Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
AbebeB
Member+
Posts: 7694
Joined: 15 Oct 2016, 10:31

@ESAT: አጭቤው ብርሁኑ ነጋ ቃለ መጠይቅ ጉዳይ (ክፍል 2):: በESAT ይተላፍ፡፡

Post by AbebeB » 08 Jan 2020, 16:35

በክፍል 2 የአሻ ቲቪ ቃለ መጠይቅ ደግሞ አጭቤው ብርሀኑ ነጋ በጋዘጤኛውም ተይዟል፡፡ የግለሰብ መብት በመሬት ያሌለና በአየር ላይ የተንጠለጠለ ጥያቄ ነው ያላችሁ በማለት ከኢትዮጵያ ብሔር መብት ጋር አያይዞ ሲጠየቅ ሲጠይቀው አጭቤው እንደለመደው ስለ አሜሪካና ስለ ዩጎዝላቪያ ያወራል፡፡ ጋዜጠኛው ወደ መስመር ሊመልሰው ቢጥርም ተራ አልሰጥም እያለ ድምጹን ከፍ አድርጎ በእቢኝታ ቀጠለ አጭቤው፡፡ ምክንያቱ ግልጽ ነበር፡፡ ጋዜጠኛው በጠየቀው ጥያቄ ላይ ከአስገደደው አጭቤው መልስ የለውምና፡፡

በአጭቤው አባባል የግለሰብ መብት እንዲከበር የግለሰብን ሁሉንም ማንነነት (identity) ማክበር ያስፈልጋል ከተባለ አንድም የጋራ የሚያደርገን የዜግነት መብትም ሊኖረን ስለማይችል 108 ሚልዮን ሕገ-መንግስት ሊያስፈልገን ነው፡፡ ሰልዚህ የጋራ የሆነ መሰባሰቢያና በዚያ ዙርያ ቅድሚያ የሚሰጥና የግለሰብንም ወጣ ያለ መብትም ያገናዘበ ሕገ-መንግስት ካልተቀረጸ ሌላ መፍትሔ የለም፡፡ የጋራ ሊሆን የሚችልና የሚያሰባስብ ደግሞ ብሔር ነው፡፡ ብሔር የሌላቸው አያታቸውን የማያውቁ ናቸው፡፡ የጋራ መፍትሔ ካልተፈለገ ደግሞ ቀሪው ኃይል ነውና የራስን ቤት (ኦሮሚያ፣ አብሲንኒያ ወዘተ) ማስከበር ነው፡፡