ለጀዌ ቀዌ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ይሰራለታል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሏል‼
Posted: 27 Feb 2020, 20:47
በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያትም የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ። ተጠርጣሪው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 በተለምዶ ጨው በረንዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በህብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉን የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር ታሪኩ መንገሻ ተናግረዋል። ግለሰቡ በሀሰተኛ መንገድ ካዘጋጃቸው መንጃ ፍቃዶች፣ የትምህርት ማስረጃዎች፣ የተለያዩ ማህተሞች፣ ፓስፖርቶች፣ ቲተሮች፣ የልደት ካርዶች እና ከሌሎች ማስረጃዎች ጋር ነው በቁጥጥር ስር የዋለው።







