የውጭ ሪል ስቴት አልሚዎች (ኢግል ሒልስ) ለስቱዲዮ ያቀረበው የመሸጫ ዋጋ በዱባይ ከተማ ከሚጠየቀውም በላይ የተጋነነ መሆኑን የሪፖርተር ምንጮች ይገልጻሉ
Posted: 23 Jan 2020, 18:25
https://www.ethiopianreporter.com/article/17890
የውጭ ሪል ስቴት አልሚዎች ለሚገነቧቸው ቤቶች የሚያወጧቸው የሽያጭ ዋጋዎች መጋነናቸው፣ በመንግሥት ላይ ጥያቄ እንዲነሳበት ማድረጋቸው እየተገለጸ ነው፡፡ ለአብነትም በቅርቡ ሽያጭ መጀመሩን እያስተዋወቀ የሚገኘውና ኢግል ሒልስ የተሰኘው የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ሪል ስቴት ኩባንያ፣ ቤቶቹን መገንባት ሳይጀምር ሽያጭ መጀመሩን እያስተዋቀ ነው፡፡ ለስቱዲዮ ያቀረበው የመሸጫ ዋጋ በዱባይ ከተማ ከሚጠየቀውም በላይ የተጋነነ መሆኑን የሪፖርተር ምንጮች ይገልጻሉ፡፡
ሽያጭ የጀመረው ኢግል ሒልስ ሪል ስቴት ኩባንያ ቦታ መያዣ ቅድመ ክፍያን ጨምሮ፣ እ.ኤ.አ. በ2023 እንደሚያጠናቅቃቸው ለሚጠበቁ ቤቶች የዋጋ ዝርዝር በማውጣት ሽያጭ ጀምሯል፡፡ በዚሁ መሠረት ለስቱዲዮ የሚጠይቀው የመሸጫ ዋጋ 202 ሺሕ ዶላር ወይም ከስድስት ሚሊዮን ብር በላይ፣ ባለ አንድ መኝታ ከ230 ሺሕ ዶላር፣ ባለሁለት መኝታ ከ320 ሺሕ ዶላር ጀምሮ፣ ባለ ሦስት መኝታ ከ450 ሺሕ ዶላር ጀምሮ ዋጋ ሲወጣለት፣ ባለ አራት መኝታ ከ550 ሺሕ ዶላር ጀምሮ እንደሆነ በሪል ስቴት ኩባንያው እየተዋወቀ ነው፡፡
"በአንፃሩ ኢትዮጵያውያን በዱባይ ከተማ አፓርታማዎችን እንዲገዙ በአዲስ አበባ የሚያስተዋውቁ ኩባንያዎች ባለ አንድ መኝታ አፓርታማዎች የሚሸጡበት ዋጋ፣ በአዲስ አበባ ኢግል ሒልስ ለስቱዲዮ ቤት ካቀረበው ዋጋ በታች ናቸው፡፡ ለአብነት አንድ ስቱዲዮ አፓርትመንት በኢግል ሒልስ የሚሸጥበት የአዲስ አበባ ዋጋ በዱባይ ለባለ አንድ መኝታ ከቀረበው ዋጋ ያነሰ ሆኖ መገኘቱን በማመላከት፣ የሪል ስቴት አልሚው አካሄድ የሌሎች አልሚዎችን ዋጋ ሊያንር ይችላል የሚል ፍራቻ እንዳደረባቸው የኩባንያውን የሽያጭ ሒደት በሐያት ሬጀንሲ ሆቴል የተከታተሉ ይናገራሉ፡፡ ከሁሉ በላይ መንግሥት 27 በመቶ ባለድርሻ የሆነበት ይህ የለገሃር ፕሮጀክት በዚህ ደረጃ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን አፓርታማዎች ማስተዋወቁም አስገራሚ እንደሆነባቸው አስረድተዋል፡፡"
This is what is called development the Ethiopia style.It is less expensive to buy real estate in dubai than in Addis. I am dumbfounded. The country is being robbed in daylight? hhhh ! We shall see who the buyers are gonna be.