Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abaymado
Member
Posts: 4602
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

ኢትዮ ቴሌኮም በስድስት ወር ብቻ 22 ቢልዮን አገኘ !!! በስንት ቢሸጥስ ያዋጣል?

Post by Abaymado » 15 Jan 2020, 15:18

ያለፈው ዓመቱ ትርፍ 17 ቢልዮን ሲሆን በአሁን 32% እድገት አሳይቷል::
የተገኘው ትርፍ ሲዘረዘር;
1. ከሞባይል ስልክ 50%
2. ከኢንተርኔት 27%
3. ከዓለም አቀፍ ንግድ ድርሻ 10 %
ቴሌ 45 ሚልዮን የሞባይል ተጠቃሚ ሲኖረው: 22 ሚልዮን ደሞ የኢንተርኔት ተጠቃሚ ነው:: fixed telephone ደሞ 1 ሚልዮን ደንበኛ አላቸው::
እንዴት ትርፍ መጣ? እንደመሰለኝ: ቅናሽ ስላደረጉ ተጠቃሚው ስለጨመረ ነው::
አሁንም መቀነስ አለበት:: ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ውድ የኢንተርኔት አገልግሎት የምታቀርብ አገር ናት:: በወር 512Mbs የሚጠይቅ በቋሚነት የሚያስከፍሉት 550 ብር ገደማ ነው:: ይህ ወደ 250 ወይም በታች ቢሆን ጥቅሙን ያዩታል::
ትልቁ ጥያቄ : ቴሌ የሚሸጠው በስንት ይሆናል? ልብ ይባል : በአስር ዓመት ውስጥ 440 ቢልዮን ብር ማምጣት ይችላል::
(ለተጨማሪ መረጃ የቴሌን ድረ ገፅ ይጎብኙ )