በህወሃት የተቋቋመው የፌድራሎች ፎረም ምክትል ሊቀ መንበር ኮበለለ!!!
Posted: 09 Jan 2020, 08:56
በህወሃት የተቋቋመው የፌድራሎች ፎረም ምክትል ሊቀ መንበር ኮበለለ!!!
አቶ ትዕግስቱ አወሉ ከፌዴራሊስት ኃይሎች ፎረም ምክትል ሊቀ መንበርነት እራሳቸውን አገለሉ
"ህወሃት እያካሄደ ባለው የሴራ ፖለቲካ ላለመሳተፍ ከፌዴራሊስት ሃይሎች ፎረምና ምክትል ሊቀ መንበርነቴ እራሴን አግልያለሁ" ሲሉ አቶ ትዕግስቱ አወል አስታወቁ።
የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ሊቀ መንበር አቶ ትዕግስቱ አወሉ በህወሃት ጋባዥነት ትግራይ ክልል ሄደው የፌዴራሊስት ሃይሎች ፎረም በመመስረት በምክትል ሊቀመንበርነት መመረጣቸውን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ገልጸዋል።
ዛሬ ከሃላፊነታቸውና ከፎረሙ ራሳቸውን ማግለላቸውን ያስታወቁት አቶ ትዕግስቱ፤ ግብዣው በተደረገበት ወቅትና ፎረሙ ሲመሰረት ዋና አላማ ያደረገው "ህገ መንግስቱ እየፈረሰ ስለሆነ እናድን ፌደራሊዝም ስርአቱም ወደ አሃዳዊነት እየተቀየረ ነው" በሚል መነሻ እንደነበረ አመልክተዋል።
ይሁን እንጂ ፌዴራሊስት ሃይሎች ፎረም ተብሎ እየተዋቀረ ያለው አደረጃጀት ፍፁም ዴሞክራሲያዊ ያልሆነና የቀድሞውን ያረጀ አስተሳሰብ ያነገበ መሆኑን በመረዳታቸው ከሃላፊነታቸውና ከፎረሙ መልቀቃቸውን አስታውቀዋል።
ህወሃት ያደራጀው የፌዴራሊስት ሃይሎች ፎረም ገና ህጋዊ እውቅና እና ሰነድ ያላገኛ ከመሆኑም በላይ ትግሉን ለማካሄድ የሚፈልግበት መንገድ "የሃይል እርምጃን ጨምሮ ማንኛውንም አማራጭ እጠቀማለሁ የሚል ነው" ሲሉም ተናግረዋል።
በመሆኑም "ይህ አካሄድ ቢመቻቸው እነርሱ የሚፈልጉት ብሄር ተኮር የሴራ ፌዴራሊዝም ካልተቻለ ደግሞ የመነጠል ፖለቲካ ይዘው መንቀሳቀስ ነው" ብለዋል።
ይህ አካሄድ "የትግራይን ህዝብ ጨምሮ የኢትዮጵያ ህዝብ ዳግም ሊያስለቅስ የተነሳ ነው" ያሉት አቶ ትዕግስቱ፤ አሁን እየተካሄደ ያለውን ለውጥ "አሃዳዊ ነው ብለው የፈረጁት ህዝቡን ለማነሳሳት የተጠቀሙበት ሴራ ነው" ሲሉ ገልጸውታል።
በመሆኑም የአንድነት ፓርቲ አሁን እየተተገበረ ካለው ፖለቲካዊ ለውጥ ጎን "በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለአገርና ለህዝብ የሚጠቅም ፖለቲካ እሳተፋለሁ እንጂ ይህን የሴራ ፖለቲካ ልከተልም አልችልም" ሲሉም ተናግረዋል።