================================
(አፈንዲ ሙተቂ) - አዎን! ፕሬዚዳንት ኢሳያስ የተወለዱት February 2/1946 ነበር። በመሆኑም ነገ የልደት ቀናቸው ነው። ይህንን በማስመልከትም በድጋሚ አድናቆታችንን ልንገልፅላቸው ወደድን።
---
ኢሳያስ አፈወርቂ በእርግጥም ክብርና አድናቆት የሚገባው የአፍሪቃ ቀንድ ጀግና ነው። እነ ኢብራሂም ሱልጣን እና ወልደኣብ ወልደማሪያም የፈነጠቁትንና እነ ሃሚድ ኢድሪስ አዋተ እና ቀለበት የተሰውለትን የኤርትራ ህዝብ የነፃነት ትግል መርቶ ለድል ያበቃው የናቅፋ አንበሳ ሺህ ክብርና አድናቆት ይገባዋል። ኢሳያስን ለማድነቅ እርሱ እና ሻዕቢያ ያለፉበትን ፈታኝ የትግል ጉዞ በደንብ ማስተዋልን ይጠይቃል።

ኢሳያስና ሻዕቢያ በትጥቅ ትግሉ ወቅት ለሮኬት፣ ለቢኤም እና ለታንክ ሳይበገሩ በአፍሪቃ ግዙፍ ሃይል የገነባው የደርግ ሰራዊት ለሰባት ዙሮች ያደረጋቸውን ዘመቻዎች ሁሉ በቆራጥነት ተጋፍጠው አሸንፈዋል። ከነፃነት በኋላ ደግሞ ወያኔዎች "ኤርትራዊያን ይንቁናል" በሚል የድንቁርና ስሜት በጫሩት የጦርነት እሳት አሳብበው በኤርትራ ምድር ራሳቸው የሚያሽከረክሩትን አሻንጉሊት መንግስት ለመትከል ያደረጓቸውን ሙከራዎች ሁሉ ተቋቁመው አልፈዋቸዋል። የወያኔ መጥፊያ ሲቃረብም "Game over" በማለት ሞታቸውን አስታውቀዋቸዋል (በነገራችን ላይ የኢትዮ-ኤርትራ ግጭት የጀመረው ወያኔ እንደሚለው ሚያዚያ 28/1990 ሳይሆን ነሐሴ 1989 በቡሬ ግንባር ነበር። ፕሬዚዳንት ኢሳያስና አቶ መለስ ዜናዊ ከባድመ ጦርነት በፊት የተጻጻፏቸው ደብዳቤዎችም ይህንኑ የሚያመለክቱ ነበሩ። ደብዳቤዎቹ በኢትዮጵያ ነጻ ፕሬሶች በወጡበት ጊዜ ሰፊ መነጋገሪያ ሆነው ነበር)።
በ2001 የወያኔው መሪ መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ያላትን ቅርበት እንደ ጥሩ እድል በመጠቀም ኤርትራን በሐሰት ወንጅለው ማዕቀብ እንዲጣልባት ቢያደርጉም ኢሳያስንና ሻዕቢያን እጅ ማሰጠት አልቻሉም። ወይኔዎች የኤርትራዊያንን ንብረት ዘርፈው በጅምላ ከሀገር ባባረሯቸው ጊዜም ራሳቸውን ለትዝብት ከመዳረግ በስተቀር በኢሳያስና በሻዕቢያ ላይ ያመጡት ለውጥ የለም። የሚገርመው ነገር ወያኔዎች ያንን ሁሉ ወንጀል ሰርተው በቄሮ እና በህዝባዊ ትግሉ ሲወጠሩ "እኛ ቤተ ኣግዓዚያን ነን" የሚል ማጭበርበሪያ በመፍብረክ የኤርትራዊያንን ቀልብ ለመሳብ መሞከራቸው ነው።
ያለው የገለምሶው ልጅ እውነቱን ነው።ወያኔ መልቲ ሲስተም፣ የጃፓን እቃ ነው
----
እስቲ ፎቶውን በደንብ እዩት!
