የሴት ታጋዮቻችንና የ‘ገልጠም - አሶሳ - ገልጠም - ምጽዋ’ ገድል በፊዮሪ መሓሪ፡ ገነት ስዩም (ሽጎም) እንደተረከችው
Posted: 06 Feb 2020, 08:18
ይህ ጽሑፍ “ፈንቅል” በሚል ርእስ የትግሉን ዘመን ገድል ከሚተርከው 3ኛ ቅጽ መጸሐፍ ውስጥ የታጋይ ፊዮሪ መሓሪ የትግል ዘመን ታሪክን የዳሰሰ ታጋይ ነገት ስዩም (ሽጎም) የጻፈችው እ.አ.አ. በ1990 ምጽዋን ነጻ ለማውጣት የተደረገው “ኦፕሬሽን ፈንቅል” ወይ “ዘመቻ ፈንቅል” የሚባለውን ፈንቃይና ደምሳሽ የጦርነት ውሎ ዙርያ ያጠነጥናል። ታጋይ ፊዮሪ እግረኛ ሰራዊትን በመምራት “በቀጭኗ ጎዳና” ወይም “ስጋለት ቀጣን” በተባለችው መንገድ፡ ስፍር ቁጥር ያልነበረውን የጠላት አፈሙዝ የጥይት ውርጅብኝ ያቀናበትን ጎዳና ኣልፋ፡ ምጽዋን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ካስቻሉት ብርቅና ድንቅ እንስት ታጋዮቻችን አንዷ ናት። በዚህ “የቀጭኗ ጎዳና” ውጊያ ወቅት ጀብዱ ፈጽመው የተሰው ታንከኞችም ምጽዋ በተነሳች ቁጥር ሁሌም ይወሳሉ፣ ታንኮቻቸውም ምጽዋ ውስጥ የትግሉን ዘመን ታሪክ ይተርኩ ዘንድ ህያው ሃወልቶች ሆነው ተቀምጠው ይገኛሉ። ታሪኩ እንደወረደ በገነት ሽጎም አተራረክ ቀርቧል። ኮምኩሙ!
ሰምሃር የተባለው የቀይባሕር ዳርቻና ሜዳዎቹ ከረዢም ዘመናት ጀምሮ ብዙ ዕጹብ ድንቅ ፍጻሜዎች የተከናወኑበት ስፍራ ነው። የአካባቢውን የቅርብ ግዜ ታሪክን ስንቃኝ እንኳን፡ ዓይለትና ገምሆት የተባሉት የሰምሃር ቀየዎች፡ እ.አ.አ. በ1967 በኢትዮጵያ ሠራዊት በእሳት እንዲጋዩ ተደርገዋል። የምጽዋ ወደብንም ያለ አንዳች የነዋሪዎቿና የተወላጆቿ ተቃውሞ እንዳሻው ሊንፈላሰስባት ስለፈለገም ሕርጊጎ፣ እምበረሚንና ወቒሮ የተባሉትን ቀዬዎች ከነ ህንጻዎቻቸው በእሳት በማጋየት ነዋሪዎቻቸውንም በካራና በጥይት እያሳደደ ቁም ስቅላቸውን በማሳየት አመናምኗቸዋል።
ይህ የሰምሃር የቀይባሕር ዳርቻ በኤርትራ ህዝብ የነጻነት ትግል ታሪክ ውስጥ፡ እ.አ.አ. በ1977 ምጽዋን የማጥቃትና የስልታዊ ማፈግፈግ የተደረገበት እንዲሁም፡ እ.አ.አ. በ1990 የግፈኞቹ ባዕዳን ገዢዎች እድሜ ያጥርበት በነበረ ወቅትም፡ ለማመንና ለመተረኽ የሚያስቸግር በርካታ ተአምራዊ ገድላዊ ፍጻሜዎችን አስተናግዷል። ያም ሆኖ “እኔነት፡ ትምክህትና አጉል ኩፈሳ” እንዳይጎለብት በትግሉ ወቅት በተላበስነው የትግል ባህል አኳያ፡ እገሌ ወይ እገሊት እንዲህ እንዲህ አይነት ድንቅ ጀብዱ ፈጸመ ወይ ፈጸመች ይባላል ነበር እንጂ፡ ‘እኔ’ እያሉ መተረክ በኤርትራ ህዝብ የነጻነት ትግል ውስጥ ቦታ ያልነበረው መሆኑ የታወቀ ነው።
