Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4486
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

የኢትዮጵያ ኤርትራና ሶማሊያ መሪዎች የጋራ የጸጥታ ስጋቶቻቸውን ለመቀልበስ እቅድ አወጡ

Post by Za-Ilmaknun » 27 Jan 2020, 17:34

https://www.bbc.com/amharic/51270660

"ሦስቱ መሪዎች በጸጥታ እና በልማታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸው ተነግሯል።

በጸጥታው ረገድ ሦስቱ አገራት በሽብር፣ ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ፣ የሰዎች እና እጽ ዝውውር ስጋቶችን አብሮ ለመዋጋት እቅድ ማውጣታቸውን የኤርትራ የኢንፎርሜሽን ሚንስቴር አስታውቋል።

የሦስቱ አገራት መሪዎች 2018 ላይ የተፈራረሙትን የሦስትዮሽ ስምምነት ለማስፈጸም ቁርጠኛ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

የሦስቱ አገራት መሪዎች በየሃገራቸው ስላለው ሁኔታ፣ የሦስቱ አገራት ትብብር እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ የልማት እንቅስቃሴዎች ዙሪያ በዝርዝር መወያየታቸውን የኢንፎርሜሽን ሚንስትሩ በድረ-ገጹ አስነብቧል።

ሦስቱ መሪዎች 2020 የሦስቱ አገራት ጥምረት የሆነ በቀጠናው ሰላም፣ መረጋጋት እና የኢኮኖሚ እና ማሕበራዊ እድገትን የሚያጠናክር እቅድ መቅረጻቸው ተነግሯል።"