በ22 አካባቢ በሀያማኖት ተቋም ስም መሬት ለመያዝ የተንቀሳቀሱ አካላት የፈፀሙት ድርጊት ህግወጥ እንደሆነ ገለፁ፡፡
Posted: 05 Feb 2020, 14:40
በ22 አካባቢ ለግጭት መነሾ በሆነው ቤተክርስቲያን ነው በተባለ ውስጥ ፅላት እንዳልነበረ መንግስት ገለፀ፡፡
05/02/2020
በ22 አካባቢ በሀያማኖት ተቋም ስም መሬት ለመያዝ የተንቀሳቀሱ አካላት የፈፀሙት ድርጊት ህግወጥ እንደሆነ በፊንፊኔ ከተማ የቦሌ ክፍለከተማ ዋና ስራአስክያጅ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ ገለፁ፡፡
አቶ ጥላሁን ከኦ ኤም ኤን ጋር በነበራቸው የስልክ ቆይታ፤ ቦታው ለግሪን ኤሪያ ከተማ አስተዳደሩ የከለለ ነው ብለዋል፡፡
በዚህ ቦታ ላይ ምንም ህጋዊ ፍቃድ ሳይኖራቸው በውድቅት ሌሊት ቤተክርስትያን የመገንበት ስራ ነው የተሰራው ብለዋል፡፡
ከዚህ ድርጊት ጀርባ ባለሀብቶች እንዳሉበት የተናገሩት አቶ ጥላሁን፤ እነዚህ ባለሀብቶች መሬቱን ለመያዝ ከዚህ በፊት ስንቀሳቀሱ እንደነበረ አስታውሰው አላማቸውን ለማሳካት የሀይማኖት አባቶችን እንደተጠቀሙ ነው የተናገሩት፡፡
ለህገወጥ ተግባራቸው ከለላ እንዲሆኑ ለማድረግ ከጀርባው ሁነው ህዝቡን በሀሰተኛ መረጃ በድብቅ ስያንቀሳቅሱ ነበር ብለዋል፡፡
በሌሊቱ በተሰረው ቤተክርስቲያን በተባለው ውስጥ ፅላት እንዳልነበርም ተናግረዋል፡፡
መንግስት በጉዳዩ ውስጥ የተሳተፉትን አካላት ለህግ እንደሚያቀርብም የቦሌ ክፍለከተማ ዋና ስራኣስኪያጅ ገልፀዋል፡፡