ከሥራ የተባረሩት የህወሓት ደህንነቶች ተማሪ መስለው ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ገብተዋል!!!!
በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ሁከትና ብጥብጥ የሚያስነሱት እነማን ናቸው? በመሠረቱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ያለ ምንም ምክንያት እርስ በእርስ አይገዳደሉም። በእርግጥ በመካከላቸው ፀብና ግጭት ይኖራል። ነገር ግን በተማሪዎች መካከል የሚፈጠር ግጭት ቡጢ ከመሰናዘር አያልፍም። በአጠቃላይ የተማሪዎች ፀብና ግጭት ከስድብና ድብድብ አያልፍም። ካለፈው አመት ጀምሮ ግን በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ እንደሚታየው ተማሪዎች እርስ በእርስ በጭካኔ ሲገዳደሉ እያየን ነው። ዩኒቨርስቲዎቻችን ከመማሪያነት ወደ ሽብር ቀጠና ከተቀየሩ ሰነባብተዋል። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ህወሓት ከስልጣን ከተወገደ በኋላ ከስራና ሃላፊነታቸው የተነሱ የደህንነት ሰራተኞች ጓዛቸውን ጠቅልለው ዩኒቨርስቲ ውስጥ ገብተዋል። እነዚህ የህወሓት ደህንነቶች ዩኒቨርስቲ ውስጥ የገቡት የሀገሪቱን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሁከትና ብጥብጥ ለማተራመስ ነው። በዚህ መልኩ በ2011 ዓ.ም የጀመሩትን እኩይ ምግባር ዘንድሮ ይበልጥ አጠናክረው መቀጠላቸውን ከጥቅምት 30/2012 ጀምሮ በተግባር አይተንዋል። ይህን ተረድቶ አስቸኳይ የማስተካከያ እርምጃ ካልተወሰደ በስተቀር በቀጣዩ ሴሜስተር ደግሞ ከዚህ የባሰ ሁከትና ብጥብጥ ሊከሰት ይችላል።
Re: ከሥራ የተባረሩት የህወሓት ደህንነቶች ተማሪ መስለው ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ገብተዋል!!!!
Good observations. But they might not be the only problem makers. The hate preachers and the fear mongers need to be taken care of. I mean legally.