Interesting development: ኢትዮጵያ የግድቡን ድርድር ለመሳተፍ አሜሪካ አልሄድም አለች: ዮሐንስ ቧ ያለው የስልጣኑን ሹመት አለቀበልም ማለቱ: አብይ ግራ የመጋባት ፀባይ ማሳየቱ
Posted: 26 Feb 2020, 13:34
፩ ) በጣም ጥሩ ዜና ነው : ኢትዮጵያ አሜሪካን አፍንጫሽን ላሺ ብላታለች:: አሜሪካ ሊደረግ በነበረው ድርድር ላይ ኢትዮጵያ አልገኝም ብላለች:: አሁን አገራችን አገር አገር እየሸተተች ነው::
፪) አቶ ዮሐንስ ቧ ያለው ዛሬ እንዳሳወቁት : የተሰጣቸውን የመለስ አካዳሚ ዳይሬክተርነት እንደማይቀበሉት ገልፀዋል:: የአማራ ትግል ይፋፋማል እንጂ አይቀጭጭም ብለዋል ::
፫ ) እዜማ አብይን እንደ ወቀሰ እየተነገረ ነው:: የህዝብ ገንዘብ ለምርጫ ቅስቅሳ ውሏል በማለት ነው ነቀፋው:: ምንድነው እየሆነ ያለው? እየፎገሩን ነው ወይስ ሌላ ነገ አለ?
፬ ) አብይ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የነበሩትን አቶ አዲስ ባሌማን : የ ፖሊሲና ጥናት ዳይሬክተር አርጎ ሾሟችወዋል:: ግርማ ብሩም እንዲሁ ተሾሟል:: ምንድነው ነገሩ? የግድ የትግራይ ሰው ካስፈለገ የወያኔ ባለስልጣን ግድ ነው እንዴ? እየፈጩ ጥሬ እየሆነ ነው? አብይ ግራ የገባው ይመስላል::
፭ ) ኤርትራ ዛሬ ከኢትዮጵያ ተነስተው አስመራ ለስብሰባ የገቡትን የኢትዮጵያ ካቶሊክ መሪዎችን : ከጉዟቸው እንዳገዱዋቸውና ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እንዳደረጉ ተገልትሷል::