እስቲ የትግል አጋጣሚዎቻችንንና የገድል ታሪካችንን እንተርክ ስትባል፡ “ወታደራዊ ታሪክ መች የግለሰብ ታሪክ ሆነና!” ብላ ትጀምራለች ኤርትራዊቷ የነጻነት ታጋይ ፊዮሪ መሓሪ። ታጋይ ፊዮሪ መሓሪ እ.አ.አ. በ1977 ወደ ትግሉ ጎራ የተቀላቀለችና በበርካታ ጦርነቶችም የተካፈለች ተዋጊና አዋጊ ጀግና ነች። ወደ ትግሉ ከተቀላቀለችበት ግዜ ጀምሮ እስከ የኤርትራ ነጻነት ድረስ በተዋጊ የሰራዊት ክፍል ውስጥ ነበረች። ትግል የጀመረችበት ወቅት ‘ምዝላቕ’ ተብሎ በሚታወቀው፡ የኤርትራ የነጻነት ተዋጊዎች እስከ አፍንጫው ድረስ በሶቭየት ህብረትና በሌሎች ሃገሮች ብዙ ድጋፍ የተደረገለትን ግዙፍ የኢትዮጵያ የደርግ ሰራዊት በጥበብ ለማደባየት፡ ‘ስልታዊ ማፈግፈግ’ ባደረጉበት ወቅት ነበር። ፊዮሪም የደፈጣ ተዋጊ ምድብ ውስጥ ተመድባ፡ በጠላት ወረዳ ውስጥ ጥቃት ፈጽሞ፡ በመሸበት እየተሽለኮለከ የሚያድር የደፈጣ ጦር ውስጥ ‘አሃዱ’ ብላ የገድል ህይወቷን ጀመረች። በስንት ውትወታና ጥያቄ ገድላዊ ታሪዃን ልትነግረኝ የታሪኽ መዘክሮቿን እያገላበጠች ከብዙ ይሉኝታ ጋር ጥልቅ ትዝታ ውስጥ በመግባትም ገድላዊ ታሪኳን ከባህር በጭልፋ በተለይም ምጽዋን ለማጥቃት እ.አ.አ. በ1990 ስለተካሄደው ‘ኦፕሬሽን ፈንቅል’ እርሷ የተካፈለችበትን ውሎዋን እንዲህ አጫወተችኝ።
ኦፕሬሽን ፈንቅል ወይም በታጋዮች አሰያየም ‘ስርሒት ፈንቅል’ የተለኮሰው የካቲት 8 1990 ነው። ክፍለሰራዊታችን ማለትም 70ኛው ክ/ሰራዊት ግን ከወር በላይ ከአራምባ ቆቦ አራምባ ማለትም ‘ከገልጠም ወደ ገልጠም’ ነው የተወናጨፈው። እ.አ.አ. ሕዳር 11 1989 ክፍለሰራዊታችን ከዕጫይ ደብራይና ከአካባቢው ወደ ኋላ ማለትም ከምሽግ በኋላ ወዳለ ስፍራ ለልምምድና ቀጣይ ስልጠና እንዲወርድ ከተደረገ በኋላ፡ የመገናኛ ሬዲዮናችን በሙሉ ወሩን ሙሉ እንዲዘጋ ተደርጎ ነበር። ማንኛውም መልእክት በእግረኛ አማካኝነት ብቻ እንዲተላለፍም ተደረገ።
ተራ ታጋይ ይሁን ሃላፊም ወዴት እንደምንሄድ? ቀጣይ ስራችን ምን ማድረግ እንደሆነ፣ ምን እንደተወጠነ፣ በጭራሽ የሚያውቅና ለማወቅ የሚጨነቅ አንድም አልነበረንም። ነባሮቹ የሰሜናዊ ሳሕልና የናቕፋ ግንባሮችን ካፈራርስን በኋላ፡ ኑሯችን ቋሚና የተደላደለ አልነበረም። በከረን ግንባር ይሁን ማንኛውም የኛ ክፍለሰራዊት የነበረችበት ቦታ ሁሉ ጊዜያዊ ይዞታ ብቻ ነው የነበረን። በደንቡና በቅጡ አደልድለን ከሰራናቸው ምሽጎቻችን ወጥተን ጊዜያዊ መጠለያዎች እየሰራን ጠላትን እግር እግሩን እየተከተልን እንቅልፍ እንነሳው የነበር።
