Page 1 of 1

Must Read: How Woyane humilates the illiterate PM Abiy

Posted: 23 Feb 2020, 11:00
by Thomas H
Getachew Assefa is everywhere

የመቀሌው ኤርፖርት አጋች ታጋች ድራማ በተመለከተ

ባለፈው ዓመት አጋጥሞ ነገር ግን ዝርዝር ጉዳዮች ታፎነው በቆዩት የመቀሌ አሉላ አባ ነጋ ኤርፖርት በተመለከተ፣ በትግራይ ክልል የፀጥታ ኃይሎች ታግተዋል ስለተባለው የፌዴራል ፖሊስ ጉዳይ ላይ ለመጀመርያ ጊዜ ዘርዘር ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ቁጥራቸው 45 የሚደርሱ ከተለያዩ የፀጥታ ተቋማት ተወጣጥተው የተላኩ ልዩ የፌዴራል ፖሊስ ኃይል አባላት፣ ማንነታቸው ያልተገለጸ የወንጀል ተጠርጣሪዎችን ከመቀሌ ለመያዝ ተልከው እንደነበር በወቅቱ ተሰምቶ ነበር፡፡ ነገር ግን ዝርዝር ማብራሪያ በክልሉም ሆነ በፌዴራል ፖሊስ ሳይሰጥበት ተዳፍኖ ቆይቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ደብረ ጽዮን (ዶ/ር) በመግለጫቸው ተላኩ የተባሉ የፌዴራል ልዩ ኃይል አባላት ኤርፖርት ከመድረሳቸው በፊት የክልሉ ደኅንነት መረጃ እንደነበረው፣ መቀሌ ሲደርሱ ከተሳፈሩበት አውሮፕላን ሳይወርዱ መከበባቸውን ገልጸዋል፡፡

‹‹በአየር ኃይል አውሮፕላን ነበር የመጡት፣ በቅድሚያ እንደሚመጡ ለክልሉ መንግሥት አላሳወቁም ነበር፡፡ አውሮፕላኑ እንዳረፈ ወዲያው ከበብናቸው፡፡ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ አሳሰብናቸው፡፡ ዕርምጃ እንደምንወስድባቸው ካሳወቅን በኋላ ምክትል ኮማንደሩንና ሌሎች ሁለት ሰዎች ብቻ አስረን ጠየቅናቸው፤›› ብለዋል፡፡

‹‹በምርመራ ወቅት በተገኘው መረጃ መሠረት ልዩ ኃይሉ የእሴት ሰንሰለቱን በተበጣጠሰ ሁኔታ ከተለያዩ ዩኒቶች ተወጣቶ አንዱ ፖሊስ ሌላውን እንዳያውቅ ተደርጎ የተዋቀረ ነበር፡፡ የሚገርመው ነገር አንድም ከትግራይ ክልል የተመለመለ ፖሊስ እንዳይኖር ተደርጎ የተዋቀረ ኃይል ነበር፡፡ አጠቃላይ አወቃቀሩን ስንመለከት የአመራሩን ብስለት ጉድለት የሚያሳይ የልጅ ጨዋታ የሚመስል ነገር ነበር፡፡ እኛ በልምድ በምናውቀው በትክክለኛና በተቋማዊ አሠራር መሠረት ለአንድ ተግባር የፀጥታ አካል ከአንድ የሆነ ዩኒት መርጠህ ነው የምትልከው፡፡ በዚህ ግን የሆነው አሠራሩ ሕገወጥና ኢተቋማዊ ነበር፡፡ ይህን ያደረጉት ሚስጥር እንዳይወጣ ነበር፤›› ብለዋል፡፡ በወቅቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደውለው ማብራርያ ጠይቀው እንደነበር ጠቁመዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለተላከው ልዩ ኃይል የሚያውቁት ጉዳይ እንደልነበር ገልጸውልኝ ነበር ብለዋል፡፡ ነገር ግን እሳቸው የማያውቁት ኃይል ተልኳል ብለው ለማመን እንደማይችሉ አስረድተዋል፡፡

‹‹ቢያንስ ቢያንስ የአገሪቱ መከላከያ ኃይል የሚመሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ራሳቸው ሆነው ሳለ፣ ይህ ቡድን የአየር ኃይል አንቶኖቭ አውሮፕላን አስነስቶ ሲመጣ፣ እኔ አላውቅም ማለታቸው ራሱ ያስገርማል፤›› በማለት አክለው ገልጸዋል፡፡

Source: Reporter

Re: Must Read: How Woyane humilates the illiterate PM Abiy

Posted: 23 Feb 2020, 11:28
by Thomas H
ለመረጃ ያህል : የፌዴራል ሀይሎች መከበባቸውን ሲያውቁ እንደተለመደው ሱሪያቸው ላይ ሽንታቸውን ሸንተው ነበር

Re: Must Read: How Woyane humilates the illiterate PM Abiy

Posted: 23 Feb 2020, 22:41
by Thomas H
ዓብይን በቃ ሁሉም ይንቀው ጀመር:: የማንም መጫወቻ ሆኖ ቀረ

➤አሜሪካ የኢትዮጵያን ድጋፍ ሳትሻ የደቡብ ሱዳን ፖለቲካዊ ቀውስ በአንድ ማስጠንቀቂያ ጨረሰችው

➤ዓብይ አህመድ ከመበታተን አድነውኛል ብላ ያሞገሰችው ሱዳን ሆዳሴ ግድቡን በተመለከተ ስታራምድ የቆየችውን ኢትዮጵያን የሚደግፍ አቋም ወደ ጎን ብላ ግብፅን ብከዳሽ ልከዳ ማለት ጀመረች። ይህንን አቋም ተከትሎ በሱዳን ላይ ተጥለው የነበሩ ማዕቀቦች መነሳት ጀምረዋል - ጀርመን ተጠቃሽ ነች።

➤ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት እስሳሁን የአባይ የትብብር ማዕቀፍን ያልፈረመችው ኬንያ ብቻ ነች (የሱዳን እና የደቡብ ሱዳን ልዩ ምክንያት አለው)

➤በሶማሌ እና በሶማሌ ላንድ ፖለቲካ ውስጥ የኢትዮጵያ ሚና እየቀነሰ ነው

➤ጅቡቲ ኢኮኖሚዋ የተመሠረተው ለኢትዮጵያ ወደብ በማከራየት ነው። ጅቡቲ ከኢትዮጵያ የምታገኘው ጥቅም እንዳይቋረጥ የምትፈልገውን ያህል ኢትዮጵያም የወደብ አገልግሎቱ ቢቋረጥ መሔጃ የላትም። እንደውም የኃያላን ሀገሮች የሚሊቴሪ ቤዝ በጅቡቲ መንሰራፋቱ ሀገሪቱ በውስጥ ጉዳይዋ ላይ የመወሰን እና የማዘዝ ስልጣኗ የተጣበበ እንዲሆን ያደርጋል ፤ ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያ ታይም ቦምብ እንደማለት ነው።

➤ከኤርትራ የተፈጠረው የሰላም ሁኔታ ለውስጥ ፖለቲካ መጫወቻ ከመሆን ስላልተሻገረ ኤርትራም በዚህ ሁኔታ ውስጥ ምን ያህል ከኢትዮጵያ ጎን እንደምትቆይ እርግጠኛ መሆን አይቻልም።