የሲሳይ አጌና እና መሳይ መኮንን ፍርሃት ይገባኛል ።
ልክ እንዳሉት ሁከት፣ አመጽ፣ ግድያ ፣ ፍርሃት፣ ድምጽ ዘረፋ፣ ፓርቲ ክልከላ ሁሉ በልዩ ልዩ ቦታዎች ከትግሬ እስከ ባሌ እንደ ሚኖሩ ሁሉም ያምናል ።
ሁሉ ቢስማማ ለተወሰነ ግዜ ለምሳሌ አንድ አመት ቢገፋ ጥሩ ነበር ። ግን በ5 አመታት ይገፋ የሚለው ፍጹም ስህተት ነው ። ለምን?
አንድ፣ የ2012ቱ ምርጫ ተወደደም ተጠላም በቀውስ ታጅቦም ቢሆን አሸናፊ የሚሆነው ብልጽግና ፓርቲ ይሆናል ። ስለዚህ አቢይና ፓርቲው በገዥነት መቀጠላቸው አይቀሬ ነው ። ይህ ደሞ የነ ሲሳይን ፍርሃት ያስወግዳል ።
ሁለት፣ የምርጫው መደረግ ዋና እጅግ ጠቃሚ ትርፉ ሰላም በኢትዮጵያ ማምጣቱ አይደለም ። ሰላም የሚጸናው ምርጫ በመደረጉ ወይ አለ መደረጉ አይደለም ። ዎያኔዎች እና የዘር ጽንፈኞች ለውጥ መቃወማቸው ነው። እነዚህ ደሞ ተዳክመው እስካልከሰሙ ድረስ በቅድመ ምርጫም በድህረ ምርጫም ኢትዮዮጵያ ይኖራሉ ።
ሰልሆነም የምርጫው ትልቅ ፋይዳ ትልቅ የፖለቲካ ልምድና ትምህርት ይገኝበታል። ፓርቲዎች ይፈተኑበታል ። የጎሳም ሆነ የዜጋ ፖለቲካና ፓርቲዎች ይፈተኑበታል።
የምርጫ ቦርድ፣ ሚዲያ፣ ሲቪል ድርጅቶች ሁሉ ይማሩበታል፣ ይፈተኑበታል ።
ያለም ድርጅቶች ይገኙበታል።
ሶስት ። አሁን ያለው ዎያኔ ያስቀመጠው ፓርላማ ይለወጣል።
አራት ፣ ከብልጽግና ውጭ ያሉ ፓርቲዎች የተወሰኑ ወንበሮች አሸንፈው ፓርላማው አጓጊ የክርክር ቦታ ያደጉታል ።
አምስት፣ ገዚው ፓርቲ ራሱ የአምባ ገነንነት እምነት እንዳይይዝ ያደርገዋል ።
የ2012 ምርጫ እሰከነ ችግሩ ትልቅ የፖለቲካ ት/ቤት ሆኖ ያልፋል ። ዴሞክራሲ ሂደት ነው ። ሂደት የሚጀምረው እንደዚህ ነው ።