Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abaymado
Member
Posts: 4592
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

ለሚመለከተው ሁሉ: አዲስ አበባ ላይ ምንም ሥራ ቀጣሪ የለም: ፕሮፓጋንዳችሁን አቁሙ :: በዜሮ ዓመት ልምድ የሚቀጥር የለም:: ርምጃ ያስፈልጋል!!

Post by Abaymado » 04 Feb 2020, 14:27

የወያኔ የትምህርት ፖሊሲ የሚለው ለሳይንስ 70% : ለሶሻል ሳይንስ ደሞ 30% ነበር:: ለሳይንስ የሚሆን ሥራ ግን የለም :: አብዛኛው ተመራቂ እንጂነር በመሆኑ: ቀጣሪ የለውም:: ባለስልጣኖች : አብይን ጨምሮ ይህን የማስታወቂያ ዝርዝር ማየት መቻል አለባቸው:: በዜሮ ዓመት ልምድ የሚቀጥር መስርያ ቤት ወይም የግል ተቋም የለም:: አገሪቱ የግለሰብ ሆናለች ማለት ይቻላል:: የሚወጣው የስራ ማስታወቂያ ከ 5-8 ዓመት የስራ ልምድ ላላቸው ነው:: ይህ ደሞ በፊት ደህና ቦታ የያዙት ሰዎች ከቦታ ቦታ እንዲንሸራሸሩ ይረዳል እንጂ : ለመደበኛው ሥራ አጥ ምንም አልፈጠረም::
ወያኔ ጥሎት የሄደው አሻራ አሁንም አለ::: ወያኔ ለመቅጠር ሲፈልግ: የሚመርጠው ለወያኔ አጎብዳጅ ለሆኑ ብቻ ነበር:: ባብዛኛው ትግሬዎችንና ደጋፊውን ብቻ ነበር ሲያጉር የነበረው:: ይህ እንዲቀጥል ፈፅሞ አንፈልግም:: ልንታገስም አንችልም:: ትግሬዎች ተባረው ሌላው መግባት አለበት::

መንግስት በጣም ሊያስብበት የሚገባው ነገር ደሞ: ብዙዎቹ መስርያ ቤቶች ለዲፕሎማ እንጂ ለዲግሪ ማስታወቂያ አያወጡም:: ለዲፕሎማ ማስታወቂያ ቢያወጡና: አንድ የዲግሪ ተመራቂ ብቁ ነኝ ብሎ ቢሄድ: ይመልሱታል:: ለምን ሲባሉ:”over qualification ” ነው ይላሉ:: ምን ማለት ነው ይህ?

እንደ እኔ ከሆነ እነዚህ ርምጃዎች እንድወሰዱ ያስፈልጋል እላለሁ:
(፩ ) ከበላይ አካል ማንኛውም መስርያ ቤት በዜሮ ዓመት እንዲቀጥር ግዴታ እንዲጣልበት መደረግ አለበት
(፪ ) በዘመድ የሚሰራው ሥራ : አገሪቷን ባፍጢሟ ሳይደፋት ርምጃ ይወሰድ
(፫ )ሌላው አማራጭ ልክ እንደደርግ :ሁሉም ሰራተኛ እኩል ደሞዝ(ዝቅተኛም ቢሆን ) እንዲከፈል አርጎ ሁሉንም ሥራ አጥ መቅጠር::
ማን ተቀጥሮ ማን ይቀራል?

ይህንን ለማሳየት የስራ አጥ ቁጥሩን በቪድዮ ለሚቀጥለው እለጥፈዋለሁ::

Abaymado
Member
Posts: 4592
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

Re: ለሚመለከተው ሁሉ: አዲስ አበባ ላይ ምንም ሥራ ቀጣሪ የለም: ፕሮፓጋንዳችሁን አቁሙ :: በዜሮ ዓመት ልምድ የሚቀጥር የለም:: ርምጃ ያስፈልጋል!!

Post by Abaymado » 06 Feb 2020, 08:57

እዚህ አገር የስራ ማስታወቂያ በማውጣት ethiopian reporter ጥሩ ደረጃ ላይ ያለ ነው ::
ለዛሬ የስራ ማስታወቂያቸውን ለምሳሌ ያህል ካለፈው ሁለት ሳምንት ጀምሮ የወጣውን የስራ ማስታወቅያ እንይ:
1. Banking ------38 jobs
2. Const & architecture -----53 jobs
3. Engineering----135 jobs
4. Finance & accounting---138 jobs
5. Garduate ---30 jobs
6. Healthcare ---20
7. Management ---168 jobs
8. NGO---20 jobs
9. Sales and marketing---39 jobs
10. Legal---13
11. It and telecom-----34
12. Hotel and hospitality ----50
ናቸው::

https://www.ethiopianreporterjobs.com/
አሁን ጥያቄው ምን ያህል በዜሮ ዓመት ቀጠሩ የሚለው ነው: ከሌለ ሥራ የለም ማለት ነው:: ያው ሽግሽግ ነው የተደረገው:: አንድ ሚልዮን ሥራ አወጣን ብሎ ፕሮፓጋንዳ መስራቱ ለጥቂት ግዜ ማምለጫ ይሆን ይሆናል::
ለምሳሌ በዚህ ሁለት ሳምንት በ engineering የወጣው የስራ ብዛት 138 ነው አሉን:: ግን በዜሮ ዓመት አንድ የቀጠረ መስርያ ቤት አለ? የለም ::
እንደውም ባለፈው ስድስት ወራት በዜሮ ዓመት የቀጠሩት 10 ሰው ካለ ትልቅ ነገር ነው:: በ engineering ዉስጥ chemical, electrical, civil, mechanical .. እንዳለ ሊታወስ ይገባል:::
እናስ? በዜሮ ዓመት ካልቀጠሩ : ሥራ የለም ማለት ነው::
በአሁኑ ሰዓት ሥራ በደንብ ያለው ለዘበኝነት: ለፅዳት:.. ነው:: ዘበኞች እንደውም በተመረቁት ላይ ማላገጥ ይዘዋል:: “መማር ትርጉም የለውም” እየተባለ ነው::
አፋጣኝ ርምጃ ያስፈልገዋል!
Action now!!!!!!

Post Reply