ገልጠም፡ ሃበሮ በተባለው ወረዳ ፡ ማለትም ከዛራ በስተምስራቅ የሚገኝ ከብዙ ትንንሽ ጅረቶችና ሸለቆዎች እየሰበሰበ ከምስራቕ ወደ ምዕራብ ወደ ዓንሰባ ወንዝ የሚቀላቀል ጠባብና ጥልቅ ወንዝ ነው። ገልጠም እንደ ስሙ በሁለት ትልልቅ ተራሮች መካከል የታቀፈ በመሆኑ፡ ድምጽ ሲፈጠር በቀላሉ አጋንኖና አግዝፎ የገደል ማሚቶው በጣም የሚያስተጋባበትና የሚያጉረመርምበት ወንዝ ነው። በገልጠም ወንዝ ውስጥ የሚገኙት ድንጋዮችና አለቶች እጅግ ትልልቅ አይደሉም። ሻካራዎችና ስለታማ በመሆናቸው ግን በገድል ላይ ገድል የሚጨምሩ አስቸጋሪዎችና ለመራመድ አሰናካዮችም ናቸው። ይህ ስፍራ የናቅፋው ግንባር ከመፍረሱ በፊት የመሸግንበት ሲኦል የሆነ ቦታ ነው። ከገልጠም በስተደቡብ ታጋዮች “ሃገር-ግኒ!” ብለው የሰየሙት በስተጀርባው የሚመታው አዳጋች ስፍራ፡ ይህ የገልጠም አካባቢ ነው።
ክፍለሰራዊታችን ከምሽግ ጀርባ ቆይታ ካደረግን በኋላ፡ ስልጠና ወደ ምናደርግበት ወደ ገልጠም ታሕሳስ እ.ኣ.ኣ. 13 1989 ተመለስን። ጠንካሮቹ ትልልቅ ማርቸዲሶቻችን በምርጥ ሹፌሮቻቸው እየተመሩ፡ ሳዋ ገባን። ከሳዋም በዒላ ኣብደላ በኩል ወደ ሱዳን መሬት ገባን። ሌት ተቀን ያለ አንዳች እረፍት ተጉዘንም አባይን ወይም ኒልን(ናይልን) አቋርጠን፡ የኢትዮጵያ መሬት ውስጥ ገባን። ታሕሳስ 30 በገስ በተባለ ስፍራ፡ የጉዟችንን ዓላማና ተልእኾ በተመለከተ በ70ኛው ክፍለ ሰራዊታችን አዛዥ በፊሊጶስ ወልደዮሃንስ (የአሁኑ ጄነራል) ኣማካኝነት ገለጻ ተደረገልን። ከወር በኋላ ገደማም ጊዛኒ ላይ በከፈትነው የማጥቃት እርምጃ ተዘግተው የነበሩት የክፍለሰራዊታችን የመገናኛ ሬዲዮኖች ተከፈቱ። ጠላትም ጠፍቶበት የነበረው የኛን ድምጽ ጊዛኒ ማለትም ምዕራብ ኢትዮጵያ ላይ ሰማ። ወደ አዲስ አበባ የሚወስደውን ዳውስ ላይ የሚገኘውን ድልድይም እ.አ.አ. ጥር 8 1990 በፈንጅ አፍርሰን፡ የጠላትን ቀልብ ስበን ወዲያውኑ ተመለስን።
ከጊዛኒ ወደ ዳውስ የተጓዝነው ብርቱ በሆኑት የስለያ ክፍሎቻችን አባላት እየተመራን ባይሆን ኖሮ እጅግ ጥቅጥቅ ያለ ጫካ ወይ ዱር በመሆኑ እጅግ አዳጋች በሆነብን ነበር። የምትረግጠው መሬት ሁሉ ረግረግ ጭቃ ነው። የሰው ሳይሆን የአራዊት ስፍራ ነው፡ ምንም ያልተዳሰሰ ድንግል መሬት፡ ሰው ሆነ ከብት ያልረገጠውን ስፍራ ተረማመድንበት ተጎማለልንበትም። ያኔ አዲስ የሃይል አመራር የሆንኩበት ግዜ ነበር። በዚያ ጭልጥ ባለ ዱር ወይ ጫካ ውስጥ የመገናኛ ሬዲዮዬ፡ ወዲህ ብላት ወዲያ ብላት ድምጿ ጥልቅም ብሎ ጠፋ! እንደዚያ ጊዜ ሆኜ ተጫንቄ አላውቅም። የሚነኩትን የሬዲዮ ክፍሎች ሁሉ ብነካካ ድምጽ የለ ምንም የለ ጥልቅም ብላ “ሹሽ” ብላ ድምጿን ማሰማት አሻፈረኝ አለችኝ! ከጊዛኒ ማለትም ከአሶሳ አካባቢ አይደለም የሬዲዮ ግንኙነት አቋርጠህ ይቅርና፡ በእግር እንኳ ስትሄድ እጅ ለእጅ ተያይዘህ ከመሄድ ከተሳነፍክ፡ አለቀልህ ነው! ብልህና ጀግና የኮማንዶ ስለያ አባላት ስለነበሩን ግን በነሱ ጥበብና የሬዲዮ ሞገድ ችግራችን ተፈታ።
