የፍትሕ እጦት በራያ!!!!
Posted: 14 Jan 2020, 15:15
ባለፈው በራያ ዋጃ ጥሙጋ ከተማ ትህነጎች የነዋሪውን ህዝብ መሬት መቀራመታቸው ተገልጾ ነበር፡፡ ይህ ዛሬ ደግሞ ብሶት የወለደው ህዝብ የሚሰማው አጥቶ እንዲህ ይከራተታል፡፡ እንዴት መሬታችንን በግፍ እንወረራለን እያለ በአደባባይ ተቃውሞውን እየገለጠ ነው፡፡ ወገኔ ሆይ ፍትህን ከነጠቀህ ቀማኛ ፍትህ አትጠይቅ፤ ይልቅስ ፍትህን አንገት ላንገት ተናንቀህ አስፍን፡፡ ራስህን በራስ አስከብር!! ዛሬ በጥሙጋ ማዘጋጃ ቤት የትህነግን የዲሞግራፊ ለውጥ ፖሊሲ ህዝቡ እንደዚህ በነቂስ ወጥቶ እየተቃወመ ነው!! በርስታችን በፈናቀል ይብቃ፡፡ ፍትህ ለራያ ህዝብ!!



