Page 1 of 1

በትግራይ ፖለቲካዊ፣ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች አሳሳቢ እየሆኑ መምጣታቸውን የታላቅዋ ትግራይ ብሄራዊ ሸንጎ ገለፀ

Posted: 07 Feb 2020, 11:26
by Za-Ilmaknun
ባለፈው ዓመት ተመስርቶ በትግራይ በመንቀሳቀስ ላይ ያለው የታላቅዋ ትግራይ ብሔራዊ ሸንጎ (ባይቶና) ተብሎ የሚታወቀው ፓርቲ በክልሉ እየታዩ ናቸው ያላቸው ፖለቲካዊ፣ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች አሳሳቢ እየሆኑ መምጣታቸው ገልጿል፡፡ባይቶና በተጨማሪም የመንግስትና ፓርቲ መደበላለቅ፣ በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች እየታየ ነው የተባለ የፀጥታና ድህንነት ችግር፣ የክልሉ መገናኛ ብዙሐን ወገንተኝነት፣ በመንግስትና ግል ወገኖች እየታየ ነው የተባለ የሀብት ብክነት የትግራይ ወቅታዊ ፈተናዎች ሲል ተቃዋሚው የፓለቲካ ድርጅት አስቀምጧቸዋል፡፡

https://mereja.com/amharic/v2/215075