ጥቃት ወደምንፈጽምበት ወደ ተልዕዃችን ስፍራ ስናመራም፡ ትንሽ ገላጣ ቦታ ስላገኘሁ ለማወሃሃድ ከግራ ወደ ቀኝ ሳማትር፡ ወደ ቤቱ ወይ ስፍራው የገባሁበት፡ ጆሮ ይሁን ቀንድ እንደነበረው በውል ያላጤንኩት ዘንዶ፡ ግማሽ ሜትር የሚሆን አካሉን ከሳሩ መሀል አቅንቶና ቀጥ አድርጎ፡ በሚያጉረጠርጥ ዓይኖቹ አፈጠጠብኝ! ዳግም ተመልሶም ለጥ ብሎ ለመንቀሳቀስ ሞከረ፡ ከግዝፈቱ የተነሳም እንደልቡና እንዳሻው ለመንቀሳቀስ ያዳግተው ነበር። እንዲያው እንዲህ አይነት ነገር አየሁ ሳልል እየተጣደፍኩ ወደ መሪዎቻችንና አባሎቻችን ተቀላቀልኩ። ከአሶሳው ተልዕኳችን በኋላ፡ ሌትና ቀን በማርቸዲስ ተጉዘን ግምሩክ(‘ኩርሙክ’ ይሆንን? ተርጓሚው ያከለው) ወደሚባል የሱዳን መሬት ተመለስን፡ ቁስለኞቻችንና ሠራዊታችን ባጠቃላይ ለሳልስትም እረፍት አደረግን።
ያኔም በሳህል ይሁን ባርካ ውስጥ አይተናቸው የማናውቅ፡ በጥፍሮችና በእግር ጣቶች መካከል ቆዳ ፈልቅቀው የሚገቡ ትላትል ፍጥረቶች፡ እጆቻችንና እግሮቻችንን አቆሳሰሉን። ይህን ቦታ የሚያውቁት የስለያ አባሎቻችንም እነዚህ ትሎች “ሙጀሌ ወይ ቦጀሌ” እንደሚባሉ ነገሩን። በመርፌም ነቅሰን እንድናወጣቸው ነገሩን። እርስ በርሳችን በመርፌ ሙጀሌዎቹን ነቃቅሰን ካወጣን በኋላ፡ የዳውስን ድልድይ በፈንጅ አፍርሰን፡ በምዕራብ ኢትዮጵያ ለጠላት ድምጻችንን አሰምተን፡ የመገናኛ ሬዲዮኖቻችንን አጥፍተን፡ ያለ እረፍት ሌተቀን ተጉዘን ወደ ተነሳንባት ገልጠም ተመለስን። ከበገስ ወደ ዒላ ዓብደላ፡ ከዒላ ዓብደላ ዓዳይት፡ ከዓዳይት መዝረት፡ ከመዝረትም የማደናገሪያ ስልታችንን ጨርሰን ወደ ተነሳንባት ገልጠም እ.አ.አ ጥር 26 1990. ተመለስን። ይህ ደግሞ ኦፕሬሽን ፈንቅል ከመጀመሩ ሁለት ሳምንታት በፊት ነው።
ይህ ሁሉ ከሁለት ወራት በላይ ከገልጠም ወደ ገልጠም ማለትም ከአራምባ ቆቦ አራምባ እንወናጨፍና እንጥበለበል የነበረው፡ ወደ ዋንኛው የሰምሃር ስርሒት ፈንቅል ማለትም ኦፕሬሽን ፈንቅል ጥቃት ለመፈጸም፡ ጠላትን ለማደናገርና ለማደነጋገር ነበር። በገልጠም ለሳልስት አደረጃጀታችንን በቅጡ ከፈተሽንና ካስተካከልን በኋላ፡ እጅግ ጥንቃቄና ምስጢራዊነት በተሞላበት እንቅስቃሴ በእግር ከገልጠም ታንከኞቻችን ወደሚገኙበት ሃበሮ፡ ከሃበሮም ወደ አፍዓበት፡ ከዚያም በሌሊት አፍዓበትን በስተግራ በመተው በረሃ ለበረሃ የእግር ጉዞ በማድረግ ዒን ወደ ተባለው ወንዝ አካባቢ ገባን፡ እዚያም ተደብቀን ዋልን። (በማግስቱ ምን እንዳደረግን በቀጣዩ ክፍል ትረካችን ይጠብቁን!)