እሾህን በእሾህ !!!
Posted: 27 Jan 2020, 13:10
የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት አብቅቶ የድንበሩ ውዝግብ በ2002 በአልጀርስ መፍትሄ ከአገኘ በኃላ የኢትዮጵያ መንግስት የነበረው ወያኔ ላልፉት 16 ዓመታት ኤርትራን የተዋጋት ለህወሃት ተገዢ በነበሩ በጎረቤቶቿ መሪዎች አማካኝነት ብቻ ነበር። የድንበሩን ጉዳይ ከመስመር እንዲወጣ ተደርጎ ኤርትራን ከ2008 ጀምሮ ለ10 ዓመታት በኢኮኖሚ፣ ጦር መሳሪያ እና ዲፕሎማሲያዊ እገዳ እንዲጣልባት እና የአልጀርስን ውል እንዲቀለበስ የተደረገው በሶማሊያ እና ጅቡቲ ሰበብ ነበር። ያም የሟቹ መለስ ዜናዊ "ሰንዓ ፎርም" ይባላል። እንግዲያውስ ይህ የሶስቱ ሀገራት ትብብር ፎርም የዛ ቅዱስ ላልነበረው ማህበር ፈውስ መድሓኒት መሆኑ ጥርጥር የለውም!!







