አባይ ፀሃየ እና ውሾቶቹ!!!
Posted: 27 Jan 2020, 11:31

አሁንስ ትግራይ እንዴት ናት?
ፍትሕ፣ ነፃነት፣ እኩልነት አላት ወይ?
መስፍናዊ ስርዓት ህወሓት ምን እያረጋት ነው?
ትግራይ ውስጥ ጭቆና፣ አፈና እና እስር የለም ማለት ነው?
ትግራይ ውስጥ ልማት፣ ሰላም፣ እድገት፣ ዴሞክራሲ ኣለ ማለት ነው?
አሁን በናንተው ዘመን ትግራዋይ አይሰደብን፣ አይዋረድም፣ አይሰደድም፣ አይታሰርም፣ አምበጣ በሊታ አይባልም፣ በብሄሩ እየተጠቃ አይደለም ልትለን እንዴት ደፈርክ?
እንዴት የትግራይ ህዝብ ያለማቋረጥ ለ40 ዓመታት ልትዋሸው ትደፍራለህ?
የሃ/ስላሴ ስርዓት በአሜሪካ የሚዘወር ከነበረ የእናንተው ባንዳ ብዱንስ ደርግን ለመገረሰስ በማን ነበር የሚነዳው?
የአንተው ትውልድ የትግል፣ የነፃነት፣ የህዝባውነትና የዴሞክራሲ ጀግና ከተባለ አሁንም ይሄ ትውልድ ወደ ወሃላቀር እና የድንቁርናው የእርስበርስ ጦርነት መግባት አለበት ማለት ነው?
ጀግንነት በእርሰበርስ ጦርነትና ፣ ለስልጣን በሚደረገው የጀኔሬሽን ህይወት በሚቀዝፍ አካሄድ ነው የሚለካው?
ጀግኖች ከሆናቹሁ ምን ነው ታድያ አሁን ስርዓቱንና አገሪቱን ጥላቹ ወደ መቀሌ ለማምለጥ ወሰናቹ?
በርግጥ እናንተ በህዝብ ውሳኔ መሄድ ትችላላችሁ? ከመቼ ጀምሮ?
ሕገ መንግስቱስ በእናንተ ተከብሮ ያውቃል?
እኔ ሁሌም ትክክል ነኝ አልከን፣ ማን ነው ታድያ ትክክል ያልነበረው ና ያልሆነው?
እኔ በመርህ እና በመትከል ነው የሚንቀሳቀሰው ካልክ ማነው ታድያ እየዋዠቀ እስከ አሁን ስልጣን ላይ ያለው? 1968/9 ፣ 1993 የፈፀምካቸው ክህደቶች እንዴት ረሳሃቸው?
ማን ነው ብልጣብልጥ፣ ማን ነው በተንኮል የተመረዘ ሰው?
ስኳር ኮርፖሬሽን ስዎስት ግዜ ኦዲት ከተደረገ ምን ነው ታድያ በቤተሰብህ ስም የዘረፍከው ገንዘብ፣ በውሽማዎችህ ስም የዘረፍከው ገንዘብ በባንክ ብቻ ነው የሚገኘው ያለ ማን ነው?
በፕሮፓጋንዳ ህዝብ እንዲጠላቹ ከተደረገ እናንተስ ምን ስትሰሩ ነበር?
የፖለቲካ ስዎች ብቻ እንድትወገዱ ያረገው ማን ነው?
እናንተስ ምን እያረጋቹ ነበር? ትምክህተኛ ሃይሎች ገርስሰናል ስትሉ ነበር አሁን እንዴት ልትሸነፉ እና ትግራይ ህዝብ ላይ ምሽግ ልትሰሩ ተገደዳቹ?
ለእኩልነት የማትቆም ኢትዮጵያ ለማን አትጠቅም አልከን በናንተ ግዜ እኩልነት ነበረ ለማለት ነው?
ዋጋ የከፈሉ ሰማእታት ማመስገን፣ አይዛቹ ማለት እፈልጋለሁ አልከን ከወሬ ያለፈው ነገር ምን ልታርግላቸው ቻልክ በዚህ 28 የስልጣህ አመታት?
ኣንተ ለመሆኑ ታጋይ ነኝ ልትለን ነው? ታጋይ ማለት ከህዝብ ጥቅም ለራስህ ስልጣን አስበልጦ ለግሉን በመስፍናዊ ስልጣን ለማስኖር ነው እንዴ? ታጋዮች እማ በረሃ ላይ ወድቆዋል አንተ ግን ከንቱ፣ ግለኛ፣ ጥቅመኛ፣ አግላይ፣ ወንጀለኛ እና አረሜናዊ የእርስ በርስ ጦርነቱን ከህዝብ ይልቅ ለቡድን ጥቅም አሳልፈህ የሰጥክ ወራዳ ምንም አቋም የሌለው ሰው መሆንህ ነው የምናውቅህ። ሞኝህን ፈልግ እንልሃለን።