አቶ ኢሳያስ በኤርትራዊያን ዘንድ ያለውን ቦታ ለመግለጽ እንዲቻለኝ ከዚህ ቀደም ይህንን ፎቶ ለጥፌው ነበር። ፎቶው ኢሳያስ ጠመንዣ ባነገቱ የሳዋ ሰልጣኞች መካከል በድፍረት ገብቶ ሰላምታ ሲሰጣቸው ነው የሚያሳየው። ታዲያ ፍቶውን በለጠፍኩበት እለት አንዳንድ ሰዎች ኮሜንት ሲሰጡ "ጠመንዣው ጥይት የሌለው ቢሆንስ?" በማለት የኔን አስተያየት ለማጣጣል ሞክረው ነበር።
ተንኮለኛ ሰው ካለ መሪው ይህንን በመሰለ crowd ውስጥ ሲገባለት በጥይት ይቅርና በሰደፉ ብቻ መትቶት ጉዳት ሊያደርስበት አይችልም? በደንብ ነው የሚችለው። ሆኖም እንደዚያ ዓይነት ተንኮለኛ በኤርትራ ህዝብ ውስጥ የለም። ኢሳያስ በኤርትራዊያን ልብ ላይ የታተመ ብራንድ ነውና በተንኮል የሚፈልገው ሰው በዚያ ምድር የለም።
በነገራችን ላይ ወያኔ አቶ ኢሳያስን ለመግደል ከሃያ ጊዜ በላይ ሞክሮ ነበር። ነገር ግን አንድም ጉዳት ሊያደርስበት አልቻለም። እነዚህን ሙከራዎች ሁሉ ያከሸፋቸው ደግሞ የኤርትራ ህዝብ ራሱ ነው። ይህ ህዝብ ለመሪው ያለውን ፍቅር ሲገልፅ "ወዲ አፎም ይንበር" ይለዋል። "የአቶ አፈወርቂ ልጅ ይኑርልን" ማለት ነው።
-----
ወገን!
እውነትን እንጂ ፕሮፓጋንዳን አትመን። ፕሮፓጋንዳ ብዙ ያሳስታልና፡፡ ኢሳያስ በህዝቡ ባይወደድ ኖሮ ለሽንት እንኳ ከቤት የማይወጣ ቦርቧራ መሪ ሆኖ በቀረ ነበር፡፡ ሰውዬው ግን የህዝብ ልጅ ነው፡፡ የታገለው ለህዝቡ ነው፡፡ የሚኖረውም ቤተ መንግሥት ሳይሆን እንደ ማንኛውም ዜጋ አንድ አነስተኛ ቪላ በኪራይ ወስዶ ነው፡፡ ሻይና ቡና ለመጠጣትም ወደ አስመራ ካፍቴሪያዎች በእግሩ ይጓዛል፡፡ ባለቤቱ ወይዘሮ ሳባ ሃይለ እንደማንኛውም ኤርትራዊት እናት ገበያ እየወጣች የቤት አስቤዛ እና አትክልት ገዝታ ትመለሳለች፡፡ ልጆቹ ትምህርታቸውን የተማሩት በመንግሥት ትምህርት ቤት ነው፡፡ ኢሳያስ አፈወርቂ ማለት ነው እንዲህ ነው፡፡
----
"የኤርትራ ህልም" በሚል ርእስ በሰየምኩት መጽሐፍ ውስጥ ዋነኛ ትረካ የሆነውን "የኤርትራ ህልም" የተሰኘ የኢትኖግራፊ ወግ ለዚህ ጀግና የኤርትራዊያን መሪ እና የአባቴ ጓደኛ ለነበረው ዑሥማን ሳሊሕ ሳቤ መታሰቢያ ማድረጌ ትክክለኛ ውሳኔ ነበር (ሁለቱ ሰዎች በትግሉ ሂደት መግባባት አቅቶአቸው መለያየታቸውን አውቃለሁ፣ ነገር ግን በልጅነቴ ስለኤርትራ የማወቅ ጉጉት ያደረብኝ አባቴ የሳሊሕ ሳቤ ጓደኛ መሆኑን በማወቄ እንደሆነ ይበሉ)።
ለወደፊቱ የፕሬዚዳንት ኢሳያስን ሙሉ የህይወት ታሪክ የሚተርክ የባዮግራፊ መጽሐፍ ለመጻፍ እሞክራለሁ። ኢንሻ አላህ!!
----
እንኳን ተወለዱልን ክቡር ፕሬዚዳንት!
Baga nuud dhalattan kabajamoo Prezidant Isaayyaas!
ርሑስ በዓል ልደት ንፕሬሲደንት ኢሳያስ!
Happy Birthday!

