የትግራይ ክልል የብልፅግና ፓርቲ መልዕክት አስተላለፈ
Posted: 19 Feb 2020, 11:56
https://mereja.com/amharic/v2/221605
የትግራይ ሕዝብ ተጋድሎና መሰዋዕትነት በከሰሩ ሃይሎች ኣይራከስም ፤ የቡዱናዊ ፍላጎት መጠቀሚያም አይሆንም እጅግ የተከበርከውና ከባድ የህይወት መስዋእትነትን ጨምሮ ውድ ዋጋ በመክፈል እና መራራ ትግል በማካሄድ ድል ያስመዘገበከው መላው የትግራይ ሕዝብ እንኳን ለ45ኛው የካቲት 11 በዓልህ በሰላም አደረስህ።
ይህን አኩሪና የህይወት መስዋእትነትን የጠየቀው ተጋድሎ በአንድ በኩል የትግሉ ዓላማን በማጠልሸት መስዋእትነቱን ለማራከስ በሚዳክሩ የከሰሩ ሃይሎች፤ በሌላ በኩል ደግሞ የተከፈለውን ህዝባዊ መስዋእትነት ለራስ ጠባብ ቡዱናዊ ዓላማ ለማዋል በሚፈልጉ ሃይሎች መካከል በሚደረግ የገመድ ጉተታና አንቶ ፈንቶ ጨዋታ ባለቤት የሆነውን የትግራይ ህዝብ የሚጋፋ መሆኑ እንገነዘባለን።
"እሳት ተኝቶ አመድ ጐበኘው” እንዲሉ የየካቲት 11 በዓል ዝክር ተምሳሌነቱ ሕዝባዊ እምቢተኝነትና የመስዋዕትነት ተጋድሎ እሳት የተቀጣጠለበት መሆኑን ዘንግተው የትግሉን የህዝብ ልዕልና አስኳል ጥያቄ ወደ ጐን ትተው አመድ የሆነውን የፖለቲካ ጨዋታ ሊጫወቱበት ሲከጅሉ ማየት ቢያሳዝንም ታሪክ ሰሪውና አስተዋዩ የትግራይ ህዝብ በተለይም ወጣቱ ሁኔታውን በጥሞና እንደሚከታተለው በጥልቅ እንገነዘባለን፡፡
ዛሬ ሃገራችንን ሰንጐ የያዛትን አክራሪ ብሄርተኛነት እና የፅንፈኝነት ክፉ በሽታ ምንጭና ምክንያት እንዳለው ልናስተውል ይገባል፡፡ የህብረ ብሔራዊ ፌደራሊዝም ስርዓቱ ምስረታ የብሔር ብሔረሰቦችን ማንነት ባህልና ታሪክ ሙሉ እውቅናና ጥበቃ የሚሰጥ ሲሆን የብሔር ማንነትና የህብረብሔር አንድነት በተመጣጠነ ሚዛን ለሐገረ መንግስትነት ግንባታ ተግባር ማዋልን የሚጠይቅ፤ ይህንንም በብሔራዊ መግባባትና ቅቡልነት ባለው የህግ ስርዓት ፅኑ መሰረት ላይ የመጣል ታሪካዊ ተልዕኮ መወጣትንም ጭምር ያካትታል፡፡
የህዝቡን የነጻነት እና የእኩለነት ትግል ለቡደናዊ እና ግላዊ ዓላማ ለማዋል የሚደረገው ሙከራ ውጤቱ ተመሳሳይ ነው። የፖለቲካ ክስረት ዋነኛ መገለጫ ሕዝባዊ መሰረትን ማጣትና ተራማጅ የፖለቲካ ሃሳቦችን በማፍለቅ ለመምራት የሚያስችል ብቃት ንጥፈት ዋነኛ ተጠቃሾች ናቸው፡
አብርሃም በላይ በርኸ ዶ/ር
የብልፅግና ፖርቲ አመራር አባል እና የትግራይ ቅርንጫፍ አስተባባሪ