Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Hameddibewoyane
Member
Posts: 3890
Joined: 25 Sep 2019, 02:42

የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ሁሉም ጥያቄህን ወደ ጎን በይደር በማቆየት! በቅድምያ ህወሓት ከትግራይ ህዝብ ጫንቃ ለማውረድ በአንድነት ልትቆም ይገባል!!!!

Post by Hameddibewoyane » 17 Jan 2020, 15:52

ህወሓት ሳይወገድ በሰላም ምርጫ ማድረግ አይቻልም ምክነንያቱም የክፋት የሴራ ምንጭ ህወሓት ስለ ሆነች፡፡ ህወሓት ሳይወገድ ሰላም መረጋጋት አይኖርም። ወንድማችሁ ሚኪ ተስፋዬ አድራሻዬ ህወሓት ጥሏት ከፈረጠጠባት ውቢትዋ የኢትዮጵያ አገራችን ዋና ከተማ አዲስ አበባ ሁኜ ነው። አዲስ አበባ ቀደም ብዬ አላውቃትም ከመጣሁ አመትም አልሞላኝ ዛሬ ይሄው ህወሓት በአዲስ አበባና በአራት ኪሎ ቤተመንግስት ናፍቆት እየተሰቃየ ይገኛል። እኔ ደግሞ በኢትዮጵያውያን ወገኖቼ መሐል ሁኜ የትግራይ ህዝብ ከህወሓት ነፃ ለማውጣት እታገላለሁ።
ሚኪ ተስፋዬ

Ejersa
Member
Posts: 3978
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

Re: የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ሁሉም ጥያቄህን ወደ ጎን በይደር በማቆየት! በቅድምያ ህወሓት ከትግራይ ህዝብ ጫንቃ ለማውረድ በአንድነት ልትቆም ይገባል!!!!

Post by Ejersa » 17 Jan 2020, 18:09

ህወሓት የትግራይ ህዝብ አሁንም ገንዘብ እንዲያዋጣ በግድ ጥሪዋን አስተላልፋለች፣ ትርጉሙ ይህ ይመስላል

“የሰማእታት ቃል እንዳትከዱ
ባሁኑ ሳ አት የትግራይ ህዝብን እና ስርዓታችን (ህወሓት) ለማጥፋት እየተደረገ ያለው ሴራ የታወቀ ነው፣ ይህንን ለመፍታት ፓርቲያችን (ህወሓት) የገንዘብ ድጋፍ ስለጠየቀን ለ 10/05/12 02:00 ሰአት በወርቅ አምባ ትምህርትቤት እንድትገኙልን ጥሪ እናቀርባለን።
የወርቅ አምባ አስተዳድር
ክብር ለሰማእታት”

እኛም እንላለን ህወሓትን ለማጥፋት ከሚታገሉ የውስጥም ይሁኑ የውጭ መንግስታት እና ፓርቲዎች፣ ህወሓትን ለማጥፋት አብረን እንሰራለን።ህወሓት እስክትጠፋ ድረስ እንታገላለን። ከደህንነት ያልተላቀቀው የትግራይ ህዝብ፣ አሁንም ቢሆን ገንዘብ አዋጣ እየተባለ ካለቹው ገንዘብ እየተነጠቀ ይገኛል፣ ባለፈው ሳምንት ሁሉም የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ለህወሓት ሃያ ሃያ ብር እንዲያዋጡ ተደርገዋል፣ ስለዚህ አንድ ቤተሰብ አራት ልጆች ካሉት፣ በልጆቹ ስም፣ በራሱ ስም አሁን ደግሞ በየ ወረዳው እና ጣብያው እየተላለፈ ባለው ጥሪ ለህወሓት ገንዘብ ሊያዋጣ ነው። የአራት አባት ልጆች ከደሞዙ ምን ቀረው።ይህ የግዴታ ገንዘብ አዋጡ የሚለው መልእክት የህውሓት ማህተም ያለበት ነው፣ አንድ ፓርቲ ህዝብን እያስገደደ ገንዘብ አዋጡ እያለ ነው፣ ህወሓት እስካሁን ድረስ የካቲት ፩፩ ለማክበር ሁለት መቶ አምሳ ሚልዮን ብር መድባለች፣ ጨረታውም ኢፈርት ወስዶታል። በዚህ መሰረት የካቲት ፩፩ን ለማክበር

ለቲሸርት እና ቆብ ******$100 ሚልዮን ብር****
ርችት **************$10 ሚልዮን ብር****
ለቁልፍ መያዣ***** ****$15 ሚልዮን ብር*****
ያልታወቁ ወጪዎች *****$85 ሚልዮን ብር*****
.
የሰማእታት እናት እና አባቶች የሚበላ የሚጠጣ ባጡበት ወቅት
3000 ሺ የዳስ ትምህርት ቤቶች እያሉ
400 ሺ ስራ አጥ ወጣት እያለ
ህወሓት ከ 250 ሚልዮን ብር በላይ ወጪ በማውጣት የካቲት ፩፩ን ልታከብር ነው፣ ተምሮ የደነቆረ የትግራይ ሙሁር; አሁንም ቢሆን ፌደራል መንግስት በጀታችን ከለከለን ይልሃል፣ ህወሓት የተማረው የትግራይ ሙሁር አደንቆራ በመግዛት ተዋጥቶላታል።

Ejersa
Member
Posts: 3978
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

Re: የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ሁሉም ጥያቄህን ወደ ጎን በይደር በማቆየት! በቅድምያ ህወሓት ከትግራይ ህዝብ ጫንቃ ለማውረድ በአንድነት ልትቆም ይገባል!!!!

Post by Ejersa » 17 Jan 2020, 18:23

በትክክል እባብ ቤትህ ውስጥ እያለ በሰላም ትኝተህአታድርም ነው ነገሩ: የትህነግ መርዝ እነበቀለ ገሪባን መርዞ: ኢትዮጵያን እየበከለ ስለሆነ ሰላም አይኖርም :oops:
Hameddibewoyane wrote:
17 Jan 2020, 15:52

Post Reply