ሰበር ዜና:- በወለጋ ተማሪዎቹን "ያገቷቸው" ተማሪዎች ናቸው! ታጋቾቹ 26 ሲሆኑ 21 ተለቀው 5 ይቀራሉ!
Posted: 12 Jan 2020, 15:14
ጀመሪያ 17 ተማሪዎች ታገቱ ተባለ። ትላንት ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ሃላፊው አቶ ንጉሡ ጥላሁን 21 ተማሪዎች ተለቀዋል ማለታቸው ይታወሳል። በዚህ መሠረት መታገታቸው ያልተሰማ 4 ተማሪዎች አሉ ማለት ነው። BBC አማርኛ ደግሞ ተማሪዎቹን ቤተሰቦች አናግሮ "በሚዲያ ተለቅቀዋል" መባሉን ከመስማታቸው በስተቀር የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ዘግቧል። የደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲም ተመሣሣይ አስተያየት መስጠቱ ተሰምቷል። ስለዚህ ማንን እንመን? ስለታገቱት ተማሪዎች ትክክለኛው መረጃ የቱ ነው? እትጌ Meskerem Abera እነዚህንና ሌሎች ጥያቄዎችን እያነሳች ስለወተወተችኝ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊ ጋር ስልክ ደወልኩና ጉዳዩን አጣራሁ። ነገሩ እንደዚህ ነው፤
በመጀመሪያ ደረጃ ከ16 ዩኒቨርስቲዎች ወጥተው ወደ ቤተሰቦቻቸው የሄዱ 35ሺህ ተማሪዎች አሉ። ኸእነዚህ ውስጥ ግማሹ ቤተሰቦቹ ጋር ደርሷል፤ ሌላው መንገድ ላይ ይሆናል፣ ከፊሉ ወደ ቤቱ ሳይሄድ ከተማ ውስጥ አንዱ ጋር ተቀምጧል፤ ጥቂቶች ደግሞ ጫካ ውስጥ አድፍጠው ተማሪዎች #ያግታሉ። ተሳስቼ አይደለም‼ አዎ... ከደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ወጥተው ወደ ቤተሰቦቻቸው በመሄድ ላይ የነበሩ ተማሪዎችን መጀመሪያ ላይ ያገቷቸው የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ወይም ጃል ማሮ አይደለም። ከዚያ ይልቅ በአማራ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩና ሰሞኑን በተፈጠረው ችግር ምክንያት ወደ ትውልድ ስፍራቸው የተመለሱ የደምቢዶሎ አከባቢ ተወላጅ የሆኑ የዩኑቨርሲቲ ተማሪዎች ናቸው።ሆኖም ግን "ተማሪዎቹን ያገተው ኦነግ ሸኔ ነው" እየተባለ በሰፊው ስለተወራ ጃል ማሮ ራሱ አጋቾቹ ያሉበትን ቦታ አፈላልጎ ማግኘቱና አስፈላጊውን ድጋፍና ጥበቃ ማድረጉ አይቀርም። ምክንያቱም፤ አንደኛ፦ ነገሩ ከፍተኛ የሆነ ፕሮፓጋንዳ እየተሰራበት ነው፣ ሁለተኛ፦ ድርጊቱ የተፈፀመው በስሙ ነው፣ ሦስተኛ፦ መንግሥት ከሚወስደው እርምጃ በተጨማሪ በማህብረሰብ ደረጃ የሚያስከትለው ጣጣ ብዙ ነው። ስለዚህ አክቲቪስት የተባለ ሁሉ "ኦነግሸኔ የአማራ ተማሪዎችን አገተ!" እያለ ወሬውን ሲያራግብ ልጆቹን ከአጋቾቹ ተማሪዎች አሳልፎ ለጃል ማሮ ታጣቂዎች ሰጣቸው። "ጉድ በል ጎንደር!" ማለት ይሄኔ ነው።
በመጨረሻም ጎረምሶቹ ያገቷቸው ተማሪዎች ብዛት 27 ነበር። ከእነዚህ ውስጥ አንዷ በራሷ አምልጣ ቤተሰቦቿ ጋር ሄዳለች። እዚህ ጋር ልጅቷ ከBBC ጋር ባደረገችው ቃለምልልስ "ወጠምሻዎቹ ከሌሎች ተማሪዎች ጋር በዚህ ሂዱ እያሉ ሲጨቃጨቁ ቀስ ብላ እንዳመለጠች ተናግራለች። ማይ ፍሬንድ ክላሽ የታጠቀ አጋች ሂድ አትሂድ እያለ አይጨቃጨቅም። አንተም ከአጋቾቹ ጋር አትሳፈጥም። ይህቺ ልጅ ግን "...ካመለጥኩ በኋላ ጫካ ውስጥ ሁለት ቀን አድሬ አንድ አባት አገኙኝ። እሳቸውም የእኔስ ልጆች ቢሆኑ እንዲህ አይደል የሚሆኑት ብለው ኮታቸውን አለቀሱኝ። ከዛ ሸኙኝ..." ጲሪሪሪሪ ወራጅ አለ‼ ከልጅቷ አነጋገር ሁለት ቀን ጫካ ውስጥ ያደረች አይመስልም። ከዚያ ይልቅ መረጃውን እንድታወጣ የለቀቋት ይመስላል። ለመሆኑ BBC አማርኛ የልጅቷን እና የተማሪዎቹን ቤተሰቦች ስልክ መቼና እንዴት አገኘ? ኦኦ... ስልክ ስል ትዝ... አለኝ። ልጅቷ ከታገቱት ልጆች ጋር በስልክ ታወራ እንደነበር ገልፃ ስልኩም የአጋቾቹ እንደሆነ ለBBC ተናግራለች። የራሱን ስልክ ሰጥቶ ያለበትን ቦታ ለደህንነት ሰዎች የሚናገር አጋች!! ሆሆይ... ለማንኛውም ከቀሩት 26 ተማሪዎች ውስጥ ትላንት 21ዱ ተለቅቀዋል። በዚህ መሠረት አሁን 5 ተማሪዎች ይቀራሉ። የጠቀስኩት የመንግስት ሃላፊ እንደነገረኝ የቀሩትን ተማሪዎች ለማስለቀቅ በሰከነ መልኩ እየተሰራ ነው። ነገሩን ያለ ቅጥ ማራገብ የባሰ ችግሩን ከማወሳሰብ የዘለለ ፋይዳ የለውም። ይህን ጉዳይ በማቀነባበር ረገድ ተሳታፊ የሆኑት አካላት፦ የኦነግ ሽኔ ደጋፊዎች፣ የአማራ ሸኔ ብሔርተኞች፣ የBBC አማርኛ ባልደረቦች፣ የበጀትና ሎጅስቲክ ድጋፍ እነ አንቶኒዎች። BBC አማርኛ ሲከፈት ጃዋር ኬኒያ ድረስ ሄዶ የሰጣቸው መመሪያ ምን እንደሆነ አሁን በደንብ እየገባኝ ነው።