በታገቱት ተማሪዎች ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የፖለቲካ ቁማር ለመጫወት መሞከር የከፋ ኪሳራ ያስከትላል። የታገቱት ተማሪዎች ብዛትና እገታው የተፈፀመበት ዕለትን አስመልክቶ የተጣራ መረጃ የለም። እስካሁን ድረስ በጉዳዩ ዙሪያ አይን እማኝነቷን እየሰጠች ያለችው አንዲት ተማሪ ነበረች። ሰሞኑን ግን የVOA ጋዜጠኛ Tsion Girma ስምንት (8) የታጋች ቤተሰቦችን በስልክ ማናገሯን ገልፃለች። ጉዳዩን አስመልክቶ አስተያየት እንዲሰጡ የተጠየቁት የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ሃላፊ "የተማሪዎቹ ቤተሰቦች ለሚዲያ አስተያየት ከሚሰጡ ወደ እኛ ጋር ደውለው መረጃ ቢሰጡ ይሻላል" ብለዋል። ነገር ግን ጋዜጠኛዋ ከአሜሪካ ድረስ ስልክ አፈላልጋ ያናገረቻቸውን ሰዎች የፌደራል ፖሊስ አዲስ አበባ ውስጥ ተቀምጦ ሰዎቹን አፈላልጎ ተጨባጭ መረጃ ማግኘት የተሳነው የማንን ፀጉር እያበጠረ ነው? ቆይ እዚህ ሀገር ሥራና ሃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት የተሳነው የመንግስት ሃላፊ ተጠያቂ የሚሆነው መቼ ነው? ከዚህ በተረፈ ባህርዳር ላይ አብንና አዴፓ ዳግም ቂጥና ፓንት ማሽቋለጥ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። በሌላ በኩል "ነገሩ አጉል በሚዲያ እንዳይራገብ ብለን ውስጥ ለውስጥ ሥራችንን እየሰራን ነው" ሲል የነበረው መንግስት የታገቱት ልጆች እስካሁን የት እንደደረሱ በግልጽ መናገር አልቻለም። ጉዳዩ አደባባይ ወጥቶ ህዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ "ውስጥ ለውስጥ" የሚባል ነገር የለም። በመሆኑም
1) የታገቱት ተማሪዎች ስንት ናቸው?
2) እገታው የተፈፀመው በማንና መቼ ነው?
3) አሁን ላይ ታጋቾቹ ያሉበት ትክክለኛ ቦታ የት ነው?
4) ተማሪዎቹ የታገቱበት መሠረታዊ ምክንያት ምንድነው?
5) ከታገቱ በኋላ በተማሪዎች ላይ ጥቃት ተፈፅሟል ወይ?
6) የክልልና ፌደራል መንግስት ለጉዳዩ አስቸኳይ መፍትሄ መስጠት የተሳናቸው ለምንድነው?... ወዘተ
ለሚሉት ጥያቄዎች ይፋዊ ማብራሪያ ሊሰጥ ይገባል።
ከዚህ በተረፈ በታገቱት ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው ሰቆቃ የፖለቲካ ቁማር መጫወት ይብቃ‼
Re: በታገቱት ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው ሰቆቃ የፖለቲካ ቁማር መጫወት ይብቃ! መንግስት ማብራሪያ ይስጥ!!!!
Ejersa
u r online pls answer this for me..
did u ask this when fano killed ?
u r online pls answer this for me..
did u ask this when fano killed ?
Re: በታገቱት ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው ሰቆቃ የፖለቲካ ቁማር መጫወት ይብቃ! መንግስት ማብራሪያ ይስጥ!!!!
show me proof .. give me link .. where u or other opposed fano