የአልዛይመር ህሙማን ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ "የመርሳት በሽታ የለም" በማለት በሙሉ ድምፅ አፀደቀ!"
Posted: 05 Jan 2020, 12:33
የህወሓት ጠቅላላ ጉባኤ 'በፓርቲው ህልውና እና ቀጣይ እጣፈንታ ላይ ወሳኝ ይሆናል' ያሉትን ውሳኔ ያሳልፋል" ተብሎ ሲጠበቅ "ህወሓት ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ላለመዋሃድ ያሳለፈውን ውሳኔ በሙሉ ድምፅ ተቀብለን አፅድቀናል" ብለው ሀገር ያወቀውን፥ ፀሃይ የሞቀውን ነገር መልሰው አልነገሩንም? ይሄ እኮ "የአልዛይመር ህሙማን ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ "የመርሳት በሽታ የለም" በማለት በሙሉ ድምፅ አፀደቀ!" እንደማለት ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ከሞላ-ጎደል ሁሉም የህወሓት አባላትና አመራሮች ትላንት ላይ የቆሙ፣ በሙታን ታሪክ ላይ የቆዘሙ፣ እንኳን የወደፊቱን አሁን ላይ በዙሪያቸው ያለውን ነባራዊ እውነታ ማየት የተሳናቸው ቆሞ-ቀር ናቸው። እነዚህ እንደ አልዛይመር ህሙማን ታላንት የሆነውንና የተናገሩትን ማስታወስ የተሳናቸው ሰዎች አንድ ላይ ተሰብስበው "የመርሳት በሽታ የለም" የሚል ውሳኔ በሙሉ ድምፅ ቢያፀድቁ ምን ፋይዳ አለው? የአልዛይመር በሽታ የለም ቢሉ፤ ከህመማቸው አይፈውሳቸው፣ የበሽታውን አይነትና ባህሪ አይቀይረው። ትላንት፣ ዛሬም ሆነ ነገ የህወሓቶች መሠረታዊ ችግር መናገርና መፃፍ ሳይሆን የተናገሩትን ማወቅና ማስታወስ ነው!!