው የትግራይ ሙሁር ግን ልምሻ እና ሙቱቻ ነው ይላሉ፣ አሁን ያለው የትግራይ ሙሁር ትውልድ እኔ አባቴ መስፍን ስለ ነበር ታግየ እናዳባረርኩት፣ አሁን ያለው የትግራይ ሙሁሩ ትውልድ እኔ (ህወሓትን) ታግሎ ማሸነፍ አልቻለም ይላሉ!
*****************************************************************************************
ለዚህም ነው አቦይ ስብሓት ይህ ትውልድ ፈሪ እና ባንዳ ነው ያሉት። ይቀጥላሉ አቦይ ስብሓት፣ ህወሓት ከፌደራል መንግስት ተሸንፋ መቀሌ ከገባች ቦሃላ የተፈጠሩ አይጦች(ባይቶናን እና ሳልሳይ ወያኔን) ማለታቸው ነው፣ እነሱ ቢሆኑም ባንዳዎች ናቸው ብለው በድፍረት ተናግረዋል። አቦይ ስብሓት ባይቶናን እና ሳልሳይ ወያኔን ባንዳዎች ያልዋቸው ምክንያት፣ ከህወሓት ሽንፈት ማግስት የህወሓትን ሽንፈት ተጠቅመው ስለ ተመሰረቱ ብቻ ነው፣ እዚህ ላይ አቦይ ስብሓት ሽንፈት ያስመስልብኛል ብለው ነው እንጂ ዓረናን እንደሚያደንቁ ከፊታቸው ማንበብ ይቻላል። ዞሮ ዞሮ ባይቶናን እና ሳልሳይ ወያኔን ባንዳዎች ናቸው ብለዉናል፣ ይህ ብቻ አይደለም፣ እንገነጠላለን ባዮች በሙሉ ባንዳዎች ናቸው ብለዋል።
*****************************************************************************
አቦይ ስብሓት ፖለቲካን ሲሞቃቸው በማንክያ ሲበርዳቸው በእጃቸው እያደረጉ ተምሮ የደነቆረው የትግራይ ሙሁርን፣ በተከበናል እና በ አንድ ቢሄር ያነጣጠረ ፖለቲካዊ እርምጃ እየተወሰደ ነው በማለት የትግራይ ሙሁርን ለጊዚያዊ ፖለቲካዊ ፍጆታ ተጠቅመው ጥለውታል፣ አቦይ ስብሓት እኔ ኢትዮጲያዊ ነኝ ብለዋል፣ በዘረኝነት ያበደው ማሃይሙ የትግራይ ሙሁር እንገንጠል ሲል አቦይ ስብሓት ከተገነጠልክ እንካንስ አለም የአፍሪካ ህብረት ቻርተርም አያቅ ህም ብለዉታል። የትግራይ ሙሁር ሆይ አይገባህም እንጂ አቦይ ስብሓት እንዴት እንደናቁህ ልንገርህ፣ “ዋና ስንዋኝ” ይላሉ አቦይ ስብሓት፣ ለጉሮሮህ የሚጠጣ ዉሃ እና ለገላህ መታጠብያ የሌለህ የተማርክ ግን የደነቆርክ ፣ እምበር ተጋዳላይ መጨፈር የሚያምርህ ትውልድ፣ አቦይ ስብሓት ግን የውሃ ጥማቸው የሚያረካላቸው ውሃ ብቻ ሳይሆን፣ እዲሚያቸው የሚራዝምላቸው እና የሰውነታቸውን ሚዛን የሚጠብቅላቸው ለዋና የሚሆን ውሃ አላቸው፣ አንተ ፈሪ የትግራይ ሙሁር ግን የሚጠጣ ዉሃ ሳይኖርህ ለህወሓት ለመሞት እና ፀረ ፌደራል መንግስት ለመዋጋት ይዳዳሃል።
**********************************************************************************
ለኒን ህዝብ ግመል ነው፣ በአንድ አጠር ያለች እና ቀጭን ገመድ ስትፈልግ ገደል ትከተዋለህ እንዳለው፣ አቦይ ስብሓትም ተምሮ ለደነቆረው የትግራይ ሙሁር ላለፉት ሁለት አመታት ከተጠቀሙበት ቦሃላ ዛሬ ጥለውታል፣ አቦይ ስብሓት እኔ ኢትይጲያዊ ነኝ ብለዋል፣ አቦይ ስብሓት ከኢትዮጲያ ሊገነጠል የሚያስብ ሁሉ ባንዳ ነው ብለዋል፣አቦይ ስብሓት አባቴ ፊታውራሪ ነጋ የመስፍናዊ ስርአት አራማጅ ታግየ አሸንፌው ታሪክ ሰርቻለሁኝ፣ ይህ ትውልድ (የትግራይ ሙሁሩ)ግን ፈሪ እና የራሱ ታሪክ የማይሰራ ትውልድ ስለሆነ እስከምሞት ድረስ እንደፈለኩ አርጌ እገዘዋለሁኝ ብለዋል።
****************************************************************
አቦይ ስብሓትም ልክ ናቸው፣ የራሱ ታሪክ መስራት የማይችል የትግራይ ሙሁሩ(የትግራይ ትውልድ) ራስ አሉላ በሰራው ታሪክ ብቻ ሳይሆን አቦይ ስብሓት በሰሩት ታሪክ እየተኩራራ ታሪክ ሳይሰራ ጊዜው ሄዶበታ፣ የትግራይ ሙሁር ህወሓት በሰራችው የደደቢት ታሪክ የጉና ታሪክ እያላዘነ ሊኖር ነው። የካቲት 11 በመጣች ቁጥር ታሪክ ሳይሰራ ቁምጣ እና ሽርጥ ለብሶ እምበር ተጋዳላይ ሊለን ነው፣ ጀግና ሳይሆን “ተጋሩ ኢናየ ጀጋኑ ኢና” እያለ ሊዘፍን ነው። ባልሰራው የሰማእታት ሃወልት እንደ ሞዴሊስት ሃወልቱ ስር ቆሞ ፎቶ ሊነሳ ነው። አቦይ ስብሓት ልክ ናቸው፣ ትግራይ ውስጥ ተምሮ የደነቆረ ታሪክ የማይሰራ ፈሪ ተምሮ የደነቆረ ትውልድ ፈጥረዋል።
*******************************************************************
የኢትዮጲያ ወጣት ሆይ፣ ተምሮ የደነቆረው የትግራይ ሙሁር የካቲት 11 በመጣ
ቁጥር፣ ቁምጣ ቢለብስ፣ ሽርጥ ቢሸርጥ፣ ያልተኮሰው ክላሽ እና ላውንቸር ብይዝ ፣በእምበር ተጋዳላይ ቢጨፍር ጀግና እና ታሪክ ሰሪ እንዳይመስልህ። አቦይ ስብሓት እንዳሉት የራሱ ታሪክ መስራት የማይችል ፈሪ ትውልድ ነው።
Please wait, video is loading...