Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Bashu
Member
Posts: 808
Joined: 19 Mar 2009, 22:24

Seyoum Teshome Has Finally Seen The Light About Imposter Abiy Ahmed?

Post by Bashu » 02 Feb 2020, 09:17

Seyoum Teshome
14 hrs ·
#ሁከትና_ብጥብጥ የሚያስነሳው #መንግስት ራሱ ነው‼
=====================================
ይሄ መጥረቢያና ገጀራ ይዞ #ሐረርና_ድሬዳዋን ሲበጠብጥ የሚውለው ጎረምሳ #ከጃዋር_መሃመድ ጋር ተቃቅፎ ስታዩ የተገረማችሁ በሙሉ በሉ አሁን #እርማችሁን አውጡ። ምክንያቱም ከታች በምስሉ ላይ እንደምታዩት ይሄ በጥባጭ #ጎረምሳ የወጣቶች የስራ ሂደት ባለቤት አቶ #እስክንድር ከተባለ ግለሰብ ጋር ቢሮ ስብሰባ ተቀምጧል። በዚህ መሠረት ከግብረአበሮቹ ጋር በቀጣይ ተግባራዊ ስለሚደረገው #የብጥብጥ_ስትራቴጂ ይወያያል። ከዚህ የምንረዳው ነገር፤ 1ኛ) #ሐረርና_ድሬዳዋ ላይ ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት የብሔርና ሃይማኖት ግጭት የሚቀሰቅስው #በመንግሥት ፍቃድና በጀት ነው። በመሆኑም የአከባቢው ህዝብ ዘወትር በሽብር ሰቆቃ ከሚኖር ከነጭራሹ "#መንግስት_የለም" ብሎ እርሙን ያውጣ‼ወይም ደግሞ 2ኛ) #የጃዋርና_አህመዲን የሽብር ቡድን ሐረርና ድሬዳዋ ላይ የመንግስትን ስልጣንና መዋቅር በበላይነት ተቆጣጥሯል። ስለዚህ የአከባቢው ነዋሪዎች ጓዛቸውን ጠቅልለው ይሰደዱ አሊያም ከአሸባሪዎች ጋር አብሮ መኖር ይለመዱ‼
ከዚህ በተረፈ የማንም ጎረምሳ በመንግስት ፍቃድና በጀት ህዝብና ሀገር እያሸበረ መስኪድና ቤተክርስቲያን በእሳት ሲቃጠል፣ ንፁሃን ዜጎች በግፍ እየተገደሉ ዳግም ከህዝብ ጋር አብሮ ማልቀስ፣ በዚህ እኩይ ተግባር የተሰማሩ ሰዎችን ከተጎጂዎች ጋር ሆኖ መርገምና ማማረር አይቻልም። "ሞኝን እባብ ሁለቴ ነክሰው፤ አንዴ ሲያይ ሌላ ግዜ ሲያሳይ" እንደሚባለው ሁሉ ህዝብ ሰላምና ደህንነቱን ማጣቱ ሳያንስ በፍትህ እጦት መሰቃየት የለበትም። ከዚህ በኋላ በተጠቀሰው አከባቢ ሁከትና ብጥብጥ ቢነሳ በመንግሥት ፍቃድና በጀት የተፈፀመ መሆኑን አውቃችሁ ያለ ማንም ድጋፍና እርዳታ ሰላምና ደህንነታችሁን በራሳችሁ ለማስከበር ከወዲሁ ተዘጋጁ‼ይህ በጥባጭ ጎረምሳ በህግ ቁጥጥር ስር ውሎ ለፍርድ እስካልቀረበ ድረስ በተለይ ሐረርና ድሬዳዋ ላይ ለሚፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ ከመንግስት ሌላ ማንም ተጠያቂ ሊሆን እንደማይችል ሊታወቅ ይገባል‼
See Translation