Page 1 of 1
የኢትዮጵያ አየር መንገድና የመንግስት ድርጅቶች በዘመዳ ዘመድ የሚሰሩ ናቸው: ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልጋል
Posted: 22 Jan 2020, 06:28
by Abaymado
አየር መንገዱ በአገሪቱ በጣም ከፍተኛውን ደሞዝ የሚከፍል መስርያ ቤት ነው:: ለምሳሌ ያህል አገሪቱ ውስጥ ትንሹ የጡረታ ክፍያ 1200 ብር ሲሆን: የአየር መንገዱ(የአብራሪዎች) ግን ትንሹ 150,000 ብር ነው:: ይሄ ሊታመን አይችልም:: ይህ የተንዛዛ ክፍያ አጠያያቂ ነው: ሌላው ህዝብስ? ይህ መስርያ ቤት የተሞላው በዘመደ አዝማድ ነው:: እናም የቤተሰብ ድርጅት ነው ማለት ይቻላል::
ለውጥማ ያስፈልጋል- ስር ነቀል ለውጥ!!! አንዱ ተጠቃሚ ሌላው ደሞ ተመልካች የሚሆንበት ምንም ምክንያት የለም::
ቴሌ ወደ 16,000 ቋሚ ሰራተኛ እንዳለው ይታወቃል:: ግን ቴሌም ችግር አለበት : መስርያ ቤቱ የተሞላው በቤተዘመድ በመሆኑ የማጥራት ሥራ ሊሰራ ይገባል:: ትላንት በወያኔ ግዜ ሲሄድ የነበረው አሁን አይቀጥልም: እኛ የታገልነው የተወሰኑ ቡድኖችን ተጠቃሚ ለማድረግ አይደለም!!
ወጥ የሆነ አሰራር በአገሪቱ ያስፈልጋል::
Re: የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኪሳራ ነው ያለው? ሊታመን የማይችል!
Posted: 22 Jan 2020, 06:38
by Dawi
Abaymado wrote: ↑22 Jan 2020, 06:28
ዋዜማ ሬድዮ በቅርቡ እንዳሳወቀው አየር መንገዱ ከ 2003 ዓመት ጀምሮ በኪሳራ ነው ያለው ሲል ዘግቧል:: ስለዚህም ያደርግ የነበረውን በረራ ለመሰረዝ እንደተገደደ ነው የታወቀው:: ይህም ከደቡብ አፍሪካ ወደ ተወሰኑ አውሮፓ አገር ሲያደርግ የነበረውን በረራ ከኪሳራ ለመዳን ሲል እንደሰረዘ ነው:: አየር መንገዱ ከኢትዮጵያ መንግስት የሚፈልገው ብድር ከ100 ሚልዮን ዶላር በላይ ብር እስካሁን ስላልተለቀቀለት ችግር ላይ ነው ያለው ብሏል ራድዮው::
‘ በብልዮን ብር አተረፈን’ ሲሉ የነበሩት ከምን ተነስተው ነበር? ምናልባትም ሙስና ሊሆን ይችላል:: ሌላው ደሞ: አየር መንገዱ በአገሪቱ በጣም ከፍተኛውን ደሞዝ የሚከፍል መስርያ ቤት ነው:: እና ለምን ለኪሳራ አይጋለጥም? ለምሳሌ ያህል አገሪቱ ውስጥ ትንሹ የጡረታ ክፍያ 1200 ብር ሲሆን: የአየር መንገዱ(የአብራሪዎች) ግን ትንሹ 150,000 ብር ነው:: ይሄ ሊታመን አይችልም:: ይህ የተንዛዛ ክፍያ አጠያያቂ ነው: ሌላው ህዝብስ? ይህ መስርያ ቤት የተሞላው በዘመደ አዝማድ ነው:: እናም የቤተሰብ ድርጅት ነው ማለት ይቻላል::
ለውጥማ ያስፈልጋል- ስር ነቀል ለውጥ!!! አንዱ ተጠቃሚ ሌላው ደሞ ተመልካች የሚሆንበት ምንም ምክንያት የለም::
ኢትዮ ቴሌ በዓመት 440 ቢልዮን ብር ማትረፍ ከቻለ: መሸጥ የለበትም:: ቴሌ ወደ 16,000 ቋሚ ሰራተኛ እንዳለው ይታወቃል:: ግን ቴሌም ችግር አለ: መስርያ ቤቱ የተሞላው በቤተዘመድ በመሆኑ የማጥራት ሥራ ሊሰራ ይገባል:: ትላንት በወያኔ ግዜ ሲሄድ የነበረው አሁን አይቀጥልም: እኛ የታገልነውየተወሰኑ ቡድኖችን ተጠቃሚ ለማድረግ አይደለም!!
ሲጠቃለል አየር መንገዱ በኪሳራ የሚሄድ ከሆነ መሸጥ አለበት::
Source?
That news was talking about SAA not EAL.
Re: የኢትዮጵያ አየር መንገድና የመንግስት ድርጅቶች በዘመዳ ዘመድ የሚሰሩ ናቸው: ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልጋል
Posted: 22 Jan 2020, 14:13
by Ethoash
Abaymado wrote: ↑22 Jan 2020, 06:28
አየር መንገዱ በአገሪቱ በጣም ከፍተኛውን ደሞዝ የሚከፍል መስርያ ቤት ነው:: :
dear Abaymado
አሜሪካኖች ዋስ ጥራ ሲሉህ መስሪያ ቤታቸው የሚስራ ሰው ዋስ ከጠራኸላቸው በጣም ነው ደስ የሚላቸው ። የብረት መዝጊያ ዋስ ነውና።
ሁለተኛ እኔ ፓለት ብሆን በወር ፫ሺህ ዶላር ቢከፈለኝና ዱባይ ደግሞ ፶ ሺህ ዶላር ቢከፍለኝ ለምን ብዬ ነው ለኢትዬዽያ አየር መንገድ የምስራው ። ፓለት እኮ ፕሮፌሽናል ስራ ነው የትም ሄደህ የሚያበላህ አሜሪካ ከመጣህ ደግሞ ፬መቶ ሺህ ዶላር ፤ ስለዚህ አየር መንገዱ ወስጥ የሚስሩት ፓለቶች አገር ወዳድ ናቸው እንጂ እኔ ብሆን ሳምንትም አልቆይም ላጥ ነበር የምለም ምስጋና ለሎው ስራ።
እንዲህም ብል የእኛን ፓለቶች ከእመሬት ከአረቦች ፓለቶች የበለጠ መክፈል ይቻላል በዶር ሳይሆን በብዛት ባለን ነገር መሬት ፤ መሬት በብዛት አለን መሬት ለፓለቶቻችን ብንስጥ እነሱ ደግሞ ተበድረውም መሬቱንም አስይዘው ፎቅ ቢስሩበት በወር ፶ሺህ ዶላር ስለሚያገኙ የትም አይሄዱም ተደስተውም ይስራሉ። ሌላ ዘዴ አለ። አየር መንገዱ በቢሊዬን ተቀማጭ ገንዘብ ስላለው በየአመቱ በመቶ ሺህ ዶላር የሚቆጠር ፋብሪካ በመስራት ለስራተኞቹ በደሞዛቸው ልክ ሼር በማስገባት ስራተኞቹ እንዲውስዱት ማረግ ይቻላል። ይህ ማለት በነፃ ሳይሆን በረዝም ግዜ የሚከፈል እና በሼር ክፍያ የሚገዛ ።
ለምሳሌ ፫፻ሺህ ዶላር የሚያወጣ የጭማቂ ፍብሪካ ለኤርላይንሱ የሚያስፈልጉትን ማንኛውንም ምርት የሚያመርቱ እንበል የዶሮ እርባት ለአየር መንገዱን ለከተማ ሕዝብ የሚሆን እርሻ አየር መንገዱ ጀምሮ ለስራተኞቹ ማዘዋወር ይችላል ። ይህ ማለት የተውስነ ገንዘብ መድቦ በየግዜው እንደዚህ ያሉ ተጎዳኝ ድርጅቶችን በመስራት ለስራተኞቹ በማዛውር ስራተኞቹን በሙሉ ሀብታም ማረግ ይችላል። አሁን ቤት ስርቶ መስጠት ጀምሮዋል ግን እንዱስትሪ ስርቶ ማዛውር እውነተኛ ሀብታም ያረጋቸዋል ። ይህ ዜዴ ለማንኛውም ድርጅት ይሆናል።
የኢትዬዽያ ሕዝብ ድሀ ስለሆነ የአየር መንገዱ ስራተኞች ደሀ ይሁኑ የሚለው አልቀበለውም ። አየር መንገዱ እንደዚህ ትንሽ ገንዘብ የሚከፍል ከሆነ ክፓለቱ ጀምሮ እስከሆስተሱ የኮንተሮባንድ ነጋዴዎች ይሆናሉ ክብራቸውንም ዝቅ ያረጋሉ ። ሽቀጥ ከሚሽከሙ ዶላራችንን በጥቁር ገበያ ከሚያወጡ ለምን አገር ቤት ውስጥ ፋብሪካ ተቋቁሞላቸው በሚስታቸው ስም አይነግዱም ። ለያንዳንዳቸው ሳይሆን ሼር ካፓኒ ።።።
ይህ ማለት ጎቦም ይቀራል ለምሳሌ የግዚ ክፍሉ ደሞዙ ፫ሺህ ብር ከሆነ ምን ይለዋል ከሻጭ ጋራ ተባብሮ አየር መንገዱን የሚጎዳ ስራ ይስራል ። ጥርት ያለ ስራ እንዲስራ ከፈለግን መክፈል አለብን ። ከዚህ ሌላ አማራጭ የለንም ። አዋ አየር መንገዱ ለመክፈል አቅም የለውም ስለዚህ በተዘዋዋሪ ክፒታል ፋብሪካ እየገነባ በሼር ለስራቶኞቹ ማዛር ይቻላል። ስራተኞቹም ከፍለው ሲጨርሱ ሌላ ፋብሪካ በመክፈት ሁለተኛ ዙር የቀሩትን ስራተኞች ሼር ይሽጣል እንዲህ እያለ በአጠቃላይ የአየር መንገዱ ስራተኞች በጣም አይለኛ ተከፋይ ያረጋቸዋል አየር መንገዱ ሳይጎዳ።
አሁን አየር መንገዱን መንካት ግን የጥፋት መልክተኛ መሆን ነው ጠቅላላ ፓለቶች ። ቴክኒሻኖች ትግሬ ክሆን በአንደ ጀምበር ተነስተው ቢሄዱ በ፫ሺህ ዶላር የውጭ ፓለት ማግኘት ትችላላህ ውይ ነው ጥያቄው።። ስለዚህ አፋችንን ባናበዛ የተሻለ ነው። አንዱን ትግሬ ፓለት ንካ ጠቅላሎቹ ናቸው ተነስተው ላጥ የሚሉት።
this is for world renounce expert economist Ash...